Ministry of Revenues -Medium Taxpayers Branch No2 Telegram channel photo

Ministry of Revenues -Medium Taxpayers Branch No2

@mormto2Public Channel

This is official Telegram Channel of Ministry of Revenues Medium Taxpayers Branch No 2. Join the channel.

18.2k (18,176 subscribers)
Members
—
Rating
43
Total Posts
Sep 16, 2026, 4:21 PM
Updated
Apr 1, 2026
Created
Stats

You are viewing English content. To see content in other languages, change the language of the site.

Channel Information

Channel Information
Channel NameMinistry of Revenues -Medium Taxpayers Branch No2
Username@mormto2
CategoryGovernment Exams
LanguageEnglish
CountryUnited States
Members18,176
Channel TypePublic Channel
CreatedApr 1, 2026
Last UpdatedSep 16, 2026 • 10 days ago
StatusActive

Ranking

Global Ranking
#52989-44
Language Ranking
#11256-7
Category Ranking
#136No change

Participant Growth (Last 21 Days)

Total: 18.2K
24h growth: +88 0%
04/0104/1004/2606/0307/1808/0308/2809/16

Latest Posts

"እናቶች ተረጋግተው እንዲሠሩና ልጆቻቸውን በቅርበት እንዲከታተሉ የማቆያው ሚና ከፍተኛ ነው!" — አቶ ቶሉ ፊጤ
************************
(ጳጉሜ 3 ቀን 2018 ዓ.ም፤ መካከለኛ ግብር ከፋዮች ቅ/ጽ/ቤት)
የመካከለኛ ግብር ከፋዮች ቁጥር 2 ቅርንጫፍ ጽሕፈት ቤት በሕፃናት ማቆያው ውስጥ ሲንከባከባቸው የቆዩትንና አሁን ላይ ቅድመ-መደበኛ ትምህርትን ለሚቀላቀሉ ሕፃናት ሽኝት አደረገ።

በመርሐ ግብሩ ላይ የተገኙት የቅርንጫፍ ጽሕፈት ቤቱ ዋና ሥራ አስኪያጅ አቶ ቶሉ ፊጤ ለሕፃናቱ እና ለወላጆች የእንኳን ደስ አላችሁ መልዕክት አስተላልፈዋል።

በመልዕክታቸውም የሕፃናት ማቆያው እናቶች በሙሉ ትኩረትና እረፍት አግኝተው ሥራቸውን እንዲያከናውኑ ያስቻለ መሆኑን፣ ልጆች የሕይወት ዘመን ስንቃቸውን የሚሰንቁበትና ለነገው ትውልድ መሠረት የሚጣልበት ሥርዓት መሆኑን አብራርተዉ ሕፃናቱን በፍቅር በመንከባከብ ለእናቶች እረፍት የሆኑትን የሴቶችና ወጣቶች ማኅበራዊ ጉዳይ ቡድንን እንዲሁም የሕፃናት ተንከባካቢዎችን አመስግነዋል።

አቶ ቶሉ አክለውም የዚህ መሰል ማቆያዎች ፋይዳ ለእናቶች ብቻ ሳይሆን ለሀገርም ከፍተኛ መሆኑን በማስገንዘብ፣ ወደ ቅድመ-መደበኛ ትምህርት ለተሸጋገሩት ሕፃናት መልካም የትምህርት ዘመን እንዲሆንላቸው ተመኝተዋል።
መርሐ ግብሩ ለሕፃናቱ የተዘጋጁ የማበረታቻ ሽልማቶችን በመስጠት በደመቀ ሁኔታ ተጠናቋል።

ግብር÷ ለሃገር ክብር!

ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ቴሌግራም፦
ፌስቡክ፡- https://web.facebook.com/info.mto2/
ቲክቶክ፡- https://www.tiktok.com/@mto2education
ኢሜል፡- [email protected]
ዩትዩብ፡- https://www.youtube.com/@ministryofRevenues-MTO2
3,310004
📣 ለግብር ከፋዮች በሙሉ፦ ስለ አዲሱ የታክስ አስተዳደር ማሻሻያ አዋጅ (ቁጥር 1434/2018) ማወቅ የሚገቡዎት ዋና ዋና ነጥቦች! 📣
የፌዴራል ታክስ አስተዳደር አዋጅን ለማሻሻል የወጣው አዋጅ ቁጥር 1434/2018 ከሐምሌ 23 ቀን 2018 ዓ.ም (July 30, 2026) ጀምሮ በነጋሪት ጋዜጣ ታትሞ ፀድቋል። አዋጁ የታክስ አሰራሩን ፍትሐዊ፣ ቀልጣፋ እና ዘመናዊ ለማድረግ በርካታ አዳዲስ መብቶችና ግዴታዎችን ይዞ ወጥቷል።
እነዚህን ዋና ዋና ለውጦች በአጭሩ ይወቁ፦
🔹 1. የታክስ አለመግባባትን በስምምነት (Conciliation) የመፍታት መብት
ከታክስ ባለስልጣኑ ጋር አለመግባባት ከተፈጠረ፣ ጉዳዩን በገለልተኛ አካል አመቻችነት በስምምነት/በዕርቅ መጨረስ ይቻላል።
አሰራሩ ሙሉ በሙሉ በፈቃደኝነት እና በሚስጥራዊነት ላይ የተመሰረተ ነው።
ልዩ ዕድል፦ አዋጁ ከመውጣቱ በፊት ይግባኝ ብለው ክርክር ላይ ያሉ ግብር ከፋዮች፣ ጉዳያቸው በዕርቅ እንዲያልቅ አዋጁ ከፀደቀበት ቀን ጀምሮ በ60 ቀናት ውስጥ ማመልከቻ ማቅረብ ይችላሉ።
🔹 2. በሁኔታ ላይ የተመሰረተ የታክስ ምስክር ወረቀት (Conditional Tax Clearance)
የታክስ ዕዳ ያለበት ግብር ከፋይ በቅሬታ/ይግባኝ ሂደት ላይ ከሆነ ወይም የክፍያ ስምምነት (Installment Agreement) ከፈጸመ፣ በሁኔታ ላይ የተመሰረተ ክሊራንስ ማግኘት ይችላል።
ጥቅሙ፦ የንግድ/የሙያ ፈቃድ ለማደስ፣ በጨረታ ለመሳተፍ፣ የተሽከርካሪ/ማሽነሪ ምርመራ ለማድረግ እና የባንክ ብድር ለማግኘት ያገለግላል።
🔹 3. የታክስ ውሳኔ ማስታወቂያ ማስተካከያ እና ይርጋ
ስህተትን ማረም፦ በታክስ ውሳኔ ላይ የሂሳብ/የስሌት ስህተት፣ አዲስ ማስረጃ ወይም የህግ ትርጉም ግድፈት ካለ ባለስልጣኑ ወይም በግብር ከፋዩ ጥያቄ ውሳኔው ሊስተካከል ይችላል።
የይርጋ ጊዜ፦ በመደበኛ ሁኔታ የራስ ታክስ ስሌት ከቀረበበት ወይም ውሳኔ ከተሰጠበት ቀን ጀምሮ የ5 ዓመት የይርጋ ጊዜ አለው። የታክስ ማጭበርበር ከተረጋገጠ ግን የይርጋ ጊዜው ወደ 10 ዓመት ከፍ ይላል።
🔹 4. ደረሰኝ አለመስጠት እና አስተዳደራዊ ቅጣቶች
ደረሰኝ አለመስጠት፦ ደረሰኝ ሳይሰጥ በሚቀርብበት በእያንዳንዱ ግብይት ላይ 100,000 (አንድ መቶ ሺህ) ብር አስተዳደራዊ ቅጣት ይጣላል። ይህ ቅጣት በባለስልጣኑ ሊነሳ አይችልም።
የወንጀል ተጠያቂነት፦ ደረሰኝ አለመስጠት ወደ ወንጀል ክስ የሚቀየረው በአንድ የግብር ዘመን ውስጥ ለሁለት ጊዜያት ያህል አስተዳደራዊ ቅጣት ከተቀጡ በኋላ ድርጊቱ ለ3ኛ ጊዜ ከተፈጸመ ብቻ ነው።
የሃሰት ደረሰኝ/ዋጋ ማሳነስ፦ በአንድ ግብይት ላይ ተመሳሳይ ደረሰኝ ላይ የተለያዩ ዋጋዎችን በመመዝገብ ዋጋ ማሳነስ 100,000 ብር ቅጣት እና ከ5 እስከ 7 ዓመት በሚደርስ ጽኑ እስራት ያስቀጣል።
