Zad Travel Agency Telegram channel photo

Zad Travel Agency

@ZadTravelAgencyPublic Channel

Zad Travel Agency shares Travel & Tourism updates and media on Telegram. Join to stay updated.

4.1k (4,052 subscribers)
Members
—
Rating
31
Total Posts
Sep 17, 2026, 10:09 PM
Updated
Apr 7, 2026
Created
Stats

You are viewing English content. To see content in other languages, change the language of the site.

Channel Information

Channel Information
Channel NameZad Travel Agency
Username@ZadTravelAgency
CategoryTravel & Tourism
LanguageEnglish
CountryUnited States
Members4,052
Channel TypePublic Channel
CreatedApr 7, 2026
Last UpdatedSep 17, 2026 • 9 days ago
StatusActive

Ranking

Global Ranking
#53667-48
Language Ranking
#11408-6
Category Ranking
#339-2

Participant Growth (Last 13 Days)

Total: 4.1K
24h growth: +42 1%
04/0704/2905/1607/0108/0808/3009/17

Latest Posts

Zad Travel Agency

Sep 08, 2026, 00:16

Voice
ከ15ኛ ዙር የዑምራ ተጓዦቻችን የመዲና ዚያራ የተወሰደ

1⃣▫️2⃣
1,270008
Zad Travel Agency

Sep 08, 2026, 00:16

ልዩ እድል‼

ከመስከረም 07–17 (September 17–27) ዑምራህ ማድረግ ለምትፈልጉ፤ እስከ ነገ ቅሳሜ ማታ ለምትመዘገቡ 138 ሺህ ብር አለላችሁ።




ለመመዝገብ፦ የፓስፖርታችሁን ፎቶ በሚከተሉት አድራሻዎቻችን ላኩልን፦

🎁 ቴሌግራም፦ https://t.me/ZadTravel

🎁 ለመደወል: 0985222666

🎁 ዋትስአፕ፦ 0986111333
28,700008
Zad Travel Agency

Sep 08, 2026, 00:16

Photo
በነ ኡስታዝ አቡ ቁዳማ የተመራው የ14ኛ ዙር ጀማዓችን፤ የመካና መዲና የ10 ቀን ቆይታውን አጠናቆ በሁለቱም አየር መንገድ የሄደው ቡድን በትናንትናው ዕለት በሰላም አዲስ አበባ ገብቷል።

አል-ሐምዱ ሊላህ!


የ15ኛ ዙር ቡድናችን ደግሞ በአላህ ፈቃድ የፊታችን ረቡዕና ሐሙስ ወደ መዲነተል ሙነወራ የሚያቀና ይሆናል።



ከመስከረም 7–17 ላዘጋጀነው የ16ኛ ዙር የዑምራ ፓኬጃችን መመዝገብ የምትፈልጉ፤ ሳይሞላባችሁ ከወዲሁ ቦታ ያዙ።



ከነሐሴ  – መስከረም 03 ያለንን 15ኛ ዙር ፓኬጃችንን አጠናቀን፤ ከመስከረም 07–17 ያለንን ፓኬጃችንን ምዝገባ ስለጀመርን፤ ይህም ሳይሞላባችሁ ከወዲሁ መመዝገብ ትችላላችሁ።



ለመመዝገብ፦ የፓስፖርታችሁን ፎቶ በሚከተሉት አድራሻዎቻችን ላኩልን፦

🔹 ቴሌግራም፦ https://t.me/ZadTravel

🔹 ለመደወል: 0985222666

🔹 ዋትስአፕ፦ 0986111333

🔹 http://ኢሜይል፦[email protected]/
28,4000010
Zad Travel Agency

Sep 08, 2026, 00:16

ምድር ላይ በጣም ከባዱ ነገር ጀርባን ለካዕባ ሰጥቶ መች እንደሚመለሱ ሳያውቁ ወደፊት መራመድ ነው ።

በዚህ ሰዓት  አካላችን ከመካ እየራቀ ይገኛል ግን አውቃለው ብዙዎቻችን ልባችን መካ ላይ ጥለን መጥተናል።

መካን ለቆ መውጣት መድሃኒት የማይፈውሰው ቁስል ይዞ መሄድ ነው።
ይህ ስንብት የአንድ ከተማ ስንብት አይደለም 👉 የምድራችን ቁዱስ እና የተባረከ ምድር ቢሆን እንጂ

አቤት ይሀው መጣው ጌታዬ መጣው እያልን አልነበር ከበራፉ የቆምነው እስኪ ከልባችን አንድ ጊዜ እንድገመው (ለበይክ አለሁመ ለበይክ ለበይክ ላ ሸሪከለክ ለበይክ ኢነል ሃምደ ወኒእመተ ለከወል ሙልክ ላ ሸሪክአለክ) ምክንያቱም መሄጃ መመለሻ ሰዓቱ ደርሷል መራቅን ከእባን ወደ ኃላ ትተን እየሄድን ነው  ብላን እንዴት ይሆን የምንገልፀው??

