ትምህርት ሚኒስቴር - Education Minstry Telegram channel photo

ትምህርት ሚኒስቴር - Education Minstry

@education_Minstry_ETPublic Channel

#education #education_Minstry #ትምህርት_ሚኒስቴር #ትምህርት Buy ads: https://telega.io/c/education_Minstry_ET

21.8k (21,841 subscribers)
Members
—
Rating
45
Total Posts
Sep 16, 2026, 3:55 PM
Updated
Apr 1, 2026
Created
Stats

You are viewing English content. To see content in other languages, change the language of the site.

Channel Information

Channel Information
Channel Nameትምህርት ሚኒስቴር - Education Minstry
Username@education_Minstry_ET
CategoryCourses & Learning
LanguageEnglish
CountryUnited States
Members21,841
Channel TypePublic Channel
CreatedApr 1, 2026
Last UpdatedSep 16, 2026 • 10 days ago
StatusActive

Ranking

Global Ranking
#30091-35
Language Ranking
#6501-3
Category Ranking
#149+1

Participant Growth (Last 21 Days)

Total: 21.8K
24h growth: +254 1%
04/0104/1004/2605/1306/2808/0308/2809/16

Latest Posts

Photo
📤የሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲዎች የ2019 ዓ.ም ቅበላ የመግቢያ ፈተና ጳጉሜን 04/2018 ዓ.ም ይሰጣል።

በ2019 ዓ.ም በአዳማ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ እና በአዲስ አበባ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ በአፕላይድ ሳይንስ እና በኢንጂነሪንግ የትምህርት ዘርፎች የመግቢያ ፈተና ለመፈተን በኦንላይን የተመዘገባችሁ አመልካቾች የመግቢያ ፈተና ጳጉሜን 04/2018 ዓ.ም እንደሚሰጥ ተገልጿል።

በመሆኑም ያመለከታችሁ በሙሉ በመረጣችሁት የፈተና ጣቢያ በአካል በመቅረብ መፈተን የምትችሉ መሆኑን ዩኒቨርሲቲዎቹ አሳውቀዋል።

ተፈታኞች በዕለቱ ከጠዋቱ 1፡00 ሰዓት በመፈተኛ ጣቢያዎች መገኘት ይጠበቅባችኋል። የሞባይል ስልክ እንዲሁም ማንኛውም ኤሌክትሮኒክስ መሳሪያዎችን ይዞ ወደ ፈተና ጣቢያ መግባት የተከለከለ መሆኑ ተገልጿል፡፡

አመልካቾች ለፈተና ስትቀርቡ የ2018 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ የዩኒቨርሲቲ መግቢያ ፈተና ውጤት፣ የአድሚሽን ካርድ እና የምዝገባ ማረጋገጫ ኮፒ መያዝ ይጠበቅባችኋል፡፡

የመግቢያ ፈተናውን የሚያልፉ አመልካቾች በትምህርት ሚኒስቴር በኩል በሚደረገው የዩኒቨርሲቲ ምደባ ውስጥ አይካተቱም፡፡

💠ትክክለኛ የትምህርት ሚኒስቴር መረጃዎችን ለሌሎች ያጋሩ!
6,9100029
Photo
🔔NGATResult

ነሐሴ 20 እና 21/2018 ዓ.ም የተሰጠው የ2018 ዓ.ም የድኅረ-ምረቃ ፕሮግራሞች የመግቢያ ፈተና (NGAT) ውጤት ተለቋል።

ውጤትዎን ለማየት 👇
https://result.ethernet.edu.et/

ሊንኩን ከተጫኑ በኋላ 'NGAT Results' ላይ 'View Results' የሚለውን በመጫንና Username በማስገባት ውጤትዎን ይመልከቱ።

💠ትክክለኛ የትምህርት ሚኒስቴር መረጃዎችን ለሌሎች ያጋሩ!
6,3200026
Photo
🔈🔈🔈🔈🔈🔈

የዩኒቨርሲቲ እና የትምህርት መስክ ምርጫ ያድርጉ!

በ2018 ዓ.ም የ2ኛ ደረጃ ትምህርት ማጠናቀቂያ ሀገር አቀፍ ፈተና ወስዳችሁ በመደበኛው የትምህርት መርሐግብር የዩኒቨርሲቲ መግቢያ ውጤት ያስመዘገባችሁ ተማሪዎች በሙሉ የዩኒቨርሲቲ እና የትምህርት መስክ ምርጫ እንድታደርጉ ትምህርት ሚኒስቴር አሳውቋል፡፡