🔹 5. የድርጅቶች እና የኃላፊዎች ተጠያቂነት
በድርጅት ደረጃ የታክስ ጥሰት ሲፈጸም፣ የድርጅቱ ሥራ አስኪያጅ ወይም የፋይናንስ ኃላፊ ተጠያቂ ይሆናሉ።
ነገር ግን ድርጊቱ ከእውቀታቸው ውጭ መሆኑን፣ ያላዘዙ/ያልተባበሩ መሆኑን ወይም መከላከል የሚያስችል የውስጥ ቁጥጥር ስርዓት የዘረጉ መሆኑን ካስረዱ ነፃ ይሆናሉ።
📍 ተጨማሪ መረጃ፦ የደንበኞች ቻርተርን፣ የኤሌክትሮኒክስ ደረሰኝና የQR ኮድ አጠቃቀም መመሪያዎችን በመከተል የግብር ግዴታዎን በወቅቱ ይወጡ፤ ህጋዊ አሰራርን በመከተል ንግድዎን ያሳድጉ!
6,0600022
Photo
የክፍል ሁለት መመዘኛ ፈተና ተሰጠ
*******************************
 (መካከለኛ ግብር ከፋዮች ቁጥር 2 ቅርንጫፍ ጽ/ቤት)
 የክፍል ሁለት ቀጥተኛ ያልሆኑ ታክሶችን አስመልክቶ የተከታታይ ሞጁላር ስልጠና ላጠናቀቁ የ37ኛ ዙር ሰልጣኞች የመመዘኛ ፈተና ተሰጠ።
ፈተናው ሰልጣኞቹ በተከታታይ በስልጠናው ያገኙትን እውቀትና ክህሎት ለመመዘን የተዘጋጀ ሲሆን፣ ሰልጣኞች ከስልጠናው ምን ያህል ግንዛቤ አግኝተዋል የሚለውን ለመለካት ያለመ ነው።
ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ቴሌግራም፦
ፌስቡክ፡- https://web.facebook.com/info.mto2/
ቲክቶክ፡- https://www.tiktok.com/@mto2education
ኢሜል፡- [email protected]
ዩትዩብ፡- https://www.youtube.com/@ministryofRevenues-MTO2
5,870006
Photo
የኤሌክትሮኒክ ደረሰኝ ሥርዓት ተጠቃሚ ታክስ ከፋይ የሚከተሉት ኃላፊነቶች ይኖሩበታል፤
✅የኤሌክትሮኒክ ደረሰኝ እንዲጠቀም የተፈቀደለት ታክስ ከፋይ ለሚያደርገው ማንኛውም ሽያጭ የተመዘገበ የኤሌክትሮኒክ ደረሰኝ መስጠት አለበት፡፡
✅    የታክስ ባለስልጣኑ በማንኛውም ሰዓት በታክስ ከፋዩ የሽያጭ መመዝገቢያ ሥርዓት ላይ ፍተሻ በሚያከናውንበት ጊዜ ተገቢውን መረጃ የመስጠት፣ የባለስልጣኑ ሠራተኞች ሥርዓቱን እንዲያዩ/እንዲፈትሹ ፈቃድ የመስጠት እና ለሂደቱ ትብብር የማድረግ ግዴታ አለበት፡፡
✅ በግብይት ወቅት ገዥው በደረሰኝ ላይ ማንነቱን የሚገልጽ መረጃ፣ የመታወቂያ ቁጥር ወይም የስልክ ቁጥር እንዲመዘገብለት ከጠየቀ መመዝገብ ግዴታ አለበት፡፡
✅  የተፈቀደው የኤሌክትሮኒክ ደረሰኝ ሥርዓት ከታክስ ባለስልጣኑ የኤሌክትሮኒክ ደረሰኝ ምዝገባ ሥርዓት ጋር መገናኘት በማይችልበት ጊዜ የተደረጉ ግብይቶችን በሙሉ ከኤሌክትሮኒክ ደረሰኝ ምዝገባ ሥርዓት ጋር እንደተገናኘ በ72 ሰዓት ውስጥ መመዝገቡን እና ለገዥው ኤሌክትሮኒክ ደረሰኝ መስጠቱን ማረጋገጥ አለበት፡፡
📌 ጥብቅ ማሳሰቢያ፦ የኤሌክትሮኒክ ደረሰኝ ሥርዓት እንዲጠቀም የተፈቀደለት ታክስ ከፋይ በባለስልጣኑ ያልተፈቀደ ማንኛውንም አይነት የሶፍትዌር ለውጥ እና ማሻሻያ ማድረግ አይችልም፡፡
6,120008
Photo
የኤሌክትሮኒክ ደረሰኝ ሥርዓት አስተዳደር  መመሪያ ቁጥር  1142/2018  በአጭሩ
***********************************

