
የወልድያ ዩኒቨርሲቲ ተጠባባቂ ፕሬዝዳንት ሆነው የተመደቡት አነጋግረኝ ጋሻው (ዶ/ር) አቀባበል ተደርገላቸዋል።
ወልድያ ዩኒቨርሲቲ አዲስ ፕሬዝዳንት የተመደበለት ተቋሙን ላለፉት ስድስት ዓመታት በፕሬዝዳንትነት ሲያገለግሉ የቆዩት አበበ ግርማ (ዶ/ር) የኃላፊነት ጊዜያቸው መጠናቀቁን ተከትሎ መሆኑ ተገልጿል።
አዲሱ ፕሬዝዳንት የትምህርት ሚኒስቴር የሥራ ኃላፊዎች በተገኙበት የሥራ ርክክብ አድርገዋል፡፡
አዲሱ ፕሬዝዳንት በዩኒቨርሲቲው ባለፉት ዓመታት የተሠሩ እንዲሁም አሁን በግንባታ ላይ የሚገኙ ፕሮጀክቶችን ጎብኝተዋል።
አነጋግረኝ ጋሻው (ዶ/ር) ከዚህ ቀደም የደብረ ታቦር ዩኒቨርሲቲ ፕሬዝዳንት በመሆን ማገልገላቸው ይታወሳል።








