Hulum News ሁሉም ኒውስ Telegram channel photo

Hulum News ሁሉም ኒውስ

@Hulum_newsPublic Channel

Official channel of Hulum News Buy ads: https://telega.io/c/Hulum_news For paid promotion DM @algiti

World NewsEnglishUnited States
22.7k (22,694 subscribers)
Members
—
Rating
58
Total Posts
Sep 16, 2026, 11:52 AM
Updated
Mar 31, 2026
Created
Stats

You are viewing English content. To see content in other languages, change the language of the site.

Channel Information

Channel Information
Channel NameHulum News ሁሉም ኒውስ
Username@Hulum_news
CategoryWorld News
LanguageEnglish
CountryUnited States
Members22,694
Channel TypePublic Channel
CreatedMar 31, 2026
Last UpdatedSep 16, 2026 • 10 days ago
StatusActive

Ranking

Global Ranking
#70219-46
Language Ranking
#14935+2
Category Ranking
#345+1

Participant Growth (Last 20 Days)

Total: 22.7K
24h growth: -318 1%
03/3104/1004/2105/1206/2708/0209/0709/16

Latest Posts

Photo
🍵ተጠንቀቁ❗️❗️

👉በ3 የሻይ ሲኒ  ደረሰኝ  ምክንያት 300 ሺህ ብር ቅጣት ይጣልባቸዋል።

👉በአዲሱ የታክስ አስተዳደር አዋጅ መሰረት ደረሰኝ አለመስጠት ንብረትዎን ሊያሳጣዎት ይችላል!

👉አንድ ሰራተኛዎ ቸልተኛ ሆና 100 ብር ለሚያወጣ 'ሻይ' ደረሰኝ ባትቆርጥ... ቅጣቱ 100 ብር ሳይሆን 100 ሺህ ብር ነው ተብሏል።

👉ይባስ ብሎ ደግሞ... ሰራተኛዋ ለ3 ደንበኞች ደረሰኝ ካልሰጠች፣ ለድርጅቱ ባለቤት የ300 ሺህ ብር መብረቅ የመሰለ ቅጣት ይወርድበታል።

👉ይህ ቅጣት ደግሞ በአዋጁ አንቀጽ 125 ንኡስ ቁጥር 2 መሰረት በባለስልጣኑ ሊነሳ ወይም 'ይቅር' ሊባል አይችልም!

👉መፍትሄው መክፈል ብቻ ነው! ነጋዴዎች ተጠንቀቁ፣ ሰራተኞቻችሁን አስተምሩ።
1,050007
የደረቀ ውቅያኖስ የለም‼️
“በሱማሊያ በኩል ያለው ቀይ ባህር ደረቀ” የሚለው መረጃ ውሸት ነው‼️
​በማህበራዊ ሚዲያዎች ላይ “በሱማሊያ በኩል ያለው ቀይ ባህር ደረቀ” በሚል የሚሰራጨው መረጃ ሙሉ በሙሉ አሳሳች እና የሐሰት መረጃ (Fake News / Misleading) እንጂ እውነት አይደለም።

​በጂኦግራፊ፣ በውቅያኖስ ጥናት (Oceanography) እና በአካባቢ ጥበቃ ሳይንሳዊ መረጃዎች መሠረት በቀይ ባህርም ሆነ በአደን ባሕረ ሰላጤ አካባቢ ምንም ዓይነት የውኃ መድረቅ አልተከሰተም።

​◉ ሳይንሳዊ እና ጂኦግራፊያዊ እውነታዎች

​ሱማሊያ ከቀይ ባህር ጋር ድንበር የላትም፦ ሱማሊያ የምትገኘው በህንድ ውቅያኖስ እና በአደን ባሕረ ሰላጤ (Gulf of Aden) ዳርቻ ላይ እንጂ በቀይ ባህር (Red Sea) ወሰን ላይ አይደለም። የቀይ ባህር መውጫ (ባብ ኤል-መንደብ) የሚያበቃው በጅቡቲ እና በየመን የባህር ወሰን ላይ ነው።

​የውኃ መጠኑ አልቀነሰም፦ የቀይ ባህር እና የአደን ባሕረ ሰላጤ ውኃ ከታላቁ ህንድ ውቅያኖስ ጋር የተያያዘ በመሆኑ እንደ ተነጠሉ የቤት ውስጥ ሐይቆች (ለምሳሌ እንደ አራል ባህር) የመድረቅ ዕድል የለውም።

​◉ የተሳሳተው መረጃ ምንጭ እና ሳይንሳዊ ምክንያቶች

​የሞገድ መሸሽ (Low Tide) በጨረቃ እና በፀሐይ የስበት ኃይል ምክንያት በየቀኑ የባህር ውኃ ወደ ኋላ የመሸሽ (Low Tide) ክስተት ያጋጥማል።በዚህ ወቅት የባህሩ ዳርቻ ሰፊ ሆኖ ስለሚታይ፣ አጋጣሚውን በቪዲዮ ቀርፀው "ባህሩ ደረቀ" የሚል አሳሳች መረጃ ያሰራጫሉ።

​የባህር ወለል መስፋፋት (Seafloor Spreading)፦ የአፍሪካ እና የአረቢያ ቴክቶኒክ ፕሌቶች እየተራራቁ በመሆናቸው ቀይ ባህር እና የአደን ባሕረ ሰላጤ በየዓመቱ በጥቂት ሚሊሜትር እየሰፉና እየጠለቁ እንጂ እየደረቁ አይደሉም።

​የባህር ወለል መጨመር (Sea Level Rise)፦በአለም አቀፍ ደረጃ በሚታየው የአየር ንብረት ለውጥ እና የዋልታዎች በረዶ መቅለጥ ምክንያት የባህር ወለል መጠን (Sea level) እየጨመረ እንጂ እየቀነሰ አይደለም።

​◉ በማህበራዊ ሚዲያ የተሰራጩት ምስሎች እና ቪዲዮዎች ላይ የሚታየው እውነተኛ ቦታው የት ነው?

​ትክክለኛ ቦታው ምስሎቹ የሚያሳዩት በህንድ (India) ጉጃራት ግዛት የሚገኘውን አላንግ (Alang Ship Breaking Yard) የተባለውን የዓለማችን ትልቁን አሮጌ መርከቦች ማፍረሻ ቦታ ነው።

​በምስሉ ላይ የሚታዩት መርከቦች ​በግራ በኩል የሚታየው ትልቅ የነዳጅ መጫኛ መርከብ (Tanker) ነው።​በቀኝ በኩል የምትታየው ደግሞ "Marco Polo" የተባለች አርጅታ ለመበጣጠስ የመጣች የሽርሽር መርከብ (Cruise Ship) ናት።​ከበስተጀርባ የሚታዩት መርከቦቹን ለመቁረጥ የተዘጋጁ ክሬኖች (Cranes) እና የመበጣጠሻ መሳሪያዎች ናቸው።
​
◉ መርከቦቹ ደረቅ መሬት ላይ እንዴት አረፉ?