የታክስ አስተዳደራችንን ዘመናዊ፣ ቀልጣፋና ውጤታማ ለማድረግ እንዲሁም የግብር ስወራን ለመከላከል የገቢዎች ሚኒስቴር አዲስ    የኤሌክትሮኒክ ደረሰኝ ሥርዓት አስተዳደር  መመሪያ ቁጥር 1142/2018 (Directive No. 1142/2026)   አውጥቷል።

በመመሪያው የተካተቱ ዋና ዋና ነጥቦች፦

·   ዲጂታል  ደረሰኝ (Electronic Invoice)፦ በየቀኑ የሚደረጉ ግብይቶች በሚኒስቴሩ እውቅና ባገኘ ሶፍትዌር አማካኝነት ዲጂታል ሆነው ይመዘገባሉ። እያንዳንዱ ደረሰኝ ልዩ የደረሰኝ ምዝገባ ቁጥር (IRN) እና ፈጣን መላሽ ኮድ (QR Code) ይኖረዋል።

·   የኢኮሜርስ (e-Commerce) እና የዲጂታል ገበያ ቦታዎች፦ በኦንላይን መድረኮች ላይ የሚከናወኑ ግብይቶችም በተናጠል በሻጩ የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (TIN) ደረሰኝ እንዲቆርጡ ሥርዓት ተዘርግቶላቸዋል።

·  ከቀጥታ ግንኙነት ውጭ (Offline Mode) መሥራት፦ የኢንተርኔት ግንኙነት በሚቋረጥበት ወቅት ግብይት እንዳይስተጓጎል ለተወሰነ ጊዜ ከመስመር ውጭ ሽያጭን መመዝገብና ግንኙነቱ ሲመለስ በቀጥታ ወደ ማዕከላዊ ሲስተሙ መላክ የሚያስችል አማራጭ ተካቷል።