የዩኒቨርሲቲ እና የትምህርት መስክ ምርጫ ማድረጊያ ጊዜ 👇
ከነሐሴ 28/2018 ዓ.ም እስከ ጳጉሜን 05/2018 ዓ.ም

የዩኒቨርሲቲ እና የትምህርት መስክ ምርጫ የሚያደርጉበት ሊንክ 👇
https://student.ethernet.edu.et/?fbclid=IwcGRvZgVleHRuA2FlbQIxMABicmlkETFXcUlxZjUzVjNsR3kwdHVvc3J0YwZhcHBfaWQQMjIyMDM5MTc4ODIwMDg5MgABHgt6KhCeBSre-Z_njSCfWG8KDUamucoZHepu9E6x0iN7cjBtzmOUz3VMsQhaemoz919Q0vxdvHuUc6x3P4g

የሕክምና፣ የአካል ጉዳተኝነት፣ ተመሳሳይ ጾታ ያላቸው መንትያዎች እና ከስድስት ወር በታች ህጻን የሚያጠቡ እናቶች አስፈላጊውን ሕጋዊ ማስረጃ ማያያዝ ይኖርባችኋል ተብሏል።

💠ትክክለኛ የትምህርት ሚኒስቴር መረጃዎችን ለሌሎች ያጋሩ!
9,0700037
Photo
አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ በ2019 የትምህርት ዘመን በቅድመ-ምረቃ መደበኛ መርሐግብር (በመንግሥት ስኮላርሺፕ እና በግል ክፍያ) እንዲሁም በማታና ተከታታይ መርሐግብር አዲስ ተማሪዎችን ተቀብሎ ማስተማር ይፈልጋል።

🔔መስፈርቶች

🟢 በ2015፣ 2016፣ 2017 እና 2018 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ መልቀቂያ ፈተና ወስደው የዩኒቨርሲቲ መግቢያ ነጥብ ያመጡ ወይም ደረጃ 4 አጠናቀው (COC) ያለፉ
🟢 በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የሚሰጠውን የመግቢያ ፈተና (UAT) ይወስዳሉ

🖥የምዝገባ ጊዜ 👇
እስከ ነሐሴ 29/2018 ዓ.ም ድረስ

🔔ኦንላይን ይመዝገቡ 👇
https://admission.aau.edu.et/

የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የመግቢያ ፈተና (UAT) ከጳጉሜን 02-04/2018 ዓ.ም ይሰጣል፡፡

💠ትክክለኛ የትምህርት ሚኒስቴር መረጃዎችን ለሌሎች ያጋሩ!
12,3000046
Photo
💠ዛሬ ይፋ ከተደረገው የ2018 ዓ.ም የሪሚዲያል ፕሮግራም ተማሪዎች ውጤት ጋር በተያያዘ ያላችሁን ቅሬታ በ ኦንላይን አስመዝግቡ።

ቅሬታችሁን በኦንላይን አስገቡ 👇
https://result.ethernet.edu.et/

ከውጤታችሁ ስር መጨረሻ ላይ ያለውን Submit Complaint የሚለውን ይጫኑ፣ Select a category የሚለውን ይክፈቱ፣ My result disqualified without reason የሚለውን ይምረጡ፣ አጠር ያለ መግለጫ ይፃፉ፣ የስልክ ቁጥርዎን ይሙሉ እና Submit Complaint የሚለውን በመጫን ቅሬታዎን ያስገቡ።

የሪሚዲያል ፕሮግራም የማለፊያ ነጥብ 250 ለተፈጥሮ ሳይንስ ተማሪዎች (5 የትምህርት አይነቶች) እና 200 ለማኅበራዊ ሳይንስ ተማሪዎች (4 የትምህርት አይነቶች) መሆኑ ታውቋል።

💠ትክክለኛ የትምህርት ሚኒስቴር መረጃዎችን ለሌሎች ያጋሩ!
9,8700042
Photo
ነሐሴ 13/2018 ዓ.ም የተሰጠውን የሙያ ፈቃድ የፅሑፍ ፈተና የወሰዳችሁ የአንስቴዥያ ሙያ ተመዛኞች፣ ውጤታችሁን ከዛሬ ነሐሴ 22/2018 ዓ.ም ጀምሮ መመልከት የምትችሉ መሆኑን ጤና ሚኒስቴር አሳውቋል።

የፅሑፍ ፈተናውን ያለፋችሁ ተመዛኞች የተግባር ፈተና ለመውሰድ ነሐሴ 23 እና 24/2018 ዓ.ም ብቻ ምዝገባ የሚከናወን መሆኑ ተገልጿል።

በመሆኑም በተገለፁት ቀናት https://hple.moh.gov.et/ ላይ በመግባት የብሔራዊ መለያ ቁጥር (FAN) እና Password በማስገባት መፈተኛ ጣቢያ በመምረጥ ምዝገባችሁን እንድታከናውኑ ተብሏል።