​መርከቦቹ አሸዋው ላይ ያረፉት ባህር ደርቆ ሳይሆን ሆን ተብሎ በተደረገ ቴክኒካዊ አሰራር (Beaching Process) ነው። ​ውኃው በጣም በሚሞላበት ጊዜ (High Tide) መርከቦቹን በከፍተኛ ፍጥነት ወደ አሸዋማው ዳርቻ ያስጠጉዋቸዋል። ​ውኃው ወደ ኋላ በሚሸሽበት ጊዜ (Low Tide) መርከቦቹ በደረቁ አሸዋ/ጭቃ ላይ ስለሚቀሩ ሰራተኞች በእግራቸው ሄደው ለመቁረጥ ይመችቸዋል።

​በቪዲዮው ላይ የሚታየው ክስተት በህንድ አገር አሮጌ መርከቦችን ለማፍረስ በባህር ውኃ መሸሽ ወቅት (Low tide) የተቀረፀ ተራ የመርከብ ማፍረሻ ቦታ እንጂ የቀይ ባህር መድረቅ አይደለም። መረጃው ሙሉ ለሙሉ ውሸት ነው።
980000
የ12ኛ ክፍል ፈተና ውጤት ይፋ ሆነ።

የ2018 ዓ/ም የ12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ ፈተና ውጤት ይፋ ተደርጓል። ተፈታኞችም ውጤታቸው ማየት ጀምረዋል።

ውጤት ለማየት ፦
👉 በድረ ገጽ ፡ https://result.eaes.et/
👉 ቴሌግራም፡ https://result.eaes.et/telegram
👉 አጭር የጽሑፍ መልዕክት፡ https://result.eaes.et/sms

በአንድ ጊዜ በርካታ ተማሪዎች ውጤታቸውን ለማየት ስለሚሞክሩ የኔትዎርክ መጨናነቅ ሊያጋጥም ስለሚችል ደጋግሞ መሞከር ይገባል።

የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት ተፈታኞች ቅሬታ ሲኖራቸው በአካል መምጣት ሳያስፈልጋቸው https://result.eaes.et/complaint የሚለውን ማስፈንጠሪያ በመጠቀም ቅሬታቸውን ከነሐሴ 19 እስከ 26/2018 ዓ/ም ከቀኑ 10፡00 ሰዓት ድረስ ማቅረብና ምላሹንም በዛው ማስፈንጠሪያ መከታተል እንደሚችሉ ገልጿል።
951000
Video
"የአንድ መንደር ነዎሪዎች ተጠርገው ሄደዋል!" - ከአደጋው የተረፈ‼️
* በኔፓል የደረሰው የጎርፍ አደጋ የሟቾች ቁጥር 160 የደረሰ ሲሆን የበርካታ የውጭ ሀገር ጎብኚዎች ደህንነት አሁንም አሳሳቢ ሆኗል።
በሰሜናዊ ኔፓል ራሱዋ በተባለው የተራራማ አካባቢ እ ኤ አ ኦገስት 26 ቀን 2026 በድንገት በተከሰተ የበረዶ እና የዓለት መደርመስ ምክንያት የተነሳው የጎርፍ አደጋ ከፍተኛ የሰው ሕይወት እና የንብረት ጉዳት አድርሷል።

የኔፓል ፖሊስ እና የቻይና ቲቤት ባለስልጣናት እስካሁን የ160 ሰዎችን አስከሬን ማግኘታቸውን ያረጋገጡ ሲሆን በርካታ አስከሬኖች በጭቃ እና በፍርስራሾች ውስጥ ተቀብረው በመገኘታቸው የሟቾች ቁጥር የበለጠ ሊጨምር እንደሚችል ተገልጧል።

የኔፓል ቱሪዝም ቦርድ እንደተናገረው በአደጋው ቀጠና 105 የህንድ፣ 54 የአሜሪካ፣ 34 የአውስትራሊያ፣ 33 የእንግሊዝ፣ 24 የካናዳ፣ 19 የማሌዢያ እንዲሁም የሌሎች ሀገራት ዜጎችን ጨምሮ በድምሩ 384 ጎብኚዎች የት እንደገቡ ማወቅ አልተቻለም።

አደጋው በማለዳ ወቅት የተከሰተ በመሆኑ እና የቱሪስት ማረፊያዎች እንዲሁም የኮሚዩኒኬሽን መስመሮች ሙሉ በሙሉ በመውደማቸው ከተጓዦቹ ጋር ግንኙነት ማድረግ አልተቻለም።

ይህንን ተከትሎ የተለያዩ ሀገራት መንግስታት ከፍተኛ ስጋታቸውን እየገለጹ ይገኛሉ።

የኔፓል መንግስት አካባቢውን የአደጋ ጊዜ ቀውስ ቀጠና ብሎ ያወጀ ሲሆን የህንድ፣ የአሜሪካ እና የእንግሊዝ መንግስታት ከኔፓል የነፍስ አድን ቡድኖች ጋር በመተባበር የጠፉ ዜጎቻቸውን ለመፈለግ እየሰሩ ነው።
927002
Photo
የ12ኛ ክፍል ፈተና ውጤት ይፋ አልተደረገም።

የተለያዩ የማህበራዊ ሚዲያ ገጾች የ12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ ፈተና ውጤት መለቀቁን በመግለጽ ተማሪዎችና ወላጀችን የሚያደናግር ሀሰተኛ መረጃ እያሰራጩ ይገኛሉ።

እስካሁን የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት፣ የፈተናው ውጤት ይፋ ስለመደረጉ በይፋ አላሳወቀም።

ትክክለኛ የተረጋገጡ መረጃዎች ከትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት ብቻ የሚገኙ በመሆኑ ተማሪዎች እና ወላጆች ሀሰተኛ መረጃዎችን ከሚያሰራጩ የተለያዩ አካላትና ገጾች ትጠነቀቁ ዘንድ ቲክቫህ ኢትዮጵያ መልዕክት ያስተላልፋል።

የትምህርት ሚኒስትሩ ብርሃኑ ነጋ (ፕ/ር) በ2018 ዓ/ም የ12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ ፈተና ውጤት ዙሪያ መግለጫ በሰጡበት ወቅት የፈተናው ውጤት ሰኞ ወይም እስከ ማክሰኞ ከሰዓት ይፋ ይደረጋል ማለታቸው ይታወሳል።

ውጤት ሰኞ ዕለት ይፋ ያልተደረገ ሲሆን እስከ ማክሰኞ ከሰዓት ይፋ ይደረጋል ተብሎ ይጠበቃል።

የፈተናው ውጤት ይፋ ሲደረግ የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት ብቻ በይፋ የሚያሳውቅ ሲሆን እንዴት ማየት እንደሚቻልም ተቋሙ ገለጻ ያወጣል። እኛም ተከታትለን የምናቀርብ ይሆናል።
949004
Photo
" ተማሪዎች ከምሽቱ 1፡00 ሰዓት ጀምረው ውጤታቸው ማየት ይችላሉ " - የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት

የ2018 ትምህርት ዘመን የኢትዮጵያ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ማጠናቀቂያ ፈተና ውጤት የሚገለጽባቸው አድራሻዎች ይፋ ሆነዋል።

በ2018 ትምህርት ዘመን የኢትዮጵያ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ማጠናቀቂያ ፈተና ውጤትን ተፈታኞች  ዛሬ ነሐሴ 19 ቀን 2018 ዓ/ም ከምሽቱ 1፡00 ሰዓት ጀምረው የሚከተሉትን አማራጭ ማስፈንጠሪያዎችን (Link) በመጠቀም ማየት የሚችሉ መሆኑን የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት አሳውቋል።

በተያያዘም ተፈታኞች ቅሬታ ሲኖራቸው በአካል መምጣት ሳያስፈልግ https://result.eaes.et/complaint የሚለውን ማስፈንጠሪያ በመጠቀም ቅሬታቸውን ከነሐሴ 19 እስከ 26/2018 ዓ/ም ከቀኑ 10፡00 ሰዓት ድረስ በማቅረብ ምላሹንም በተመሳሳይ ማስፈንጠሪያ በኩል መከታተል የሚችሉ መሆኑን አገልግሎቱ ገልጿል።

ውጤት የሚገለጽባቸው ማስፈንጠሪያዎች፡-
- በድረ ገጽ ፡ https://result.eaes.et/
- ቴሌግራም፡ https://result.eaes.et/telegram
- አጭር የጽሑፍ መልዕክት፡ https://result.eaes.et/sms
850000
ነገ ነሐሴ 17 ቀን 2018 ዓ.ም የጥገና ሥራ ለማከናወን የኃይል አቅርቦት የሚቋረጥባቸው አካባቢዎች ፡-

✅ ከጠዋቱ 2፡00-9፡30

👉አለም ባንክ፣ ኢንዲያና ት/ቤት፣ ታፍ ማደያ፣ አቃቂ ብሩህ ተስፋ ት/ቤት፣ ኮፊ ሲቲ ፣ ገነት ሆቴል፣ ቡልጋሪያ፣ ቄራ፣ ኦሮሚያ ሳርቤት ቢሮ እና አካባቢው፣   

👉ቂሊንጦ ኮንዶሚየም፣ አዲስ አበባ ሳይንስ እና ቴክኖሎጂ ዮኒቨርስቲ፣ ቂሊንጦ ላይ ሰፈር፣ ቂሊንጦ ሚካኤል፣ ሌስ ፍራንስ ት/ቤት፣ ጥሩነሽ ቤጂንግ ሆስፒታል፣ አሳማ ጊቢ፣ ኮዬ አደባባይ፣ ዋሊያ ቢራ እና አካባቢው፣

👉በባህርዳር፣አባይማዶ፣ማራኪ ቀበሌ፣120 ቪሌጅ እና አካባቢው፣

✅ ከጠዋቱ 2፡00-11፡00

👉አወልያ  መስጅድ፣ ካኦጄጄ፣ አቡነሃብተማርያም፣ አስኮ ጨረታ፣ 40/60 ኮንዶሚኒየም፣ ብርጭቆ ቀይ መስቀል ጋር፣ ብርጭቆ ማርያም ቤተክርስቲያን፣ አርሴማ ቤተክርስቲያን እና አካባቢው፣

👉አስኮ አዲስ ሰፈር፣ኦሮሚያ ሜዳ፣ አዲስ አበባ ቆዳ፣ መድሀኒያለም ቤተክርስቲያን፣ መልካ በሮ 01 ቀበሌ እና አካባቢው፣  

👉አውጉስታ፣ ወይራ ሰፈር፣ ወይራ ኮንዶሚኒየም፣ ሞቢል፣ የድሮው ራሺያ ካምፕ፣ ተዘንአ ሆስፒታል ፣ ጦርሃይሎች ጎልፍ ክለብ እና አካባቢው ፣

👉ጉርድ ሾላ ቴሌ፣ የካ ሞሰብ፣ ትምህርት መሳሪያዎች፣ ጃክሮስ አደባባይ ፣ ሜታ ቢራ ፋብሪካ እና አካባቢው፣

👉ኮተቤ ኪዳነ ምህረት፣ አራራት ሆቴል፣ ሀይሌ ሪዞርት ሆቴል፣ እስራኤል ኢምባሲ፣ የካ ክፍለ ከተማ ድረስ እና አካባቢው

👉አፍሪካ ሕብረት፣ መቻሬ ኮንዶሚኒየም፣ ልደታ ፀበል፣ ሜክሲኮ፣ ትንባሆ ሞኖፖል፣ ሳር ቤት፣ በአደማ አዋሽ መልኬሳ እና አካባቢው የኃይል አቅርቦት ይቋረጣል፡፡

ስለሆነም በአካባቢው የምትገኙ ክቡራን ደንበኞቻችን ይህንኑ በመገንዘብ አስፈላጊውን ቅድመ ዝግጅት እንድታደርጉ በአክብሮት እናሳውቃለን
857003
Photo
#የ12ኛ ክፍል ውጤት‼️

ዘንድሮ በአጠቃላይ ፈተናውን ከወሰዱ ተማሪዎች መካከል ማለፍ የቻሉት 70 ሺ 544 ናቸው።

ካለፉት መካከል በተፈጥሮ ሳይንስ 16.5 በመቶ ሲሆኑ በማህበራዊ ሳይንስ ደግሞ 8.33 በመቶ ናቸው።
በዘንድሮ የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና 563 ሺ 960 ተማሪዎች ተመዝግበው 550 ሺ 210 ተማሪዎች ፈተናውን ወስደዋል። የትምህርት ሚኒስትሩ ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ መግለጫ እየሰጡ ይገኛሉ።
853001
#የ12ኛ ክፍል ውጤት‼️ ዘንድሮ በአጠቃላይ ፈተናውን ከወሰዱ ተማሪዎች መካከል ማለፍ የቻሉት 70 ሺ 544 ናቸው። ካለፉት መካከል በተፈጥሮ ሳይንስ 16.5 በመቶ ሲሆኑ በማህበራዊ ሳይንስ ደግሞ 8.33 በመቶ ናቸው። በዘንድሮ የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና 563 ሺ 960 ተማሪዎች ተመዝግበው 550 ሺ 210 ተማሪዎች ፈተናውን ወስደዋል። የትምህርት ሚኒስትሩ ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ መግለጫ እየሰጡ ይገኛሉ።
865000
Photo
ውጤት መቼ ይታያል❓