ስንርቅ ልባችን ሙዕተሚሮች ጋር ጧፍ ሲያረግ ይሰማን ይሆናል ምናልባት?
በዚህ ሰዓት ደረታችን ብንነካ ባዶ ሆኖ የቀረ ይመስላል ሰውነታችን ወደፊት ቢጓዝም  መንፈሳችን ነጭ ልብስ በለበሱት በነዛ ከዓባን ዟሪዎች መሀከል በኮረብታው መሀል አረንጓዴው መብራት ስር እየሮጠ ቀርቷል አቤት ጌታዬ

መካ በቀላሉ አይለቅም
አየሩ ወደ  እስትንፋስ ተቀይሮ ድምፁ ወደ ጆሮ ሲደርስ በአጥንቶች ውስጥ የተቀረጸ መስሎ በማስተጋባት የአዛኑ ድምፅ በትዝታ ውስጥ እንዳለ ይቆያል። የእያንዳንዱ የሰላት ጊዜ ዙሁር ተሰግዶ አስር ተሰግዶ መግሪብ ተሰግዶ ኢሻ ተሰግዶ  ሱብህ ተሰግዶ ትንሽ እንቅልፍ.... አቤት በረካ ድካም ሳይበግረን ያከታተልናቸው አጭር ጊዜያት እንዴት ከውስጥ ይጠፋል?

ሙቀቱ እኮ የሆነ ታአምር ያለው አይመስልም? መጠፋፋቱ የራሱ የሆነ ደስ የሚል ስሜት አለው አቤት ጌታዬ ያንተ ቤት ላይ መጥፋት ደስስስስ ይላል

ከናፍቆት ጋር ስለተደባለቀ እንግዳ የሆነ ሀዘን ታውቃላቹ? ቀን ከቀን ስለሚጨምረው እንዲለቀን  ስለማንፈልገው  ሀዘንስ? 😭😢🥲😭

ትዝታው ከመካ ሶላት በውስጡ ስላደረግነው ዱዓ በእያንዳንዱ የዘምዘም ውሃ  ጠብታ ያስታውሰናል። ሁል ጊዜ መሸም ነጋ በሃረም ላይ የሚፈሰው ብርሃን ተጓዦችን በምሕረት የሚያደምቀውን ዕይታ ያመጣብናል።

ያ ብርሀንና የመመለሻው በሮች እሩቅ ሆነው ሲታዩ ምን ማድረግ ይቻላል?

ጉዞው እንደገና ሊደረግ በማይችልበት ጊዜ ነው ምኞቱ  የሚጠናከረው ያልተለመደ ህመም ተሸክመን በተለመደው ቀናችን ውስጥ ስንጓዝ ✈️🚗🚀🛫🛬

በአላህ ፍቃድ ይሄ መጨረሻችን አይሆንም እየተሄደ አይደል የሚመጣው የመመለሻው  መጀመሪያ እንለዋለን  አዎ የእኛ እግር  በድጋሚ በግቢው ውስጥ ይሄዳል የእኛ አይን አሁንም ካዕባን ይመለከታል  የእኛ ከንፈር  አሁንም በድጋሚ ከተቀደሰው ግንብ ጥላ ስር ይንሾካሾካል ።

ምናልባት ሀዘኑ ቆንጆ የሆነው ለዚህ ነው

ምክንያቱም ያቺ ከተማ  በተወችው ረሃብ ሁሉ ፍቅር አለ። እግር በድጋሚ የተባረከውን መሬት እስክትነካው ድረስ የማይታይ ገመድ ወደ ኋላ ይጎትታል ።

ሳንተኛ ነግቶ ልንተኛ ስንል ዙሁር ደርሶ ለካ እንቅልፍ በተወደደችው ምድር ትንሽ ይበቃል አይ የእንቅልፍ በረካ
ሌላውስ ትውስታ ስንቱ በየክፍሉ ተዋወቀ አይ እስልምና ኒኢማው በረካው 😄😅 😂😅😄
💚💐 ከሁሉም 💐💕💜🌺 ሁሉ ነገር በረካ እና ደስታ የበዛበት ምድር አይ መካ የተባረከች ምድር 💕💙💜

አላህን የምንታዘዝበት የምንገዛበት ለዲናችን ትንሽ ድካም መኖሩ እንዴት ደስታ ይፈጥራል🥰

እስከዚያ ድረስ ያ ደስ የሚለው ሀዘን ድክመት ሳይሆን ዒባዳ ሆኖ ይቀጥላል ።
I love 💕 💕 🕋 🕋 🕋 🕋
ጌታዬ ቤትህን እንደ ቤቴ ልመላለስበት

ጌታዬ ሆይ በምድራችን ትልቁን ሃጅር እና ደረጃ በምታስገኝበት ቤትህ አመላልሰን 🤲🤲🤲🤲🤲🤲
የአንተን ትዛዝ ለመፈፀም እና ውዴታህን ለማግኘት ልባቸው የተነሱትን ሁሉ ወደ ቤትህ ጥራቸው 🤲🤲🤲🤲🤲🤲

🌺💐አላህ የሁላችንም ኢባዳ ይቀበለን 🥰🤲🤲🤲🤲🤲🤲🤲🤲🤲🤲🤲

መልካም ጉዞ ያጀማአ!



©: ከተጓዦቻችን አንዱ ወንድም ዐብዱርረዛቅ የጻፈው።
2,5600022
Zad Travel Agency

Sep 08, 2026, 00:16

ለ15ኛ ዙር የዑምራ ተጓዦች የተዘጋጀ ልዩ የጉዞ ፓኬጅ!

የ15ኛ ዙር ጉዞ ለምትፈልጉ ውድ ደንበኞቻችን፣ ተጨማሪው ባሳችን ከመሙላቱ በፊት ለዛሬ እና ቢበዛ እስከ ነገ የሚቆዩ 7 ክፍት ቦታዎች ብቻ ቀርተውናል!