ስትመዘገቡ በመረጣችሁት የፈተና ጣቢያ ሲስተሙ የሚሰጣችሁን QR Code የያዘ ስሊፕ ይዛችሁ በፈተናው ወቅት እንድትገኙ ሚኒስቴሩ አሳስቧል፡፡

💠ትክክለኛ የትምህርት ሚኒስቴር መረጃዎችን ለሌሎች ያጋሩ!
12,7000023
Photo
🔈🔈🔈🔈🔈🔈

የ12ኛ ክፍል ፈተና ውጤት ይፋ ሆነ።

የ2018 ዓ/ም የ12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ ፈተና ውጤት ይፋ ተደርጓል። ተፈታኞችም ውጤታቸው ማየት ጀምረዋል።

ውጤት ለማየት ፦
▶️ በድረ ገጽ ፡ https://result.eaes.et/
▶️ ቴሌግራም፡ https://result.eaes.et/telegram
▶️ አጭር የጽሑፍ መልዕክት፡ https://result.eaes.et/sms

በአንድ ጊዜ በርካታ ተማሪዎች ውጤታቸውን ለማየት ስለሚሞክሩ የኔትዎርክ መጨናነቅ ሊያጋጥም ስለሚችል ደጋግሞ መሞከር ይገባል።

የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት ተፈታኞች ቅሬታ ሲኖራቸው በአካል መምጣት ሳያስፈልጋቸው https://result.eaes.et/complaint የሚለውን ማስፈንጠሪያ በመጠቀም ቅሬታቸውን ከነሐሴ 19 እስከ 26/2018 ዓ/ም ከቀኑ 10፡00 ሰዓት ድረስ ማቅረብና ምላሹንም በዛው ማስፈንጠሪያ መከታተል እንደሚችሉ ገልጿል።

💠ትክክለኛ የትምህርት ሚኒስቴር መረጃዎችን ለሌሎች ያጋሩ!
18,50000135
Photo
🚨🚨🔈🚨🚨🚨

" ተማሪዎች ከምሽቱ 1፡00 ሰዓት ጀምረው ውጤታቸው ማየት ይችላሉ " - የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት

የ2018 ትምህርት ዘመን የኢትዮጵያ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ማጠናቀቂያ ፈተና ውጤት የሚገለጽባቸው አድራሻዎች ይፋ ሆነዋል።

በ2018 ትምህርት ዘመን የኢትዮጵያ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ማጠናቀቂያ ፈተና ውጤትን ተፈታኞች  ዛሬ ነሐሴ 19 ቀን 2018 ዓ/ም ከምሽቱ 1፡00 ሰዓት ጀምረው የሚከተሉትን አማራጭ ማስፈንጠሪያዎችን (Link) በመጠቀም ማየት የሚችሉ መሆኑን የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት አሳውቋል።

በተያያዘም ተፈታኞች ቅሬታ ሲኖራቸው በአካል መምጣት ሳያስፈልግ https://result.eaes.et/complaint የሚለውን ማስፈንጠሪያ በመጠቀም ቅሬታቸውን ከነሐሴ 19 እስከ 26/2018 ዓ/ም ከቀኑ 10፡00 ሰዓት ድረስ በማቅረብ ምላሹንም በተመሳሳይ ማስፈንጠሪያ በኩል መከታተል የሚችሉ መሆኑን አገልግሎቱ ገልጿል።

ውጤት የሚገለጽባቸው ማስፈንጠሪያዎች፡-
- በድረ ገጽ ፡ https://result.eaes.et/
- ቴሌግራም፡ https://result.eaes.et/telegram
- አጭር የጽሑፍ መልዕክት፡ https://result.eaes.et/sms

💠ትክክለኛ የትምህርት ሚኒስቴር መረጃዎችን ለሌሎች ያጋሩ!
17,1000072
Photo
የሀገር አቀፍ የድኅረ-ምረቃ ፕሮግራሞች የመግቢያ ፈተና (NGAT) ተመዝጋቢዎች Username፣ Password እና Entrance Ticket አሁን ላይ ማግኘት እንደምትችሉ ተገልጿል።

በመሆኑም ፕሮፋይላችሁ ላይ በመግባት 'Exam Credentials' በሚለው ስር 'Download Entry Ticket' የሚለውን በመጫን ወደ ፈተና ማዕከል መግቢያ ትኬትዎን አውርደው ፕሪንት ያድርጉ።

ፈተናው ከሚጀመርበት ሰዓት 30 ደቂቃ ቀድማችሁ መድረስ ይጠበቅባችኋል።

ሀገር አቀፍ የድኅረ-ምረቃ ፕሮግራሞች የመግቢያ ፈተና (NGAT) ነሐሴ 20 እና 21/2018 ዓ.ም እንደሚሰጥ መገለፁ ይታወቃል፡፡