ተማሪዎች ውጤታቸውን ከሰኞ ጠዋት ወይም ማክሰኞ ከሰዓት ጀምሮ መመልከት ይችላሉ።

በውጤታቸው ላይ ቅሬታ የሚኖራቸው ከሆነም 5/6 ቀናት ቅሬታ የማቅረቢያ ጊዜ የሚሰጣቸው ይሆናል።
830000
Photo
ምፅዋ በካርጎ አውሮፕላኖች ተጨናንቋል‼️
ሱዳን ከባባድ መሣሪያዎችን በኤርትራ ምፅዋ እያራገፈች ነው‼️
ጀነራል አል_ቡርሃን ከባባድ መሣሪያዎችን በኤርትራ ምፅዋ አውሮፕላን ማረፊያ በብዛት እያራገፈ እንሚገኝ በሳተላይት ምስል ተረጋግጧል ።
ከሱዳን ተነስተው በምፅዋዋ አውሮፕላን ማረፊያ ያረፉ በርካታ የጭነት አውሮፕላኖች ከባባድ መሳሪያዎችን፣ ተወንጫፊ ሚሳይሎችንና ጥይት እያራገፉ መሆናቸውን የሳተላይት ምስሎች አሳይተዋል።
ከሱዳን በተጨማሪ ከቤላሩስ እንዲሁም ከኢራን የመጡ የጭነት አውሮፕላኖች ከሁለት ቀን በፊት ምፅዋ እንዳረፉ ከሳታላይት ምስሎች ለማየት ተችሏል።
967002
ኢትዮ-ኤርትራ‼️
የኤርትራ ሉዓላዊነት ለድርድር የሚቀርብ አይደለም-የኤርትራ ማስታወቂያ ሚኒስቴር‼️
አሁን ባለው የኤርትራ-ኢትዮጵያ ውጥረት የኤርትራ ሉዓላዊነት ለድርድር የማይቀርብ መሰረታዊ ጥያቄ ነው' ሲሉ የኤርትራ ማስታወቂያ ሚኒስቴር ገልጿል።
የንግድ ወደብ መዳረሻ መፈለግ ሌላ ጉዳይ ነው፤ የሌላ ሀገር ግዛትን ለመውሰድ የሚደረግ ጥረት ሌላ ጉዳይ ነው።" ብሏል።

ኤርትራ ከኢትዮጵያ የጠየቀችው የግዛት ጥያቄ የላትም፣ የኢትዮጵያን መሬት ወይም ሀብት አትጠይቅም እንዲሁም ኢትዮጵያ በዓለም አቀፍ ደረጃ እውቅና ያገኘችውን ድንበሮች መለወጥ አትፈልግም። ኢትዮጵያ በቀጠናው የሚገኙ ወደቦችን በድርድር ለንግድ እንዳትጠቀም ኤርትራ ተቃውማ አታውቅም። በዓለም ላይ የባህር ዳርቻ የሌላቸው አገሮች የሌሎች ሀገራትን ሉዓላዊነት ሳይጥሱ የአጎራባች ሀገራት የባህር ዳርቻዎችን በመጠቀም ዓለም አቀፍ ንግድ ያካሂዳሉ።
ኤርትራ የሌላ ሀገር ግዛት አትጠይቅም፤ እንዲሁም ከኢትዮጵያ እና ከሁሉም ጎረቤት ሀገራት ጋር ሰላማዊና ለሁለቱም ወገኖች ጠቃሚ የሆነ ግንኙነት ለመፍጠር ትሻለች።
ድርድር የማይደረግባቸው ጉዳዮች ግን የኤርትራ ሉዓላዊነት እና የግዛት አንድነት ናቸው'ብለዋል።
903002
Photo
በአዲስ አበባ ከተማ የ26 ዓመቷ እናት በአንድ ጊዜ 4 ህፃናትን ተገላገለች።

በአዲስ አበባ በሚገኘው ጥሩነሽ ቤጂንግ አጠቃላይ ሆስፒታል የ26 ዓመቷ እናት በአንድ ጊዜ አራት ህፃናትን በሰላም መገላገሏ ተሰምቷል።

እናትየዋ አራት ፅንሶችን መፀነሷ በእርግዝና ክትትል ወቅት መለየቱን የሆስፒታሉ ዋና ሥራ አስኪያጅና የማህፀንና ፅንስ ስፔሻሊስት ዶ/ር እሸቱ ታደለ ገልጸዋል።

አራት ፅንሶችን የያዘ እርግዝና ለእናቲቱም ሆነ ለሚወለዱት ህፃናት ከፍተኛ ክትትልና ጥንቃቄ የሚፈልግ በመሆኑ የወሊድ ቀኗ ከመድረሱ ከአንድ ወር በፊት ጀምሮ በሆስፒታሉ ዋርድ እንድትቆይ ተደርጎ የሌት ተቀን ክትትል ሲደረግላት ቆይታለች።

በወሊድ ወቅትም ለአራቱ ጨቅላ ህፃናት የሚያስፈልጉ ማረፊያዎችና የድጋፍ መሳሪያዎች አስቀድመው መዘጋጀታቸውን ዶ/ር እሸቱ መግለፃቸውን ብስራት ሬዲዮ ከጥሩነሽ ቤጂንግ አጠቃላይ ሆስፒታል አገኘሁት ያለው መረጃ ያመላክታል።

በዶ/ር እሸቱ ታደለና በማህፀንና ፅንስ ስፔሻሊስቱ ዶ/ር ናትናኤል የተመራው የህክምና ቡድን የቀዶ ጥገና ሂደቱን በስኬት ማጠናቀቁን ሆስፒታሉ አስታውቋል።

እናትየው እና አራቱ ህፃናት በአሁኑ ወቅት በጥሩ ጤንነት ላይ እንደሚገኙ ተገልጿል።

በሆስፒታሉ ከሦስት ዓመት በፊት የ24 ዓመቷ እናት በሪፈር ከጤና ጣቢያ መጥታ አራት ህፃናትን በሰላም መገላገሏ ተገልጿል።
976008
Photo
በከባድ ዝናብ አማካኝነት ጃፓን ውስጥ ስድስት ሰዎች ሞተዋል ተባለ

በምስራቅ ጃፓን ቺባ ግዛት ከፍተኛ ዝናብ በመጣሉ ቢያንስ ስድስት ሰዎች መሞታቸው የተነገረ ሲሆን፤ አምስት ሰዎች ደግሞ ቆስለዋል።

የጃፓን ባለሥልጣናት ‹‹ታይቶ የማይታወቅ›› ሲሉ የገለጹት ዝናብ፤ ከ20 ሺህ በላይ አባወራዎችን የኤሌክትሪክ ኃይል ሲቀንስ፣ 7 ሺህ ተጓዦች ደግሞ በቶኪዮ ናሪታ አየር ማረፊያ በአንድ ሌሊት በረራቸው እንዲዘገይ አድርጓል።        