📅 የጉዞ ቀን፦ ከነሐሴ 28 እስከ መስከረም 03

💰 ልዩ ቅናሽ፦ የ 5,000 ብር ቅናሽ አድርገናል!

እድሉን አሁኑኑ ተጠቀሙበት፤ ለሚያስፈልገው አባል ወይም ወዳጅ ዘመድዎም በማጋራት ያድርሱት።

ለመመዝገብ፦ የፓስፖርትዎን ፎቶ በሚከተሉት አድራሻዎቻችን በፍጥነት ይላኩልን፦

🔹 ቴሌግራም፦ https://t.me/ZadTravel

🔹 ለመደወል: 0985222666

🔹 ዋትስአፕ፦ 0986111333

🔹 ኢሜይል፦ [email protected]
29,200002
Zad Travel Agency

Sep 08, 2026, 00:16

Photo
كل المدن مدن إلا هي المدينة المنورة 🤍
2,430003
Zad Travel Agency

Sep 08, 2026, 00:16

Photo
من هنا..
من #الميقات…
تعقد النيه و تبدأ أجمل حكاية.
و تتجرد القلوب قبل الأجساد، وتُلبس ثياب الإحرام
وتُرفع الأصوات بالتلبية، إيذانًا ببداية رحلةٍ عظيمة نحو بيت الله الحرام.
“لبيك اللهم لبيك،...

رزقتم جمال هذه الأجواء ونداء التلبيه ❤️🤲🕋
اللهم إجعلنا من الوافدين حجاجا ومعتمرين ❤️🕋
2,240007
Zad Travel Agency

Aug 23, 2026, 20:26

Voice
ትናንት ከጂዳ ወደ መዲና ጉዞ
1,680005
Zad Travel Agency

Aug 23, 2026, 20:26

Voice
አሁን የመዲና ዚያራ – ጉዞ ወደ መስጂደ ቁባእ


በኡስታዝ አቡ ቁዳማህ
1,670003
Zad Travel Agency

Aug 23, 2026, 20:26

Photo
በኢትዮጵያ አየር መንገድም፣ በሳዑዲ አየር መንገድም የተጓዙ የ14ኛ ዙር የዑምራ ተጓዦቻችን በሰላም በውቢቷ ከተማ በመዲነተል ሙነወራ ገብተዋል።


አል-ሐምዱ ሊላህ‼
1,7800025
Zad Travel Agency

Aug 23, 2026, 20:26

Photo
سبحان من جعل الراحة النفسية في المدينة المنورة 🤍
2,0200021
Zad Travel Agency

Aug 23, 2026, 20:26

Photo
ጌታዬ ሆይ! ከዱንያና ከሰዎቿ ሁካታና ጫጫታ ርቄ፣ እዚህ (በተቀደሰው ስፍራ) ከአንተ ጋር ብቻዬን በኸልዋ ተደብቄ እንድቀመጥ እመኛለሁ።

ልቤን በአንተ ብቻ፣ በከበረው ቃልህና በነቢዩ ሙሐመድ ﷺ ሱን'ና እንድታረጋጋውና መጽናናትን እንድትለግሰው እማጸንሃለሁ።
ዓይኔና ልቤ በዚያች የተባረከች ምድር ላይ ቋሚ መኖሪያን በማግኘትና እዚያው ማረፊያ (መቃብር) በማግኘት ይረኩ ዘንድ እለምንሃለሁ።"💎


يَا ربّ أن أجلِس هُنا فِي خُلوة معك .. لَا شأن لِي بالدُّنيا وأهلها")

أن تؤنِس قَلبِي بكِ وحدك وبِكلامك وسُنَّة نبينك مُحمَّد ﷺ
أسألُك أن تقرَّ عيني وفُؤادِي بمُستقرٍ ومدفن هناك

#المدينة_المنورة ♥️
2,4300032
Zad Travel Agency

Aug 23, 2026, 20:26

Photo
ከነሐሴ 14–24 ምንም አይነት ምዝገባ አንቀበልም። አጠናቀናል።

ከነሐሴ 28–መስከረም 03 ሁለተኛ ዙር ስለጀመርን፤ ይህም ሳይሞላባችሁ ፈጥናችሁ መመዝገብ ትችላላችሁ።

በተጨማሪም ከመስከረም 07–17 አለን።






💎 የፓኬጅ ዓይነቶችና ዋጋዎች፦

  ▫️ መደበኛ ፓኬጅ (Standard)፦ ሙሉ ፓኬጅ 150,000 ብር ብቻ! (7 ቀን መካ፣ 3 ቀን መዲና - በድምሩ 10 ቀናት)

  ▫️ ቪአይፒ ፓኬጅ (VIP)፦ 177,500 ብር (ተመሳሳይ ሆቴል ሆኖ ለ2 ቤተሰቦች ወይም ለባለ ትዳሮች ለብቻ የተዘጋጀ)

▫️  VVIP፦
220 ሺህ ብር (ለሐረም በጣም ቅርብ የሆኑ ሆቴሎች ለቤተሰብ የተዘጋጀ)

▫️ VVIP Premium፦
285 ሺህ ብር (ለሐረም በጣም ቅርብ የሆኑ ሆቴሎች፣ ለባለ ትዳሮች የተዘጋጀ)