· ጠንካራ የደህንነት ሥርዓት፦ ጥቅም ላይ የሚውሉ የሽያጭ መመዝገቢያ ሶፍትዌሮች ሁሉ ከኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደር  የደህንነት ማረጋገጫ ሰርተፊኬት ማቅረብ ይኖርባቸዋል።

ለአቅራቢዎችና ለአገልግሎት ሰጪዎች  የተቀመጡ ቅድመ-ሁኔታዎች፦

ሙሉውን ለማንበብ ሊንኩን ይጫኑ፡- https://shorturl.at/zxOp9
6,430008
Photo
በገቢዎች ሚኒስቴር የመካከለኛ ግብር ከፋዮች ቁጥር 2 ቅርጫፍ ጽ/ቤት
ግብር÷ ለሀገር ክብር!
ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ቴሌግራም፦
ፌስቡክ፡- https://web.facebook.com/info.mto2/
ቲክቶክ፡- https://www.tiktok.com/@mto2education
ኢሜል፡- [email protected]
ዩትዩብ፡- https://www.youtube.com/@ministryofRevenues-MTO2
አድራሻ፡-  ከሜክሲኮ ወደ ቄራ በሚወስደዉ መንገድ ገነት ሆቴል ፊት ለፊት ካሳ ግራንድ ሞል ላይ እንገኛለን
ስልክ፡- 011-5-58-30-02/011-5-58-44-65
6,750008
Photo
የሞጁለር ስልጠና ተጠናክሮ ቀጥሏል
**************************

(ሰኔ 24 /2018 ዓ.ም፡ መካከለኛ ግብር ከፋዮች ቁጥር2 ቅርንጫፍ ጽ/ቤት)

የክፍል አንድ ስልጠናን በብቃት ላጠናቀቁ የ36ኛ ዙር ሰልጣኞች ቀጥተኛ ያልሆኑ የታክስ አይነቶችን የተመለከተው የክፍል ሁለት ስልጠና እየተሰጠ ይገኛል፡፡

ስልጠናው  በአቶ አወቀ ግዛው የታክስ ከፋዮች ትምህርት ዋና መሪ ባለሙያ የተሰጠ ሲሆን  የተጨማሪ እሴት ታክስ አዋጅን መሰረት አድርጎ የታክሱ ሽፋን፣ ታክሱ የተጣለባቸዉ እቃዎች እና አገልግሎቶች፣ከታክሱ ነጻ የሆኑ አቅርቦቶች፣  ጊዜ እና ዕሴት ፣ የታክሱ ምጣኔዎች ላይ በስፋት ማብራሪያ ተሰጥቷል፡፡

ግብር ከፋዮች የተጨማሪ ዕሴት ታክስ የምዝገባ እና ስረዛ  ስርዓት ፣የስሌት መሰረት፣የታክሱን ተመላሽ እና የማቀናነስ ስርዓት፣የግብዓት  እና የውጤት ታክስ  ተከፋይ ፣የኤሌክትሮኒክስ የታክስ አከፋፈል ስርዓትን በተመለከተ በቂ ግንዛቤ ኖሯቸው ግብራቸውን በወቅቱና በትክክል እንዲከፍሉ  ለማድረግ ታልሞ እየተሰራ ይገኛል፡፡


ግብር÷ ለሀገር ክብር!
ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ቴሌግራም፦
ፌስቡክ፡- https://web.facebook.com/info.mto2/
ቲክቶክ፡- https://www.tiktok.com/@mto2education?r=1&t=ZS-96Owjv8C6Ro
ኢሜል፡- [email protected]
ዩትዩብ፡- https://www.youtube.com/@ministryofRevenues-MTO2
በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
7,850005
File
https://shorturl.at/bKiT4?fbclid=IwZXh0bgNhZW0CMTAAYnJpZBExT1NyeUQwMDh5RHU5Z0lkWXNydGMGYXBwX2lkEDIyMjAzOTE3ODgyMDA4OTIAAR5SmQT6ZfdDR-iL3Svx23pqoV7kBCzD1hO3fDyCuEgiqHDLjRuABfacIMNxUwaem-hdyf_lElIbCdUI-RhdOcQ ደረሰኝ ሥርዓት አስተዳደር መመሪያ ቁጥር 1142/2018