ይህ የጎርፍ አደጋ የተከሰተው በዚህ ሳምንት በጃፓን እና በአጎራባች አገሮች ውስጥ ተከታታይ አውሎ ነፋሶች ከተከሰቱ በኋላ ነው።

የጃፓን የሜትሮሎጂ ኤጀንሲ እንደገለጸው፤የቅርብ ጊዜውን የጎርፍ አደጋ ያመጣው ወደ አገሪቱ ምሥራቅ የሚፈሰው ሞቃታማና እርጥበት አዘል አየር ሲሆን፤ይህም ከላይ ካለው ቀዝቃዛ አየር ጋር ተዳምሮ የከባቢ አየር ሁኔታን እጅግ ያልተረጋጋ ያደርገዋል ሲል ቢቢሲ ዘግቧል።
932003
የራያ ቆቦው ውጊያ‼️
በአማራ ክልል በሰሜን ወሎ ​ራያ ቆቦ ዛሬ ነሐሴ 9/2018 ዓ.ም ማለዳ 1:30 የተቀሰቀሰው ውጊያ ለተወሰነ ጊዜ ከቆየ በኋላ በአሁኑ ሰዓት መረጋጋት ማሳየቱን የመረጃ ምንጮች ገለጹ።

​ከማለዳው አንድ ሰዓት ተኩል (1:30) ጀምሮ ሲካሄድ የቆየው ውጊያ ለአንድ ሰዓት ተኩል ያህል የዘለቀ ሲሆን፣ 3:00 አካባቢ ጀምሮ ውጊያው ጋብ ማለቱ ተሰምቷል።
ወደ ዋጃ መስመር ተንቀሳቅሶ የነበረው መከላከያ ሰራዊት ወደ ካምቱ ተመልሷል።
​በአዲስ ቅኝ አቅጣጫ የህወሃት ታጣቂዎች  ቁጥጥር ስር የነበሩ የባቡር ጣቢያ ጊዜያዊ ካምፖችን ለቀው ወደ ኋላ አፈግፍገዋል።
ይህንን ተከትሎ በራያ ቆቦ ከተማ ውስጥ የተሽከርካሪ እንቅስቃሴ ለጊዜው ቆሞ የነበረ ቢሆንም አሁን መደበኛ እንቅስቃሴ መጀመሩን ምንጮች ለአዩዘሀበሻ ገልፀዋል።
(አዩዘሀበሻ)
937001
Photo
"ታጣቂዎች ከውጭ ኃይሎች ጋር በመሻረክ 'ያልተቀደሰ ጋብቻ' ፈጥረዋል" አሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ‼️
👉እኛ ከእስር የለቀቅናቸው ወደ አሰራቸው ቡድን የተገለበጡም አሉ ብለዋል።
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር )  በኦሮሚያ፣ አማራ እና ትግራይ ክልሎች የሚንቀሳቀሱ ታጣቂ ኃይሎች መንግሥትን ማሸነፍ እንደማይችሉ ሲረዱ "ያልተቀደሰ ጋብቻ" መፍጠራቸውን ገለጹ።
ታጣቂዎቹ ኤርትራን እና ሱዳንን ጨምሮ ከውጭ ተዋናዮች ድጋፍ ለማግኘት የሚያደርጉትን እንቅስቃሴ ሕዝቡ በጥንቃቄ ሊረዳው እንደሚገባ ያስገነዘቡት ጠቅላይ ሚኒስትሩ፤ ቀደም ሲል ሀገሪቱን በብቸኝነት ይመራ የነበረው ቡድን ያጣውን ሥልጣን በኃይል ለመመለስ ማሰቡ ለሀገሪቱ ግጭቶች መንስኤ መሆኑን ገልጸዋል።
ሆኖም እኛ እውነት ስለያዝን እናሸንፋለን ብለዋል።
1,2300010
Photo
የጦርነት ዝግጅቱ‼️
ህወሃት በራያ የጦርነት ዝግጁትን ወደ መጨረሻ ምዕራፍ እያደረሰ ይገኛል።
በዚህም በሁሉም አካባቢዎች የሚደረጉ ስብሰባዎች ከቀትር ወደ ማታ እንዲሸጋገሩ ትዕዛዝ ሰጥቷል።
ለራያ አዘቦ 1,000 ሊትር ነዳጅ እና ለመኮኒ ከተማ 3,000 ሊትር ነዳጅ እንዲከፋፈል ገልጿል።
እንስሳትን ጨምሮ የስንቅ አቅርቦት፣ውሃ የሚያቀርቡ ቦቢዎች እንዲሁም ለቀብር የሚያስፈልጉ ቁሳቁሶች እስከ ነሐሴ 10/2018 ዓ.ም እንዲዘጋጅ ለሁሉም አመራሮቹ ትዕዛዝ መስጠቱ ታውቋል።
ጦርነት ይብቃ፣ ችግሮች በውይይት ይፈቱ።
1,100008
Video
ዝንጀሮውም አረንጓዴ አሻራውን አኖረ

🐒🌱 በዘንድሮው የአንድ ጀምበር የችግኝ ተከላ ንቅናቄ ከተተከሉት 805.3 ሚሊዮን ችግኞች መካከል፤ ይህ ዝንጀሮ የተወሰኑትን ተክሏል
939008
Photo
ከላይ በምስሉ የምትመለከቷቸው ወንዶች በተመሳሳይ ፆታ ጋብቻ መስረተው  በመገኘታቸው በቤንሻንጉል ጉምዝ ክልል በባምባሲ ከተማ ፓሊስ በቁጥጥር ስር ዋሉ !   

ባምባሲ ሐምሌ 30/2018 ዓ.ም| ከማህበረሰቡ ወግና ባህል እንዲሁም እምነት ያፈነገጡ ግለሰቦችን በቁጥጥር ስር በማዋል ምርመራ እየተደረገ መሆኑ ተገለፀ ።

በቤንሻንጉል ጉምዝ ክልል በባንቢስ ከተማበፎቶ የተመላከቱት እኒሁ ታደለ እናውጋውና በፀሎት እንየው የተባሉ ተጠርጣሪዎች በተመሳሳይ ፆታ ጋብቻ በመመስረታቸው...

በማህበረሰቡ ጥቆማና ተጠርጣሪዎቹም የእምነት ቃላቸውን በሰጡት መሰረት ፖሊስ ተገቢውን የምርመራ ስራ መጀመሩንና በቀጣይ ውጤቱን የምናሳውቅ መሆኑን እንገልፃለን' ሲል የባንቢስ ከተማ አስተዳደር ገልጿል።
918003
Photo
የጆኒ እና ሴዶ MMA ፍልሚያ መግቢያ ትኬት VVIP 100 ሺ ብር መሆኑ ተገለፀ::

ቀን: ነሐሴ 21
ቦታ: አድዋ 00 ሙዚየም (Adwa 00 Museum)
ቲኬት ለመግዛት: በ M-Pesa

የቲኬት ዓይነቶች እና ዋጋ:

1. VVIP Ringside - 100,000 የኢትዮጵይ ብር

* ልዩ የሪንግ አጠገብ መቀመጫ
* ያልተገደበ የምግብ እና የመጠጥ አገልግሎት
* ወደ ተወዳዳሪዎች ልብስ መቀየሪያ ክፍል የመግባት እድል
* መቀመጫ የመምረጥ መብት