የፓኬጃችን አገልግሎቶች፦

1️⃣  የደርሶ መልስ ትኬት እና ቪዛ

2️⃣  ለሁለቱም ሐረሞች ቅርብና ጥራት ያላቸው ሆቴሎች  (መዲና፦ ዲያረ ጦይባና ዲያረል ሐቢብ ሆቴል / መካ፦ አብራጀ ተይሲር)

Map location: https://zadtravelagency.com/emergency-address

3️⃣ ሙሉ የትራንስፖርት ወጪና የታሪካዊ ቦታዎች ዚያራ (ጉብኝት)

4️⃣ ልምድ ያላቸው አስጎብኚዎችና ከጉዞ በፊት የዑምራ አደራረግ ስልጠና

⚠️ ማሳሰቢያ፦ ባለፈው ዙር እንደተከሰተው ቦታው ከሞላ በኋላ ተጨማሪ ምዝገባ የማናደርግ መሆኑን በታላቅ አክብሮት እናሳስባለን።

📞 ለመመዝገብ እና ለበለጠ መረጃ፦

  - 💬 በቴሌግራም፦ https://t.me/ZadTravel

  - 📱 በዋትስአፕ፦ 0986111333

  - 📞 በስልክ መስመር፦ 0985222666

  - 🌐 የቴሌግራም ቻናላችን፦

  - 🌎 ድረ-ገጽ፦ http://www.zadtravelagency.com/
2,480005
Zad Travel Agency

Aug 23, 2026, 20:26

Photo
ስለ አዲሱ የ1 ዓመት የዑምራ ቪዛ እውነታው‼
=============================
(ከዛድ ቱር & ትራቭል የተሰጠ ማብራሪያ)
||
✍️ እንደሚታወቀው የሳዑዲ ዓረቢያ የሐጅ እና ዑምራ ሚኒስቴር ከሐምሌ 13/2018 E.C. (July 20, 2026) ጀምሮ አዲስ የዑምራ ቪዛ ህግ በይፋ ሥራ ላይ አውሏል። በዚህም መሠረት በ13ኛው ዙር (ከሐምሌ 23 እስከ ነሐሴ 03) የተጓዙ ተጓዦቻችን
ያወረድንላቸው ቪዛ የ1 ዓመት ቪዛ ነበር።

⚠️ ትክክለኛው እውነታ እና ህዝቡ ሊያውቀው የሚገባው ማብራሪያ፦

✅ አንዳንድ ኤጀንሲዎች “እኛ የምንሰጠው የ1 ዓመት ቪዛ ስለሆነ ዋጋው ይጨምራል” ወይም “ልዩ የ1 ዓመት ቪዛ አዘጋጅተናል” በማለት ተጓዦችን ሲያደናግሩ ይስተዋላል።

▫️ እውነታው ግን ይህ ነው፦
ይህ የ1 ዓመት የዑምራ ቪዛ የሳዑዲ መንግሥት በሲስተም ደረጃ ለሁሉም ተጓዦች በይፋ የደነገገው አዲስ አሰራር እንጂ፣ የትኛውም የጉዞ ወኪል (ኤጀንሲ) በራሱ ጥረት የሚያስጀምረው ወይም የሚቀይረው ልዩ ቪዛ አይደለም! በአሁኑ ሰዓት የሚወጡ የዑምራ ቪዛዎች
በሙሉ በሳዑዲ ህግ መሠረት የ1 ዓመት ቪዛ ናቸው። የተለመደውን የ3 ወሩን እናውርድ ቢሉ ራሱ አይችሉም። By default ቫሊዲቲው 1 አመት ነው። ከታች ያያዝነውን የኡስታዝ ሳሊምን የባለፈ ቪዛ ተመልከቱት።

💎 በዚህ ከተስማማን አዲሱ የ1 ዓመት የዑምራ ቪዛ እንዴት ይሠራል? እስከዛሬ የ1 አመት ሲባል ደጋግሞ ለቪዛ ተብሎ ያለ ምንም ተጨማሪ ክፍያ መግባትና መውጣት የሚቻልበት multiple entry ነው ወይንስ የሚለይ ነገር አለው?

እውነታው፦

1️⃣  የቪዛው ቆይታ (Validity)፦ ቪዛው ከተቆረጠበት ቀን ጀምሮ ለ365 ቀናት (ለ1 ሙሉ ዓመት) ያገለግላል።

2️⃣ ተደጋግሞ መግባት (Multiple-Entry)፦
በዓመቱ ውስጥ ወደ ሳዑዲ ዓረቢያ በተደጋጋሚ መግባት እና መውጣት ይቻላል።

3️⃣ የመቆያ ጊዜ (Duration of Stay)፦
በነዚህ 365 ቀናት ውስጥ አጠቃላይ በሳዑዲ የሚያሳልፉት ድምር ጊዜ ከ90 ቀናት (3 ወራት) መብለጥ የለበትም። (ለምሳሌ፦ ለመጀመሪያ ጉዟችሁ 30 ቀን ብትቆዩ፣ በቀሪው የዓመቱ ጊዜያት ውስጥ የቀሩትን 60 ቀናት ተከፋፍለው መጠቀም ትችላላችሁ)። ከፈለጋችሁ በ1 ጉዛችሁ 10 ቀናት ብቻ ከሆነ የምትቆዩት፤ 9 ጊዜ መመላለስ ትችላላችሁ። 9*10= 90።