ሰኔ 24/2018 ዓ.ም (የገቢዎች ሚኒስቴር)

የገቢዎች ሚኒስቴር የአሰፈጻሚ አካላትን ሥልጣንና ተግባር ለመወሰን በወጣው አዋጅ ቁጥር 1263/2014 አንቀጽ 19(4)እና በፌደራል ታክስ አሰተዳደር አዋጅ በተሰጠው ስልጣን መሰረት ይንን መመሪያ አውጥቷል፡፡
7,960008
Photo
የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የተሻሻለውን የፌደራል ታክስ አስተዳደር ረቂቅ አዋጅ አፀደቀ

ሰኔ 23/2018 ዓ.ም (የገቢዎች ሚኒስቴር)

አዋጁን ማሻሻል ያስፈለገው የመረጃ ጥራትን ለማሳደግና በመረጃ መሰብስብ ሂደት ውስጥ የሚፈጠሩ ስህተቶችን ለማረም እንዲሁም ለስህተቱ መነሻ የሆኑ ግለሰቦችን በህግ ተጠያቂ እንዲሆኑ ለማስቻል መሆኑን የፕላን በጀትና ፋይናንስ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ሰብሳቢ የተከበሩ አቶ ደሳለኝ ወዳጄ ገልጸዋል፡፡

ታክስ ከፋይ ተቋማት የተወሰነባቸው የታክስ ክፍያ ላይ ቅሬታ ማሰማት ከፈለጉ ቅሬታቸውን በጠቅላይ ሚንስትር ፅ/ቤት ለሚቋቋመው ገለልተኛ የባለሙያዎች ቡድን አቅርበው መፍትሄ እንዲያገኙ ለማድረግ አዋጁን ለማሻሻል ሌላው ምክንያት እንደሆነ ተገልጿል።

አሁን የተሸሻለው ‎አዋጁ አስር ዓመታትን አገልግሎት እየሰጠ መቆየቱን የገለፀው የቋሚ ኮሚቴው ሰብሳቢ የተሸሻለው አዋጁ የፌደራል ታክስ አስተዳደር ስርዓትን ይበልጥ የሚያዘምን ይሆናል ብለዋል፡፡

ምክርቤቱ በረቂቅ አዋጁ መርምሮ በአብላጫ ድምጽ አጽድቆታል፡፡

መረጃው የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ነው
6,670007

Showing 30 of 43 posts

Rating

Login required

Frequently Asked Questions

What is the Ministry of Revenues -Medium Taxpayers Branch No2 Telegram channel about?+

Ministry of Revenues -Medium Taxpayers Branch No2 (@mormto2) is a Telegram channel in the Government Exams category. This is official Telegram Channel of Ministry of Revenues Medium Taxpayers Branch No 2. Join the channel.

How do I join Ministry of Revenues -Medium Taxpayers Branch No2 (@mormto2) on Telegram?+

Open the channel profile on tgdio, then use the Join / Open in Telegram button to go to @mormto2 in the Telegram app or web client and subscribe for free.

Is Ministry of Revenues -Medium Taxpayers Branch No2 a good Government Exams channel to follow?+

On tgdio you can check Ministry of Revenues -Medium Taxpayers Branch No2's rating, user reviews, ranking, and latest posts before joining. It currently lists about 18,176 subscribers on tgdio. Compare it with similar Government Exams channels in the same category.

Where can I see Ministry of Revenues -Medium Taxpayers Branch No2 stats and latest posts?+

On tgdio, open the @mormto2 channel page for subscriber stats, ranking, ratings, and recent posts. Use the Stats link on the profile for deeper growth and activity charts.