Library ‼️
ደ/ብርሃን ዪኒቨርሲቲ 3 ላይብረሪዎች አሉት እነርሱም፦
1. ተስፋ ገብረ ስላሴ- Main Library ሲሆን በዉስጡ የሁሉንም ዲፓርትመንት መፅሀፍት ፣ የፍፌሽማን ሞጁልና ዲጂታል ላይብረሪ ሲይዝ ከሌሎች ላይብረሪዎች በተለየ የተደራጀ የአይነ ስውራን ብቻ ማንበቢያ ክፍል አለው ። ተስፋ ገ/ስላሴ ላይብረሪ ትልቅና በርካታ ክፋሎች ያሉት በመሆኑ ለንባብ አመቺ ቢሆንም ከሴቶች ዶርም የተወሰነ ርቀት ስላለው ምሽት ላይ ለሴቶች ትንሽ አስቸጋሪ ነው ።
2.ከበደ ሚካኤል- የ Social Library እንደመሆኑ በዋናነት የሶሻል ሳይንስ መፅሀፎችን ፣ የፍሬሽማን ሞጁሎችን እና ዲጂታል ላይብረሪ ይዟል። ነገርግን የማንኛውም ዲፓርትመንት ተማሪ ገብቶ መጠቀም ይችላል ። እንዲሁም ከባለፈው አመት ጀምሮ የህግ ተማሪዎች ላይብረሪ በመሆን እያገለገለ ይገኛል ።
ከግቢው አጠቃላይ አቀማመጥ መሀከል ላይ ስለሚገኝ በብዙ ተማሪዎች ተመራጭ ነው።
3. የሴቶች ላይብረሪ - ለሴት ተማሪዎች ብቻ ከዶርማቸው ቅርበት እንዲኖረው ተደርጎ የተሰራ ነው ። የአብዛኛውን ዲፖርትመት መፅሀፍና የፍሬሽ ኮርስ ሞጁሎችን ይዟል።እንዲሁም በደንብ የተደራጀ ዲጂታል ላይብረሪ አለዉ ።
📌Wifi/ኢንተርኔት -ከ2016ዓ.ም ጀምሮ የተቋረጠ ሲሆን በተደጋጋሚ ቢጠየቅም አጥጋቢ ምላሽ አልሰጠበትም ። ግቢውስጥ እየተሰሩ ካሉ በርካታ ስራዎች ጋር በዚህ አመት ይስተካከላል የሚል ተስፋ አለን ። እስከዛው ግን በሁሉም ላይብረሪዎች ገብታችሁ መጠቀም ትችላላችሁ።
📌ወሃና መብራት - ደ/ብርሃን ዪኒቨርሲቲ በዉሃና መብራት ከሌሎች የሀገራችን ዪኒቨርሲቲዎች በጣም ጥሩ የሚባል ነው ። ውሃ ሁል ጊዜም ይኖራል በጭራሽ አይጠፋም መብራትም እንደዚሁ ቢጠፋ እንኳን በፍጥነት ጀነኔተር ይበራል ።
በአጠቃላይ የውሃና መብራት አገልግሎት የግቢው ትልቁ ጠንካራ ጎኑ ነው ።
@DBUINSIDER@DBUINSIDER