4️⃣ ነገር ግን ለቀጣይ ጉዞዎች የሚያስፈልጉ ቅድመ ሁኔታዎች፦

➡️ በቪዛው ድጋሚ ለመጓዝ ስትፈልጉ፣ ከመጓዛችሁ በፊት በNusuk (ኑሱክ) ፕላትፎርም (መጀመሪያ ባወጣላችሁ ኤጀንት) በኩል የአገልግሎት ፓኬጅ መግዛት አለባችሁ።

➡️በNusuk መተግበሪያ በኩል የዑምራ ፈቃድ (Permit) ማውጣት ግዴታ ነው።

ይህ እስከዛሬ ከተለመደው የ1 አመት ቪዛ የሚለየው ነጥብ ነው። ይህ የአገልግሎት ፓኬጅ ደግሞ አሁን ላይ ክፍያው 5000 ሪያል አካባቢ ነው። በኢትዮ ሲመነዘር፤ ለ1 ሙሉ ፓኬጅ ከሚከፈለው ይበልጣል። ምናልባት ቀስ በቀስ ሥራው ሲለመደው ሳዑዲዎች ይህን ዋጋ ካላሻሻሉት በስተቀር፤ አሁን ባለው ተጨባጭ የ1 አመት መሆኑ በ1 ጉዞ 3 ወር ሙሉ ለሚቆይ እንጂ ለሚመላለስ ፋይዳ የለውም ማለት ይቻላል።


5️⃣  ይህ ቪዛ በሐጅ ወቅት (ከዙልቂዕዳ 1 እስከ ዙልሒጃ 13) አገልግሎት አይሰጥም፤ ለሐጅ መግቢያነትም አይሆንም።



🔸 እኛ ሁልጊዜም ለደንበኞቻችን ግልጽ፣ ታማኝ እና ከማንኛውም የተሳሳተ ማስታወቂያ (Fake Marketing) የጸዳ አገልግሎት መስጠትን መርሃችን ነው።

የዑምራ ጉዟችሁን በዘመናዊ፣ አስተማማኝ እና ምቹ በሆነ መልኩ ለማካሄድ እና በትክክለኛ መረጃ ላይ የተመሠረተ አገልግሎት ለማግኘት
በራችን ክፍት ነው!


አግኙን፦

📞 ስልክ ቁጥር፦ 0985222666/0986111333

📱 ቴሌግራም/ዋትስአፕ፦ https://t.me/ZadTravel

🌐 http://www.zadtravelagency.com/
🔸 [email protected]
31,6000026
Zad Travel Agency

Aug 23, 2026, 20:26

Video
ብዙ ሰው መዲና ላይ ይህን የቧንቧ ውሃ የዘምዘም ውሃ መስሎት ይጠጣዋል።

ትክክለኛ ዘምዘም ያለባቸው መጠጫዎች በትክክል سقيا زمزم ተብሎ የተጻፈባቸው ናቸው።
2,440008
Zad Travel Agency

May 21, 2026, 05:22

Photo
ምናልባት የረመዿን ዑምራ ፓኬጅ ውድ ሆኖባችሁ ዑምራ ያላደረጋችሁ ካላችሁ፤ ለሐጅ ተብሎ ዑምራ ብቻ ለተወሰኑ ወራት ስለሚዘጋ ከሐጅ በፊት ሸዋል ላይ ዑምራ ለማድረግ ከፈለጋችሁ፤ ሙሉ ፓኬጅ (ቪዛ፣ ሆቴል፣ ደርሶ መልስ ትኬት፣ ትራንስፖርት) በ165 ሺህ ብር አለላችሁ።
0985 222 666 ላይ ደውሉ።

ወይም https://t.me/ZadTravelEthio ላይ አናግሩን።
4,3500010
Zad Travel Agency

May 21, 2026, 05:22

🕋 አምስት ታላላቅ ፀጋዎች የተሰባሰቡባት እጅግ ወርቃማዋ ሰዓት!
ውድ የዛድ ቤተሰቦች... አሁን ያለንበትን ጊዜ እና ቦታ ክብደት እስኪ ቆም ብለን እናስተንትን፡-

①) የቀናት በላጭ በሆነው የጁሙዓ ቀን ላይ ነን!

②) የወራት በላጭ በሆነው በተከበረው የረመዷን ወር ውስጥ ነን!

③) የሌሊቶች በላጭ በሆኑት በ"አሽረል አዋኺር" (የመጨረሻዎቹ አስር ቀናት) ውስጥ ነን!

④) የቦታዎች ሁሉ በላጭ በሆነችው በተከበረችው መካ (መስጂደል ሐረም) ውስጥ እንገኛለን!

⑤) ከዐስር እስከ መግሪብ ደግሞ... ዱዓእ ፈፅሞ ወደ ኋላ የማይመለስባት፣ አላህ የባሮቹን ልመና የሚቀበልባት ልዩ ሰዓት (ሳዓተል ኢስቲጃባህ) ናት!

ይህ ማለት ዱዓችን ተቀባይነት እንዲያገኝ የሚያደርጉ የቦታ፣ የጊዜ እና የሁኔታ ፀጋዎች ሁሉ በአንድ ላይ ተሰብስበውልናል ማለት ነው!