💠ትክክለኛ የትምህርት ሚኒስቴር መረጃዎችን ለሌሎች ያጋሩ!
13,9000058
Photo
🟢#NGAT_Schedule

የ2018 ዓ.ም መጨረሻ ዓመት ብሔራዊ የድኅረ-ምረቃ ፕሮግራሞች የመግቢያ ፈተና (NGAT) የፈተና መስጫ መርሐግብር፦

ፈተናው በጠዋት እና በከሰዓት ፈረቃ ነሐሴ 20 እና 21/2018 ዓ.ም ይሰጣል።

💠ትክክለኛ የትምህርት ሚኒስቴር መረጃዎችን ለሌሎች ያጋሩ!
15,5000049
#NationalExamResult | የትምህርት ሚኒስትር ብርሃኑ ነጋ (ፕ/ር) የ2018 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና ውጤት ሰኞ ወይም ማክሰኞ ለተማሪዎች ይላካል። አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ፣ እና የሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲዎች ምልመላ እና ቅበላ ካደረጉ በኋላ ሌሎቹም ዩኒቨርሲቲዎች ቶሎ ጥሪ እንዲያደርጉ እየሠራን ነው። መስከረም 05/2019 ዓ.ም ትምህርት ይጀመር የሚለውን ለመጠበቅ እንፈልጋለን።…
7,7700017
Photo
ዘንድሮ በአጠቃላይ ፈተናውን ከወሰዱ ተማሪዎች መካከል ማለፍ የቻሉት 70 ሺ 544 ናቸው።

ካለፉት መካከል በተፈጥሮ ሳይንስ 16.5 በመቶ ሲሆኑ በማህበራዊ ሳይንስ ደግሞ 8.33 በመቶ ናቸው።

💠ትክክለኛ የትምህርት ሚኒስቴር መረጃዎችን ለሌሎች ያጋሩ!
7,3500031
Photo
ዘንድሮ በአጠቃላይ ፈተናውን ከወሰዱ ተማሪዎች መካከል ማለፍ የቻሉት 70 ሺ 544 ናቸው። ካለፉት መካከል በተፈጥሮ ሳይንስ 16.5 በመቶ ሲሆኑ በማህበራዊ ሳይንስ ደግሞ 8.33 በመቶ ናቸው። 💠ትክክለኛ የትምህርት ሚኒስቴር መረጃዎችን ለሌሎች ያጋሩ! @educationMinstryET @educationMinstryET
8,0000018
Photo
ትምህርት ሚኒስቴር የ2018 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና ውጤትን አስመልክቶ ከደቂቃዎች በኋላ መግለጫ ይሰጣል።

💠ትክክለኛ የትምህርት ሚኒስቴር መረጃዎችን ለሌሎች ያጋሩ!
8,2100060
Photo
በዘንድሮ የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና 563 ሺ 960 ተማሪዎች ተመዝግበው 550 ሺ 210 ተማሪዎች ፈተናውን ወስደዋል።

ፈተናውን ከወሰዱት ውስጥ 12.8 በመቶ የሚሆኑት ተማሪዎች 50 በመቶ እና ከዚያ በላይ ማምጣት ችለዋል።

💠ትክክለኛ የትምህርት ሚኒስቴር መረጃዎችን ለሌሎች ያጋሩ!
6,7400017
Photo
አገር አቀፍ የድኅረ-ምረቃ ፕሮግራሞች የመግቢያ ፈተና (NGAT) ነሐሴ 20 እና 21/2018 ዓ.ም ይሰጣል፡፡

ተመዝጋቢዎች Username፣ Password እና Entrance Ticket ለማግኘት የኢሜይል አድራሻችሁን መጎብኘት አትዘንጉ።

💠ትክክለኛ የትምህርት ሚኒስቴር መረጃዎችን ለሌሎች ያጋሩ!
13,0000035
Photo
🔔የጤና ባለሙያዎች የብቃት ምዘና ሁለተኛ ቀን ፈተናዎች በ31 የፈተና ጣቢያዎች በዛሬው ዕለት ሲሰጡ ውለዋል፡፡

ነገ ነሐሴ 15/2018 ዓ.ም የሚሰጠው የነርሲንግ ሙያ ምዘና ጠዋት 3:00 ሰዓት እና ከሰዓት 8:00 ሰዓት የሚጀምር ሲሆን፥ ተመዛኞች ከተገለፀው አንድ ሰዓት ቀድማችሁ በፈተና ጣቢያ መገኘት እንዳለባችሁ ጤና ሚኒስቴር አሳስቧል።