2. VVIP Premium - 50,000 የኢትዮጵይ ብር

* 2ኛ ተከታታይ ረድፍ መቀመጫ
* 2 የምግብ እና 10 የመጠጥ ኩፖኖች
* መቀመጫ የመምረጥ መብት

3. VVIP Normal - 30,000 የኢትዮጵይ ብር

* ከ 3ኛ እስከ 5ኛ ረድፍ መቀመጫዎች
* 2 የምግብ እና 7 የመጠጥ ኩፖኖች
* መቀመጫ የመምረጥ መብት

4. VIP - 20,000 የኢትዮጵይ ብር

* 1 የምግብ እና 4 የመጠጥ ኩፖኖች
* መቀመጫ የመምረጥ መብት

5. Regular - 10,000 የኢትዮጵይ ብር

6. Early Bird - 4,000 የኢትዮጵይ ብር
991006
Photo
የ20 ዓመት ሴት ልጅ የገዛ ልጁን አስገድዶ ግብረ ስጋ ግንኘነት ያደረገው አባት በእስራት ተቀጣ‼️

     ሐምሌ 14, 2018 ዓ.ም ምዕራብ ዓባያ ወረዳ።

በምዕራብ ዓባያ ወረዳ ብርብር ከተማ መንደር ሰባት ነዋሪ የሆኑት ኢንስፐክተር ግርማ ጌታቸው እና ከወ/ሮ መስከረም ሙሉጌታ የተወለደችው ልጅ ሐና ግርማ ዕድሜዋ 20 ዓመት የደረሰና የዘጠነኛ ክፍል ተማሪ  ስትሆን መንግሥት ባስታጠቀው ሽጉጥ በማስፈራራት በቀን 6/9/2018 ዓ/ም ከምሽቱ 2 ሰዓት አካባቢ ቡና እያፈለች ባለችበት ኳላ በመምጣት በጉልበት ወደ መኝታ ክፍል በማምራት የለበሰችሁን ቀምስ በማወለቅ ክብረ ንጽህና በመገርሰስ በጉልበት የግብረ ስጋ ግንኙነት ሲፈፅም ልጅቷ ባሰማችው የድረሱልኝ ጥሪ ጎረቤት በመሰማት መደፈራዋን ከአንደበቷ ሰምተው ሲያረጋግጡ  ለፖሊስ ጥቆማ በማድረግ የማጣራት ስራ በመስራት በህግ ሲታይ ቆይቶ የምዕራብ አባያ ወረዳ ፍ/ቤት በተከሳሹ ላይ በዛሬው ዕለት በዋለው ችሎት 9 ዓመት ከ3 ወር ፅኑ እስራት ተፈርዶበታል ሲል ምዕራብ ዓባያ ወረዳ ኮሙኒኬሽን ነው የዘገበው።
369003
Photo
ገላሽን በሙቅ ውሃ አጥብሻለሁ በማለት የ2 ዓመት ህፃን እንዳትጮህ አፉን በማፈን የአስገድዶ መድፈር ወንጀል የፈፀመው ግለሰብ በእስራት ተቀጣ

በአሶሳ ዞን ባምባሲ ወረዳ ኤዳ ዳቡስ ቀበሌ ጎጥ አንድ በሚባል አካባቢ ነው የወንጀል ድርጊቱ ተፈፅሟል።የባምባሲ ወረዳ ፖሊስ ፅህፈት ቤት አዛዥ ኮማንደር ሀሩን ሄረላ ከብስራት ሬዲዮ ጋር በነበራቸው ቆይታ እንደገለጹት ተከሳሽ አወድ አልሀሪብ የተባለ ሲሆን ግንቦት 16 ቀን  2018 ከረፍዱ 4፡00 ሰዓት የወንጀል ድርጊቱን ፈፅሟል።

የ2 አመት ህፃን የሆነችውን ገላሽን በሙቅ ውሃ አጥብሻለሁ በማለት እናቷ ውሃ ልትቀዳ መሄዷን በማረጋገጥ ወደ ራሱ መኖሪያ ቤት ከወሰዳት በኋላ አፏን በማፈን የአስገድዶ መድፈር  ወንጀል መፈፀሙን ተናግረዋል፡፡

 የባምባሲ ወረዳ ፖሊስ የምርመራ መዝገቡን በሰውና በሰነድ ማስረጃዎች በማስደገፍ ለዐቃቤ ህግ ያቀርባል  ዐቃቤ ህጉም ተከሳሹ በኢፌዲሪ የወንጀል ሕግ አንቀጽ 627(1) ስር በተደነገገው የአስገድዶ መድፈር ወንጀል ክስ በመመስረት ለባምባሲ ወረዳ ፍርድ ቤት ያቀርባል፡፡

ፍርድ ቤቱ የቀረበውን ማስረጃ ከመረመረ በኋላ ተከሳሹን ጥፋተኛ መሆኑን በማረጋገጥ የወንጀሉን ክብደትና የቅጣት ማክበጃ እና ማቅለያ ሁኔታዎችን በማገናዘብ ሐምሌ 13 ቀን 2018 ዓ.ም. በዋለው ችሎት በ19 ዓመት ፅኑ እስራት እንዲቀጣ ወስኖበታል ሲሉ ኮማንደር ሀሩን ሄረላ ጨምረው ለብስራት ሬዲዮ ተናግረዋል፡፡
218007
Photo
ነገ በአዲስ አበባ ሰላማዊ ሰልፍ ይደረጋል። ሰልፉ ተጀምሮ እስከሚጠናቀቅ ወደ መስቀል አደባባይ የሚወስዱ መንገዶች ለተሽከርካሪ ዝግ እንደሚሆኑ የአዲስ አበባ ፖሊስ ዋና ጠቅላይ መምሪያ አስታወቀ ::

#ከመገናኛ በ22 አደባባይ ወደ መስቀል አደባባይ ቅ/ዑራኤል አደባባይ
#በቦሌ መንገድ ወደ መስቀል አደባባ ኦሎምፒያ አደባባይ
#ከጎተራ ወደ መስቀል አደባባይ ለከባድ ተሽከርካሪ አጎና ሲኒማ መስቀለኛ ለቀላል ተሽከርካሪ ጥላሁን አደባባይ
#ከሜክሲኮ አደባባይ ወደ መስቀል ለገሀር መብራት
#ከለገሀር ቴሌ ማቋረጫ ወደ ስታዲዮም ለገሀር ቴሌ ማቋረጫ
#ከአራት ኪሎ ወደ መሰቀል አደባባይ ብሔራዊ ቤተ-መንግስት
#ከካሳንቺስ በመቅረዝ ሆስፒታል ወደ መስቀል አደባባይ መቅረዝ ሆስፒታል አጠገብ
#ከአምባሳደር ቴአትር ወደ መሰቀል አደባባይ ሐራምቤ መብራት የሚወስዱ መንገዶች ከንጋቱ 11:00 ሰዓት ጀምሮ ፕሮግራሙ እስከሚጠናቀቅ መንገዶቹ ለተሽከርካሪ ዝግ ይሆናሉ።