📜 ነብዩ (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) ስለ ጁሙዓ ቀን የዱዓ ሰዓት እንዲህ ብለዋል፡-
«يَوْمُ الْجُمُعَةِ اثْنَتَا عَشْرَةَ سَاعَةً، لَا يُوجَدُ فِيهَا عَبْدٌ مُسْلِمٌ يَسْأَلُ اللَّهَ شَيْئًا إِلَّا آتَاهُ إِيَّاهُ، فَالْتَمِسُوهَا آخِرَ سَاعَةٍ بَعْدَ الْعَصْرِ»
«የጁሙዓ ቀን አስራ ሁለት ሰዓታት አሉት። በውስጡ አንድ ሙስሊም ባሪያ አላህን አንዳች ነገር ጠይቆ የሚሰጠው ቢሆን እንጂ አይገኝም። ስለዚህ ይህችን ሰዓት ከዐስር በኋላ ባለው የመጨረሻው ሰዓት ላይ ፈልጓት።» > (አቡ ዳውድ እና ነሳኢ ዘግበውታል - ሶሒሕ)


ያ ጀመዓህ! ታዲያ ይህችን በየትኛውም የዓለም ክፍል ያሉ ሙስሊሞች የሚመኟትን፣ እኛ ግን አላህ በራህመቱ አምጥቶ መካ ላይ ያስረከበንን ወርቃማ ሰዓት እንዴት እናሳልፋት?
ሐረም በጊዜ በመግባት ጥጋችንን እንያዝ!

ከሰዎች ጋር ከማውራት፣ ስልክ ከመነካካት ርቀን ከጌታችን ጋር ብቻችንን እንሁን!

የልባችንን ስብራት፣ የዱንያም ሆነ የአኺራ ሐጃችንን፣ ለራሳችንም ሆነ ለቤተሰቦቻችን እያነባን አላህን እንለምን!
ይህቺን ወቅት በአግባቡ ጥጋችንን ይዘን፣ ብቻችንን ሐረም ቀድመን ገብተን በዱዓእ ለማሳለፍ ዝግጁ? ☝️

አላህ ዱዓችንን፣ ፆማችንን እና ዑምራችንን ይቀበለን! 🤍

ዱዓው የግድ በዐረብኛ መሆን መስፈርት ባይሆንም፤ የዱዓእ ስብስብ ያለበት ፋይል ካስፈለጋችሁ፦
2,960007
Zad Travel Agency

May 21, 2026, 05:22

Photo
… አንዳንዶች ከመዲና ሲመለሱ በሻንጣቸው የመታሰቢያ እቃዎችን ይዘው ይወጣሉ፤
ሌሎች ደግሞ የቆይታቸውን ትዝታ በፎቶግራፍ አትመው ይመለሳሉ።

ነገር ግን... ብዙዎቹ ተጓዦች እዚያው ጥለውት የሚመጡት ሌላ ውድ ነገር አለ፡-
✔ በመስጂደ ነበዊ ውስጥ ሆነው፣ በእንባ ያንሾካሾኩትን የልብ ዱዓእ...

✔ ከየት መጣ ሳይሉት፣ በድንገት ጉንጫቸውን ያረጠበውን ትኩስ እንባ...

✔ ጊዜው ቢቆም ብለው የተመኙትን፣ ያንን ወደር የለሽ የሰላም እና የፀጥታ ቅፅበት...
እዚያው ጥለውት ይመለሳሉ።
አካልህ መዲናን ይሰናበታል...
ልብህ ግን፣ በምን ተዓምር እንደሆነ ባታውቀውም፣ እዚያው ቀርቶ ታገኘዋለህ።

በዚች ምድር ላይ... አንዳንድ ቦታዎችን ትጎበኝና ታልፋቸዋለህ፤
አንዳንድ ቦታዎች ግን... ለዘላለም በነፍስህ ውስጥ ታትመው፣ አብረውህ ይኖራሉ። 🤍
30,8000029
Zad Travel Agency

May 21, 2026, 05:22

Photo
ከሻንጣቸው (ጓዛቸው) ጋር ለሚመጡ የዑምራ ተጓዦች ጠቃሚ መረጃ‼
============
✔ ትልልቅ ሻንጣዎችን፣ ቦርሳዎችን ወይም የልጆች ጋሪ (ስትሮለር) ይዛችሁ ወደ መስጂደል ሐረም የምትመጡ ከሆነ፣ የፀጥታ አስከባሪዎች (ሴኪዩሪቲ) ይዛችሁ እንድትገቡ አይፈቅዱላችሁም።

ነገር ግን ብዙ ሰዎች የማያውቁት አንድ እውነታ አለ፡
መስጂደል ሐረም ለተጓዦች ነፃ (ያለ ምንም ክፍያ) ዘመናዊ የሻንጣ ማቆያ አገልግሎት ይሰጣል።

📍 የሚገኙባቸው ቦታዎች፡
✅️ ከኪንግ ዐብዱልዐዚዝ በር (በር ቁጥር 1) አጠገብ – ከ WC2 (መፀዳጃ ቤት) ጎን
✅️ ከኪንግ ፋህድ በር (በር ቁጥር 79) አጠገብ
✅️ ከበር ቁጥር 64 ፊት ለፊት (በምዕራቡ አደባባይ)

✅️ ከመካ ቤተ-መፅሐፍት አጠገብ (በምስራቁ አደባባይ)
🧳 የሚፈቀዱ እቃዎች፡
• ትልልቅ ሻንጣዎች
• ትልልቅ ቦርሳዎች
• የልጆች ጋሪዎች (ስትሮለር)