💠ትክክለኛ የትምህርት ሚኒስቴር መረጃዎችን ለሌሎች ያጋሩ!
7,8500018
Photo
▶️#ተራዝሟል

የፌዴራል ልዩ አዳሪ 2ኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች ተማሪዎች የምዝገባ ጊዜ እስከ ነሐሴ 20/2018 ዓ.ም ተራዝሟል።

አንዳንድ ክልሎች ዘግይተው የ8ኛ ክፍል ክልላዊ ፈተና ውጤት በመልቀቃቸውና ያልተመዘገቡ ተማሪዎች በመኖራቸው ምዝገባው መራዘሙን ትምህርት ሚኒስቴር አሳውቋል።

ለመመዝገብ 👇
https://sbs.moe.gov.et/apply

💠ትክክለኛ የትምህርት ሚኒስቴር መረጃዎችን ለሌሎች ያጋሩ!
8,5700012
Photo
ትምህርት ሚኒስቴር በፌዴራል ልዩ አዳሪ 2ኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች የ9ኛ እና የ10ኛ ክፍል ተማሪዎችን ተቀብሎ በነፃ ማስተማር ይፈልጋል።

🔔 ሙሉ የትምህርት ክፍያ ሽፋን እንዲሁም ነፃ የመኝታ እና የምግብ አገልግሎት በነፃ ትምህርት ዕድሉ ይሰጣል፡፡

9ኛ ክፍል ብቻ የሚቀበሉ ልዩ አዳሪ ትምህርት ቤቶች
● አርባ ምንጭ ልዩ አዳሪ ትምህርት ቤት
● ድሬዳዋ ልዩ አዳሪ ትምህርት ቤት
● አሶሳ ልዩ አዳሪ ትምህርት ቤት
● ባህር ዳር ልዩ አዳሪ ትምህርት ቤት

9ኛ እና 10ኛ ክፍል የሚቀበሉ ልዩ አዳሪ ትምህርት ቤቶች
● ቡኢ ልዩ አዳሪ ትምህርት ቤት
● ጅግጅጋ ልዩ አዳሪ ትምህርት ቤት
● ጋምቤላ ልዩ አዳሪ ትምህርት ቤት
● ወሊሶ ልዩ አዳሪ ትምህርት ቤት
● ቦንጋ ልዩ አዳሪ ትምህርት ቤት

ለ9ኛ ክፍል የመመዝገቢያ መስፈርቶች
● በ8ኛ ክፍል ሚኒስትሪ ፈተና 85 እና በላይ አማካኝ ውጤት ያመጣ/ያመጣች
● በሂሳብ እና እንግሊዝኛ የትምህርት ዓይነቶች 80 እና በላይያመጣ/ያመጣች
● ጥሩ ስነ-ምግባር ያለው/ያላት

ለ10ኛ ክፍል የመመዝገቢያ መስፈርቶች
● በ2017 ዓ.ም በ8ኛ ክፍል ሚኒስትሪ ፈተና 70 እና በላይ አማካኝ ውጤት ያመጣ/ያመጣች
● በ9ኛ ክፍል ትራንስክሪፕት 85 እና በላይ አማካኝ ውጤት ያመጣ/ያመጣች
● በሂሳብ እና እንግሊዝኛ የትምህርት ዓይነት 80 እና በላይ ያመጣ/ያመጣች
● ጥሩ ስነ-ምግባር ያለው/ያላት

➡️ኦንላይን ይመዝገቡ 👇
https://sbs.moe.gov.et/apply

➡️የመመዝገቢያ ጊዜ 👇
እስከ ነሐሴ 15/2018 ዓ.ም

ለፈተና የሚቀርቡ ተማሪዎች ዝርዝር እና የፈተና ጊዜ ወደፊት ይገለፃል፡፡ የመግቢያ ፈተናውን የሚያልፉ ተማሪዎች በሚደቡበት ልዩ አዳሪ ትምህርት ቤት ለመማር ፈቃደኛ የሆኑ መሆን አለባቸው ተብሏል፡፡

💠ትክክለኛ የትምህርት ሚኒስቴር መረጃዎችን ለሌሎች ያጋሩ!
13,7000067
Photo
የጤና ባለሙያዎች የብቃት ምዘና ፈተና መርሐግብር

የጤና ባለሙያዎች የብቃት ምዘና ፈተና ከነሐሴ 13-15/2018 ዓ.ም እንደሚሰጥ መገለፁ ይታወቃል፡፡

ነሐሴ 13/2018 ዓ.ም
Medicine, Pharmacy, Anesthesia, Environmental Health, Human Nutrition, Emergency and Critical Care Nursing, Dental Medicine and Optometry.

ነሐሴ 14/2018 ዓ.ም
Medical Laboratory Science, Public Health, Midwifery, Medical Radiology Technology, Pediatric and Child Health Nursing, Psychiatric Nursing, Physiotherapy and Surgical Nursing.