ከዛሬ ሐምሌ 10 ቀን 2018 ዓ/ም ጀምሮ በመስቀል አደባባይና በዙሪያው ባሉ መንገዶች ከምሽቱ 12፡00 ሰዓት ጀምሮ ተሽከርካሪ ለአጭርም ሆነ ረዥም ሠዓት ማቆም የተከለከለ መሆኑን የአዲስ አበባ ፖሊስ ዋና ጠቅላይ መምሪያ አስታውቋል።
753002
Photo
ሴት መስሎ በመቅረብ ስርቆት ለመፈጸም ሲንቀሳቀስ የነበረ ግለሰብ በፖሊስ ቁጥጥር ስር ዋለ።

10/11/2018ዓ/ም | በሺንሽቾ ከተማ አስተዳደር ሴት መስሎ በመቅረብ ህብረተሰቡን ለመሸወድ እና የተለያየ ስርቆት ለመፈጸም ሲንቀሳቀስ የነበረው ግለሰብ በቁጥጥር ስር ውሎ ምርመራ እየተደረገበት እንደሚገኝ የከተማ አስተዳደሩ ፖሊስ ጽ/ቤት አስታወቀ።

ግለሰቡ በቁጥጥር ስር ሊውል የቻለው በሺንሽቾ ከተማ አስተዳደር በሜጦማ ቀበሌ ልዩ ስሙ መምህራን መንደር ተብሎ በሚጠራው አካባቢ መሆኑ ታውቋል።

አቡሽ የተባለውና የትውልድ ስፍራው በምዕራብ ባደዋቾ ቆቶ ቀበሌ የሆነው ይህ ግለሰብ ወንድነቱን በመደበቅ ራሱን ሙሉ በሙሉ ወደ ሴትነት በመለወጥ ህዝብን ሲያታልል እንደነበር ተገልጿል።

ግለሰቡ የወንጀል ዓላማውን ለማሳካት የሴት ቀሚስ ፣ ሰው ሰራሽ ፀጉር (ዊግ) እና የሴት ጡት መያዣ በመጠቀም ራሱን በመለወጥ ስርቆት ለመፈጸም ሲንቀሳቀስ ነበር።

የሺንሽቾ ከተማ አስተዳደር ፖሊስ አዛዥ ም/ኢ/ር አድማሱ ሱሎሮ እንደገለጹት ግለሰቡ በተደረገበት የህዝብ ጥቆማ በቁጥጥር ስር ሊውል የቻለ ሲሆን በአሁኑ ወቅትም በጸጥታ ኃይሎች ተይዞ ጥልቀት ያለው ምርመራ እየተደረገበት ይገኛል።

Via፦ ሺንሽቾ  መንግስት ኮሙኒኬሽን
913008
Video
በቦሌ አትላስ አካባቢ በጣለው ከባድ ዝናብና ንፋስ በአንድ ተሽከርካሪ ላይ ጉዳት ደረሰ

በትናንትናው ዕለት ከላይ በቪዲዮ እንደምትመለከቱት በአስደንጋጭ ሁኔታበዋና ከተማዋ ቦሌ አትላስ ተብሎ በሚጠራው አካባቢ በጣለው ኃይለኛ ዝናብ እና በነፈሰው ብርቱ ንፋስ ምክንያት...

ከአንድ የግንባታ ቦታ ላይ የብረት ቁሳቁሶች ተፈንቅለው በመውደቃቸው በአቅራቢያው በነበረ ዘመናዊ መኪና ላይ ጉዳት ማድረሳቸው ታውቋል።

ምንም እንኳን በንብረት ላይ ጉዳት ቢያስከትልም በሰው ሕይወትም ሆነ አካል ላይ የደረሰ ምንም ዓይነት ጉዳት እንደሌለ ተረጋግጧል።
1,240004
Photo
ነገ ሀምሌ 08/2018 ዓ.ም ታሪካዊ የሀገራዊ ምክክር ጉባኤ በመዲናችን አዲስ አበባ ይጀመራል፡፡ ከመላ ሀገሪቱ የተውጣጡ የጉባኤው ተሳታፊዎችም ወደ ከተማችን ገብተዋል፡፡

የጉባኤው ተሳታፊዎች በሲኤምሲ መስመር የተባበሩት አደባባይ ወደ ሚገኘው አዲስ አበባ ዓለም አቀፍ ኮንቬንሽን ሴንተር ጠዋትና ማታ ሲገቡና ሲወጡ የሚጓዙባቸው መስመሮች ማለትም ከሲቪል ሰርቪስ ዩኒቨርስቲ በሳህሊተ ምህረት አንዲሁም ከኢትዮ ቻይና መስመር በሳህሊተ ምህረት እስከ አዲስ ዓለም አቀፍ ኮንቬንሽን ሴንተር የትራፊክ መጨናነቅ ያጋጥማል፡፡

በመሆኑም ከነገ ጀምሮ ጉባኤው እስከሚጠናቀቅበት ጊዜ ድረስ በመስመሮቹ የምትጓዙ አሽከርካሪዎች አስቀድማችሁ አማራጭ መንገዶችን እንድትጠቀሙ ከወዲሁ እናሳውቃለን፡፡

የአዲስ አበባ ትራፊክ ማኔጅመንት ባለስልጣን
3,750005
Video
የኢራን የሚሳኤል ዝናብ ‼️
አሜሪካ እና ኢራን ጦርነቱን በስምምነት ለማቆም ተቃርበው የነበረ ቢሆንም ከባለፈው ሳምንት ጀምሮ ከባድ የተኩስ ልውውጥ ውስጥ ገብተዋል፣ የተኩስ አቁሙም ሙሉ ለሙሉ ፈርሷል።
ኢራን አንድ የአሜሪካ መርከብን በሆርሙዝ ሰርጥ መትታ ማመጧን የገለፀች ሲሆን በባህሬን እና ኩዬት በሚገኘው የአሜሪካ የጦር ቤዞች ላይ አዳሩን የሚሳኤል፣የድሮን እና የክላስተር ቦንብ ጥቃት እንደዝናብ አዝንባለች። ባህሬን የሚገኘውን የአሜሪካ የጦር ቤዝ ሙሉ ለሙሉ ማውደሟን በወታደራዊ ቃል አቀባያዋ በኩል ይፋ አድርጋለች።
የአሜሪካ ጥቃት በዚሁ ከቀጠለ በቀጠናው የሚገኙ ሀገራትን መሰረተልማት እንደምታወድም ኢራን አሳውቃለች።
ቪዲዮ:- በባህሬን ላይ አዳሩን የተፈፀመ ጥቃት
1,040006
Photo
Breaking News
እንደገና ፈተና አለ‼️
ከ2010 ዓ.ም ጀምሮ እስከ 2015 ዓ.ም በመጀመሪያ ዲግሪ፣ በሁለተኛ እና በሦስተኛ ዲግሪ የተመረቃችሁ ወይም የመውጫ ፈተና ሳትፈተኑ የዲግሪ ባለቤት የሆናችሁ በሙሉ እንደገና የትምህርት ማስረጃችሁን ለማረጋገጥ ሲባል ሊፈተኑ ነው ተብሏል።