❌ የማይፈቀዱ እቃዎች፡
• ምግቦች
• ትናንሽ የግል እቃዎች
• ውድ የሆኑ ንብረቶች (እንደ ገንዘብ እና ወርቅ ያሉ)
📄 የሚያስፈልጓችሁ መረጃዎች፡
• ፓስፖርት
• የቪዛ ቁጥር

🔐 አሰራሩ እንዴት ነው?
1️⃣ ጓዛችሁን ማቆያው ማዕከል ላይ ታስረክባላችሁ
2️⃣ ሰራተኞቹ እቃዎቻችሁን ይመዘግባሉ
3️⃣ ስማርት የእጅ አምባር (Wristband) ወይም የ QR ኮድ መለያ ይሰጧችኋል
4️⃣ ዑምራችሁን ስትጨርሱ ያንን ኮድ ተጠቅማችሁ ሻንጣችሁን ትረከባላችሁ

🕒 ይህ አገልግሎት 24 ሰዓት ክፍት ሲሆን፣ በተለይ በሚከተሉት ሁኔታዎች በጣም ይጠቅማል፡
• ሆቴል ክፍላችሁን ከመረከባችሁ በፊት መካ ከደረሳችሁ
• ሆቴል ከመሄዳችሁ በፊት መጀመሪያ ዑምራችሁን ማድረግ ከፈለጋችሁ
• መካ በገባችሁበት ቀን ተመልሳችሁ የምትወጡ ከሆነ
ለቀጣይ ጉዟችሁ ይጠቅማችሁ ዘንድ ይህን መረጃ አስቀምጡት (Save አድርጉት)።🤍
3,3600032
Zad Travel Agency

May 21, 2026, 05:22

Photo
Here’s How to Wear Ihram Properly
2,8100017
Zad Travel Agency

May 21, 2026, 05:22

Photo
በርግጥ … ወደ ሀገር ቤት ሲመለሱ ሁሉም ነገር ይናፍቃል...

ለመጀመሪያ ጊዜ መካን ስትረግጣት፣ ሁሉም ነገር ቀላል ሆኖ ላታገኘው ትችላለህ።

√ የሰው ብዛትና ግፊያው ይፈትናል...
√ የአየሩ ሙቀት ይበረታል...
√ እግሮችህ እስኪዝሉ ብዙ ትጓዛለህ።
√ አንዳንዴ አንዲት ሱጁድ ማድረጊያ ጠባብ ቦታ ለማግኘት እንኳ ስንትና ስንት ትታገላለህ።

√ በዚያ ድካምና ፈተና መሃል ሆነው የሚያማርሩ ሰዎችም አይጠፉም።


ነገር ግን... ጉዞህን አጠናቀህ ወደ ቤትህ ስትመለስ፣ አንድ አስገራሚ ነገር ይፈጠራል።
√ መካን በፅኑ መናፈቅ ትጀምራለህ።
√ ያ የሰው ግፊያና መጨናነቅ ሳይቀር ይናፍቅሃል...
√ ያ የአየሩ ሙቀት ሳይቀር ይናፍቅሃል...
√ ወደ መስጂደል ሐረም የምታደርገው ያ ሁሉ ረጅም የእግር ጉዞ በናፍቆት ይመላለስብሃል።

√ ተራዊሕና ተሃጁድ ስትሰግድ አድረህ ደክሞህ ከፈጅር በኋላ ተኝተህ ፖሊሶች መጥተው «ያ ሐጅ! መምኑዕ አንነውም» (መተኛት ክልክል ነው!) እያሉ ገና ዓይንህ ስትገጠም ልታጣጥም ከጀመርከው እንቅልፍ የሚቀሰቅሱህ ክስተት፤ በወቅቱ ቢያበሳጭምህና እስከ እርግማን ቢያደርስህም፣ ቤትህ ስትመለስ ግን ይናፍቅሃል።

√ ወደ ሃገር ቤት በረራህ ነገ መሆኑን ስታውቅ መካን የመሰናበቻ ዋዜማህ ላይ ልብህ ይርዳል። ናፍቆቱ ገና መውጣት ስትጀምር ይጀማምርሃል። «ደግሜ አላህ ፈቅዶልኝ እግሬ ዳግም ይረግጥሽ ይሆን?» የሚል ጥያቄ በውስጥህ ይመላለሳል።…

✔ አካልህን ያደከመችው ያች ከተማ... ልብህን መልሳ በዚህ ልክ ስትስበው ማየት እንዴት ያስገርማል! 🤍

አላህ የተከበሩትን ሐረሞች መልሶና መላልሶ መዘየርን ይወፍቀን፣ መንገዱን ያግራልን።
3,3400028
Zad Travel Agency

May 21, 2026, 05:22

Photo
"ፈረሶች በውድድር ላይ ሳሉ መጨረሻ ሲቀራርቡ ድልን ለማስመዝገብ ከፍተኛ ጥረት ያደርጋሉ።

የረመዿን አቀባበልህ የማያምር ከነበረ፤ አሸኛኘትህን አሳምረው።

ስለዚህ፣ ፈረሶች ከአንተ የበለጠ ብልህ አይሁኑ! ሥራዎች በመጨረሻዎቻቸው ነው የሚገመገሙት።" 
- ኢብን አልጃውዚ
3,6700024
Zad Travel Agency