ነሐሴ 15/2018 ዓ.ም - Nursing

ተፈታኞች ነሐሴ 12/2018 ዓ.ም ከሰዓት 8፡00 ሰዓት በመፈተኛ ጣቢያ በመገኘት ስለፈተናው አጠቃላይ ቅድመ ገለጻ (Orientation) መከታተል ይጠበቅባችኋል፡፡

💠ትክክለኛ የትምህርት ሚኒስቴር መረጃዎችን ለሌሎች ያጋሩ!
13,5000053
Photo
✅የ2018 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ ሦስተኛ ዙር የተፈጥሮ ሳይንስ ተማሪዎች የኦንላይን እና የወረቀት ፈተና በዛሬው ዕለት ተጠናቋል።

ሦስተኛው ዙር ፈተና ከረቡዕ ሐምሌ 01/2018 ዓ.ም ጀምሮ ለሦስት ተከታታይ ቀናት ተሰጥቷል።

አራተኛ ዙር ፈተና ከሐምሌ 06-08/2018 ዓ.ም ለሦስት ተከታታይ ቀናት ይሰጣል።

በአራተኛው ዙር ፈተና የማኅበራዊ ሳይንስ ተማሪዎች በወረቀት (PBE) እና በኮምፒውተር (CBE) ፈተናቸውን የሚወስዱ ይሆናል።

💠ትክክለኛ የትምህርት ሚኒስቴር መረጃዎችን ለሌሎች ያጋሩ!
7,1300044
Photo
በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የሚሰጠውን የድኅረ-ምረቃ ፕሮግራሞች የመግቢያ ፈተና (GAT) ለመውሰድ ይመዝገቡ!

የ GAT ማመልከቻ ጊዜ የሚያበቃው👇
ነሐሴ 05/2018 ዓ.ም

➡️ https://portal.aau.edu.et/ ይግቡ።
➡️ 'Online Exams' የሚለውን ይጫኑ።
➡️ Quick Links ከሚለው ስር 'Apply for GAT' የሚለውን ይጫኑ።
➡️ 'Test Taker Registration' የሚለውን ቅፅ ይሙሉ።
➡️ የፓስፖርት መጠን ያለው ፎቶ ያስገቡ።
➡️ 'Submit' የሚለውን ይጫኑ።
➡️ ሲስተሙ የሚሰጥዎን የመለያ ቁጥር ይያዙ።
➡️ ቴሌብር በመጠቀም የምዝገባ ክፍያ ይፈፅሙ።
➡️ አድሚሽን ቲኬትዎን በማውረድ ፕሪንት ብለው፡፡

የ GAT ፈተና በሁለት ዞሮች እንደሚሰጥ የዩኒቨርሲቲው መርሐግብር ያሳያል👇
ከሐምሌ 20-24/2018 ዓ.ም እና ከነሐሴ 07-08/2018 ዓ.ም

💠ትክክለኛ የትምህርት ሚኒስቴር መረጃዎችን ለሌሎች ያጋሩ!
8,4000033
Photo
#AAEB

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ የ2019 ትምህርት ዘመን ዓመታዊ የጊዜ ሰሌዳ ለሁሉም ክ/ከተሞች ትምህርት ጽ/ቤቶች እና በከተማ አስተዳደር ስር ለሚገኙ ሦስት አዳሪ ትምህርት ቤቶች ልኳል።

በዚህም፦
ከሐምሌ 19 እስከ ነሐሴ 22/2018 ዓ.ም
የነባር እና አዲስ ተማሪዎች ምዝገባ ይከናወናል።

ከነሐሴ 26 እስከ ጳጉሜን 5/2018 ዓ.ም
የአዲስ ገቢ የ7ኛ እና የ9ኛ ክፍል ተማሪዎች ምዝገባ ይከናወናል።

መስከረም 05/2019 ዓ.ም
የመጀመሪያ ቀን የመጀመሪያ መደበኛ ትምህርት ክፍለ ጊዜ ይጀመራል።

(የከተማ አስተዳደሩ ትምህርት ቢሮ ለሁሉም ክ/ከተሞች ትምህርት ጽ/ቤቶች እና በከተማ አስተዳደር ስር ለሚገኙ ሦስት አዳሪ ት/ቤቶች የላከው ሙሉ የ2019 ዓ.ም የትምህርት ካሌንደር ከላይ ተያይዟል።)

💠ትክክለኛ የትምህርት ሚኒስቴር መረጃዎችን ለሌሎች ያጋሩ!
7,2900027
Photo
''በትግራይ ክልል በወረቀት ለመፈተን ለተመዘገቡ 15,325 የ12ኛ ክፍል ተፈታኞች ፈተናው ከሐምሌ 22-24/2018 ዓ.ም ይሰጣል።'' የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች

ተፈታኞቹ በተገለፁት ቀናት በመቐለ እና በአክሱም ዩኒቨርሲቲዎች ውስጥ በወረቀት እንደሚፈተኑ አገልግሎቱ ገልጿል።

ተፈታኞች ወደተገለፁት ዩኒቨርሲቲዎች ሐምሌ 20/2018 ዓ.ም በመግባት እና ሐምሌ 21/2018 ዓ.ም ላይ ኦሬንቴሽን በመውሰድ መፈተን የሚችሉ መሆኑን አገልግሎቱ አብራርቷል።

በተያያዘ በትግራይ ክልል በበይነ መረብ ለመፈተን የተመዘገቡ 14,755 ተፈታኞች በስድስቱ ዙር ከሰኔ 23/2018 ዓ.ም ጀምሮ ፈተናው እየተሰጠ መሆኑ ተመልክቷል።

💠ትክክለኛ የትምህርት ሚኒስቴር መረጃዎችን ለሌሎች ያጋሩ!
7,3600025
Photo
✔️ተማሪዎች ውጤታቸውን ማየት ይችላሉ !

በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በ2018 የትምህርት ዘመን 97.48% የሚሆኑ የ6ኛ ክፍል ተማሪዎች 50% እና በላይ በማስመዝገብ ወደ ቀጣዩ የክፍል ደረጃ መዘዋወራቸውን የአዲስ አበባ ከተማ ትምህርት ቢሮ አሳወቀ።

የ2018 የትምህርት ዓመት የ6ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና ውጤት ይፋ ተደርጓል።

ዘንድሮ ፈተናውን ከወሰዱ 84,257 ተማሪዎች መካከል 82,137 የሚሆኑ ተማሪዎች የማለፊያ ነጥብ ሆኖ የተቆረጠውን 50 በመቶ እና በላይ አስመዝግበዋል።

768 ትምህርት ቤቶች ፈተና አስፈትነው 543 ያህሉ ተማሪዎቻቸውን ሙሉ በሙሉ ማሳለፋቸው ተገልጿል።

ተፈታኝ ተማሪዎች ይህን ሊንክ https://aa6.ministry.et/#/result በመጠቀም ከዛሬ ጀምሮ ውጤታቸውን ማየት ይችላሉ።

💠ትክክለኛ የትምህርት ሚኒስቴር መረጃዎችን ለሌሎች ያጋሩ!
7,8500026
Photo
የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ የሁለተኛ ዙር ፈተና እየተሠጠ ነው።

ሰኔ 26/2018 ዓ.ም መሠጠት የጀመረው የሁለተኛ ዙር የኦንላይን ተፈታኝ የተፈጥሮ ሳይንስ ተማሪዎች ፈተና ነገ ይጠናቀቃል።

የሦስተኛ ዙር የተፈጥሮ ሳይንስ ተፈታኞች የወረቀት እና የኦንላይን ፈተና ከረቡዕ ሐምሌ 01/2018 ዓ.ም ጀምሮ ለሦስት ተከታታይ ቀናት ይሰጣል። ተፈታኞች ፈተናውን ወደሚወስዱበት ተቋማት መግባት ጀምረዋል።

💠ትክክለኛ የትምህርት ሚኒስቴር መረጃዎችን ለሌሎች ያጋሩ!
8,3400030
Photo
✅የሙያ ፈቃድ ፈተና ውጤት

በሰኔ 2018 ዓ.ም የተሰጠውን የጤና ሙያ ፈቃድ ፈተና የወሰዳችሁ ተመዛኞች ከነገ ሰኔ 27/2018 ዓ.ም ጀምሮ https://hple.moh.gov.et/ ላይ በመግባትና የብሔራዊ መለያ ቁጥር (FAN) እና Password በማስገባት የፈተና ውጤታችሁን መመልከት የምትችሉ መሆኑን ጤና ሚኒስቴር አሳውቋል።

በውጤታችሁ ላይ ቅሬታ ያላችሁ ተመዛኞች ውጤት ከነገ ሰኔ 27/2018 ዓ.ም ጀምሮ ባሉት 10 ተከታታይ የሥራ ቀናት በአጭር ጥሪ ቁጥር 952 በሥራ ሰዓት በመደወል ሙሉ ስም፣ ዲፓርትመንት እና የተማራችሁበትን የትምህርት ተቋም ስም በማሳወቅ ጥያቄዎቻችሁን ማቅረብ የምትችሉ መሆኑ ተገልጿል።

የጤና ሙያ ፈቃድ ፈተናውን ያለፋችሁ ተመዛኞች ከሰኞ ሐምሌ 06/2018 ዓ.ም ጀምሮ ስም ዝርዝራችሁ ወደ ክልል የሚላክ ስለሆነ፣ የሙያ ፍቃዳችሁን የ12ኛ ክፍል በተማራችሁበት ክልል ማውጣት ትችላላችሁ ተብሏል።