በጉዳዩ ላይ አስተያየት ለመስጠት በኢፌዴሪ ትምህርትና ስልጠና ባለስልጣን የፌስቡክ ገጽ ላይ በተለቀቀው ሊንክ እየገባችሁ መሙላት ትችላላችሁ።
4,380004
🎓 " ከ2010 ዓ/ም እስከ 2015 ዓ/ም የዲግሪ ተመራቂዎች በሙሉ የትምህርት ማስረጃቸውን ለማረጋገጥ በድጋሚ ፈተና ሊፈተኑ ነው " በሚል እየተሰራጨ ያለው መረጃ የተሳሳተና ህዝብ አደናጋሪ ነው።

በተለያዩ የማህበራዊ ሚዲያ ገጾች (በፌስቡክ እና ቲክቶክ) ላይ የኢፌዴሪ ትምህርትና ስልጠና ባለስልጣን ያዘጋጀውንና ለህዝብ አስተያየት ይፋ ያዳረገውን አዲስ ረቂቅ መመሪያ በማዛበት፣ " ከ2010 እስከ 2015 ዓ.ም የመውጫ ፈተና ሳይፈተኑ በመጀመሪያ፣ ሁለተኛና ሶስተኛ ዲግሪ የተመረቁ ተማሪዎች በሙሉ የትምህርት ማስረጃቸውን ለማረጋገጥ ሲባል በድጋሚ ፈተና ሊሰጣቸው ነው " በሚል እየተሰራጨ ያለው መረጃ ፍጹም የተሳሳተ እና ህዝብን የሚያደናግር ነው።

ህዝብ አስተያየት እንዲሰጥበት ይፋ የተደረገው መመሪያ በትክክል እነማንን ነው የሚመለከተው ?

ይህ መመሪያ/አሰራር የሚመለከተው በቀድሞው ዲፕሎማ (10+3፣ 12+2 ወይም ቴክኒክና ሙያ ደረጃ 4 ስልጠና) ተመርቀው፣ ነገር ግን የደረጃ አራት የብቃት ማዕቀፍ (COC) ሳይኖራቸው የመጀመሪያ ዲግሪ፣ ሁለተኛ ዲግሪ (MA) ወይም ሦስተኛ ዲግሪ (PhD) የያዙትን ብቻ ነው።

እነዚህ ዜጎች የትምህርት ማስረጃቸውን ለማረጋገጥ አሁን በያዙት የትምህርት ደረጃ/የያዙት ዲግሪን መሰረት ተደርጎ የሚሰጠውን ፈተና መውሰድና ማለፍ ይኖርባቸዋል።

በአጭሩ የሚመለከተው ወይም ተፈጻሚነቱ :-
- ለዲግሪ ትምህርት ከመግባታቸው በፊት የሙያ ብቃት ማረጋገጫ (COC) ፈተና ሳይወስዱ ዲግሪ የተማሩ እና የተመረቁ።
- የሙያ ብቃት ማረጋገጫ (COC) የወሰዱት ለዲግሪ ትምህርት ከተመዘገቡ በኋላ የሆኑ ተማሪዎች ላይ ነው።

በመደበኛው መንገድ የመግቢያ መስፈርቱን አሟልተው (ለምሳሌ የ12ኛ ክፍል ማለፊያ አምጥተው) የገቡ፣ ወይም ከዲፕሎማ ተነስተው የCOC ፈተና አልፈው ዲግሪ የጫኑ እና የተመረቁ ዜጎችን ይህ መመሪያ አይመለከታቸውም። የትምህርት ማስረጃቸውም ያለ ምንም ተጨማሪ ፈተና እንደ ቀድሞው ይረጋገጥላቸዋል።

መመሪያው በአሁኑ ወቅት በረቂቅ ደረጃ ላይ ያለና እስከ ሐምሌ 13 ቀን 2018 ዓ.ም ድረስ ለህዝብ አስተያየት ክፍት የተደረገ መሆኑ ታውቋል።
1,190005
Photo
የተገጠመለትን ጉሉኮስ ነቅሎ ከሆስፒታል ያመለጠው ታራሚ በቁጥጥር ስር ዋለ

በጂንካ ማረሚያ ተቋም በስርቆት ወንጀል ተከሶ የነበረውና በጤና ችግር ምክንያት ወደ ጂንካ ዞናል ሆስፒታል ለህክምና የገባው ታራሚ ከሆስፒታል ካመለጠ በኋላ በቁጥጥር ስር መዋሉን የጂንካ ማረሚያ ፖሊስ ተቋም አስታወቀ ።

የተቋሙ አዛዥ ምክትል ኮማንደር አስቻለው ነሬሬ ለብስራት ሬዲዮ እንደተናገሩት ታራሚው በስርቆት ወንጀል ተከሶ መደበኛ ቀጠሮውን እየተከታተለ የነበረ ሲሆን በጤና ችግር ምክንያት ለከፍተኛ ህክምና ወደ ጂንካ ዞናል ሆስፒታል ተልኮ ነበር ።

ታራሚው ሆስፒታል በነበረበት ወቅት በህክምና ላይ የተገጠመለትን ጉሉኮስ ነቅሎ ሌሊት 2 ሰዓት አካባቢ ማምለጡ ተገልጿል ።

መረጃ የደረሳቸዉ የማረሚያ ተቋሙ አመራሮች ከአካባቢው የፀጥታ አካላት ጋር በመተባበር ባደረጉት ክትትል ከሌሊቱ 10 ሰዓት ተይዞ  ቁጥጥር ስር ሊውል ችሏል ።

ታራሚው በተከሰሰበትን ወንጀል በመፀፀት ህጉ የሚሰጠውን ውሳኔ ተቀብሎ መታረም ሲገባው ለህክምና በተላከበት ወቅት ማምለጡ በጉዳዩ ላይ በህግ አግባብ ምርመራ ተደርጎ ውሳኔ ይሰጣል ሲሉ ኮማንደር አሰቻለው ነሬሬ ለብስራት ሬዲዮ ተናግረዋል።
1,280002

Showing 30 of 58 posts

Rating

Login required

Frequently Asked Questions

What is the Hulum News ሁሉም ኒውስ Telegram channel about?+

Hulum News ሁሉም ኒውስ (@Hulum_news) is a Telegram channel in the World News category. Official channel of Hulum News Buy ads: For paid promotion DM @algiti

How do I join Hulum News ሁሉም ኒውስ (@Hulum_news) on Telegram?+

Open the channel profile on tgdio, then use the Join / Open in Telegram button to go to @Hulum_news in the Telegram app or web client and subscribe for free.

Is Hulum News ሁሉም ኒውስ a good World News channel to follow?+

On tgdio you can check Hulum News ሁሉም ኒውስ's rating, user reviews, ranking, and latest posts before joining. It currently lists about 22,694 subscribers on tgdio. Compare it with similar World News channels in the same category.

Where can I see Hulum News ሁሉም ኒውስ stats and latest posts?+

On tgdio, open the @Hulum_news channel page for subscriber stats, ranking, ratings, and recent posts. Use the Stats link on the profile for deeper growth and activity charts.