May 21, 2026, 05:22

Photo
አስቸኳይ ወቅታዊ መረጃ፦ ከኢትዮጵያ አየር መንገድ የተሰጠ መግለጫ

በመካከለኛው ምስራቅ ሀገራት የአየር ክልል መዘጋት ምክንያት፣ የኢትዮጵያ አየር መንገድ ወደ ተለያዩ ከተሞች የሚያደርጋቸውን በረራዎች እስከ ሌላ ማስታወቂያ ድረስ መሰረዙን አስታውቋል።

በረራ የተሰረዘባቸው መዳረሻዎች፦

1. አማን፣
2. ቤይሩት፣
3. ባህሬን፣
4. ቴል አቪቭ፣
5. ዶሃ፣
6. ኩዌት፣
7. ዱባይ፣
8. ሻርጃህ፣
9. አቡ ዳቢ እና
10. ዳማም ናቸው::

* በረራዎች ሲጀምሩ ለሌላ ቀን በነፃ መቀየር (Rebooking)

* ወደ አቅራቢያ መዳረሻዎች በረራን ማዛወር (Rerouting)

* ያልተጠቀሙበትን ትኬት ሙሉ ክፍያ ማስመለስ (Full Refund)

ተጓዦች አላስፈላጊ እንግልት እንዳይገጥማቸው በረራቸውን ከታች ባለው ሊንክ እንዲያረጋግጡ በጥብቅ ይመከራል፦

https: www. ethiopianairlines com/et/book/booking/flight-status

በቀጥታ ከአየር መንገዱ ትኬት የቆረጣችሁ በ reservation@ethiopianairlines. com መጠየቅ የምትችሉ ሲሆን፣ በወኪል (Agent) የቆረጣችሁ ደግሞ ወኪሎቻችሁን እንድታነጋግሩ ተገልጿል።

አየር መንገዱ ለተፈጠረው መስተጓጎል ይቅርታ እየጠየቀ፣ የደህንነት ሁኔታዎችን በቅርበት እየተከታተለ መሆኑን አስታውቋል።

©️Ethiopian Airlines

🌴🌴🌴
4,9400016
Zad Travel Agency

May 21, 2026, 05:22

File
ከቁርኣንና ከሶሒሕ ሐዲሦች የተሰባሰቡ ዱዓዎች ክምችት ነው። ተጠቀሙበት።
3,440009
Zad Travel Agency

May 21, 2026, 05:22

Photo
የስልጠና ጥሪ‼
===========
✍️ ከረመዿን 16–29፣ 19–29፣ 19– ሸዋል 04 በኤጀንሲያችን የተመዘገባችሁ የዛድ ቤተሰቦች በሙሉ፤ ልዩ የዑምራ ስልጠና ከልዩ የኢፍጣር መሰናዶ ጋር የፊታችን ማክሰኞ የካቲት 24, 2018 ከቀኑ 10:00 ጀምሮ በወዳጅነት ፓርክ (ቤተ መንግስቱ አጠገብ – ሸራተን ፊት ለፊት) ስለተዘጋጀላችሁ፤ ሁላችሁም ቀድማችሁ በቦታው እንድትገኙ።

ስልጠናው በሸይኽ ዐብዱ-ስ'ሰላም አንዋር እና ኡስታዝ ሸሃቡድን ሸኑራ ይሰጣል።


አሁንም መመዝገብ ለምትፈልጉ ሁለተኛ ዙር ስለጀመርን ከፈጠናችሁ ትችላላችሁ።

መመዝገብ የምትፈልጉ https://t.me/ZadTravelEthio ወይም በዋትስአፕ 09 85 222 666 አናግሩን።


ከረመዿን፦

➡️ 16–29 ⬅️ 280 ሺህ ብር፣
➡️ 19–29 ⬅️ 270 ሺህ ብር፣
➡️ 19– ሸዋል 04 ⬅️ 275 ሺህ ብር (ይህ ሞልቷል፣ ሁለተኛ ዙር አንጨምርም በዚህ)

የምትፈልጉ መመዝገብ ትችላላችሁ።




ከረመዿን ፓኬጅ ውጭ ሁለት ጁሙዓህ የምታገኙበት ከሸዋል 06–16 ስላዘጋጀን፤ የምትፈልጉ መመዝገብ ትችላላችሁ።
41,6000014

Showing 30 of 31 posts

Rating

Login required

Frequently Asked Questions

What is the Zad Travel Agency Telegram channel about?+

Zad Travel Agency (@ZadTravelAgency) is a Telegram channel in the Travel & Tourism category. Zad Travel Agency shares Travel & Tourism content on Telegram.

How do I join Zad Travel Agency (@ZadTravelAgency) on Telegram?+

Open the channel profile on tgdio, then use the Join / Open in Telegram button to go to @ZadTravelAgency in the Telegram app or web client and subscribe for free.

Is Zad Travel Agency a good Travel & Tourism channel to follow?+

On tgdio you can check Zad Travel Agency's rating, user reviews, ranking, and latest posts before joining. It currently lists about 4,052 subscribers on tgdio. Compare it with similar Travel & Tourism channels in the same category.

Where can I see Zad Travel Agency stats and latest posts?+

On tgdio, open the @ZadTravelAgency channel page for subscriber stats, ranking, ratings, and recent posts. Use the Stats link on the profile for deeper growth and activity charts.