💠ትክክለኛ የትምህርት ሚኒስቴር መረጃዎችን ለሌሎች ያጋሩ!
9,0600029
Photo
🔈🔈🔈🔈🔈🔈🔈

የ6ኛ ክፍል መልቀቂያ ከተማ አቀፍ ፈተና ውጤት ነገ ጠዋት ይፋ እንደሚደረግ የአዲስ አበባ ትምህርት ቢሮ አሳወቀ።

💠ትክክለኛ የትምህርት ሚኒስቴር መረጃዎችን ለሌሎች ያጋሩ!
8,4800030
Photo
🔈🔈🔈🔈🔈🔈

የድሬዳዋ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ የ2018 ዓ.ም የ6ኛ ክፍል ፈተና ውጤት ይፋ አዶርጓል።

በአስተዳደሩ የ6ኛ ክፍል ፈተና የወሰዱ ተማሪዎች (ወላጆች) ከታች በተቀመጠው ሊንክ በመግባት የፈተና መለያ ቁጥራችሁን (Registration Number) በማስገባት ውጤታችሁን መመልከት ትችላላችሁ ተብሏል።

ውጤት ለማየት 👇
https://www.diresrms.org/

💠ትክክለኛ የትምህርት ሚኒስቴር መረጃዎችን ለሌሎች ያጋሩ!
8,0100032
Photo
#MoH

የተግባር ፈተና የምትወስዱ የአንስቴዥያ ሙያ ተመራቂዎች ምዝገባ ከሰኔ 24 እስከ 26/2018 ዓ.ም ብቻ የሚከናወን መሆኑን ጤና ሚኒስቴር አሳውቋል።

ሰኔ 19/2018 ዓ.ም የተሰጠውን የሙያ ፈቃድ ፈተና የወሰዳችሁ የአንስቴዥያ ሙያ ተመዛኞች ከዛሬ ሰኔ 23/2018 ዓ.ም ጀምሮ ውጤታችሁን መመልከት የምትችሉ መሆኑ ተገልጿል።

የጽሁፉ ፈተና ያለፋችሁ የአንስቴዥያ ሙያ ተመዛኞች፥ የተግባር ፈተና ለመውሰድ ከሰኔ 24-26/2018 ዓ.ም ብቻ በኦንላይን https://hple.moh.gov.et/ ላይ በመግባት የብሔራዊ መለያ ቁጥር (FAN) እና Password በማስገባት መፈተኛ ጣቢያ በመምረጥ ምዝገባችሁን እንድታከናውኑ ሚኒስቴሩ አሳስቧል።

ከላይ ከተጠቀሰው የጊዜ ገደብ ውጪ ምንም ዓይነት የምዝገባ ጥያቄ የማያስተናግድ መሆኑን ማኒስቴሩ ገልጿል።

➡️ ከዚህ ቀደም የተግባር ፈተና ተፈትናችሁ ፈተናውን ያላለፋችሁ የአንስቴዥያ ተመዛኞች፥ የተግባር ፈተናውን #በድጋሜ ለመውሰድ የብሔራዊ መለያ ቁጥራችሁን (FAN) ከስማችሁ ጋር ማስተሳሰር ይጠበቅባችኋል።

💠ትክክለኛ የትምህርት ሚኒስቴር መረጃዎችን ለሌሎች ያጋሩ!
10,4000032

Showing 30 of 45 posts

Rating

Login required

Frequently Asked Questions

What is the ትምህርት ሚኒስቴር - Education Minstry Telegram channel about?+

ትምህርት ሚኒስቴር - Education Minstry (@education_Minstry_ET) is a Telegram channel in the Courses & Learning category. #education #education_Minstry #ትምህርት_ሚኒስቴር #ትምህርት Buy ads:

How do I join ትምህርት ሚኒስቴር - Education Minstry (@education_Minstry_ET) on Telegram?+

Open the channel profile on tgdio, then use the Join / Open in Telegram button to go to @education_Minstry_ET in the Telegram app or web client and subscribe for free.

Is ትምህርት ሚኒስቴር - Education Minstry a good Courses & Learning channel to follow?+

On tgdio you can check ትምህርት ሚኒስቴር - Education Minstry's rating, user reviews, ranking, and latest posts before joining. It currently lists about 21,841 subscribers on tgdio. Compare it with similar Courses & Learning channels in the same category.

Where can I see ትምህርት ሚኒስቴር - Education Minstry stats and latest posts?+

On tgdio, open the @education_Minstry_ET channel page for subscriber stats, ranking, ratings, and recent posts. Use the Stats link on the profile for deeper growth and activity charts.