Meweda | Comparison Telegram channel photo

Meweda | Comparison

@MewedaCompPublic Channel

Faith through knowledge [ እምነትን በእውቀት ]

ReligionEnglishUnited States
2k (1,974 subscribers)
Members
—
Rating
22
Total Posts
Sep 20, 2026, 11:37 PM
Updated
May 14, 2026
Created
Stats

You are viewing English content. To see content in other languages, change the language of the site.

Channel Information

Channel Information
Channel NameMeweda | Comparison
Username@MewedaComp
CategoryReligion
LanguageEnglish
CountryUnited States
Members1,974
Channel TypePublic Channel
CreatedMay 14, 2026
Last UpdatedSep 20, 2026 • 5 days ago
StatusActive

Ranking

Global Ranking
#9932+2
Language Ranking
#2082-1
Category Ranking
#142No change

Participant Growth (Last 7 Days)

Total: 2.0K
24h growth: +11 1%
05/1407/1107/1108/2309/0209/1109/20

Latest Posts

Meweda | Comparison

Sep 02, 2026, 16:32

አሰላሙአለይኩም ወራህመቱላሂ ወበረካቱ

እህት ወንድሞች አንድ ነገር ላስቸግራቹ ነው

ለአላህ ብላቹ ተባበሩኝ

አንዲት እህት ስደት ከመጣች ሁለት አመት ሆኗታል ግን በጣም እሚያሳዝነው አሰሪዋ ጠንቋይ ናትና ልጅታን ምንም ነገር እንዳታቅ አድርጋ አፍዝዛታለች እናም ይችህ እህት አላህ ዳኚ ሲላት ዝምብላ ከቤቱ ትወጣለች ከዛም ሲደክማት መንገድ ላይ ቁጭ ትላለች ከዛም አንድ ሱዳናዊ ግለሰብ ያያታል ሲያያት ግን ልጅቷ ላይ ችግር እንዳለ ይረዳና ጠጋ ብሎ ሲጠይቃት ተስፋን የሚያስቆርጡ ንግግሮችን  ትመልስለታለች እሱም ችግር እንዳለ ይረዳና ያለውን ገንዘብ ሰጣትና ሪያድ ኢንባሲ ብላ እንድትሳፈር ተባበራት ከዛም ይችህ እህት ወደ ኢንባሲው ከገባች ቦሀላ ፈዛ ቁጭ ባለችበት አንድ ሀበሻዊ ያገኛታል ከዛም  እነደመጀመሪያው ገለሰብ  ሲጠይቃት ተመሳሳይ መልስ መለሰችለት እና ይችህ እህት ስትጠየቅ ምታቀው ወላሂ ስሟንና የአባቷን ስም ብቻ ነው ምታቀው 2ት አመት ቤተሰብን ሳታወራ ቆይታለች ቤተሰቦቿ ይኑሩ አይኑሩ አንድ ምታቀው ነገር የለም የት እንደነበረችኳን ስንጠይቃት ምታስታውሰው ነገር የለም  እና አስብት እናት የልጇን ድምፅ ሀለት አመት  ሳትሰማ ሞታለች ብላ ቁርጧን አላውቀች ሁሌ ልባ እንደተጠለጠለ  ወላሂ ይከብዳል ልጅቱም እናት አባትን የወንድም እህቶቿን ድምፅ ሳትሰማ  ጭራሽ ስማቸውን እስከመርሳት ድርስ እና ውንድምና እህቶች ሼር በማድረግ ተባበሩኝ በዝች ልጅ ቦታ እራሳችንን አስቀምጠን እናስብ
የልጅቷ ስም ሙኒራ አብደላህ ትባላለች

የትወልድ ባታ ጉንችሬ  ልዩ ስሙ ኡፍጠሬ ሚባል ቦታ ነው ብላናለች ባረከላሁፊኩም ተባበሩን ወላጆች ልጆቻቹን እያሰባቹ ወደዃላ አትበሉብን 

ያገኘ ካለ በዚህ ስልክ ተባበሩን 0550745238


የቻናል ባለቤቶች ተባበሩን
1,6500020
Meweda | Comparison

Sep 02, 2026, 16:32

በሴት ልጅ አዕምሮና ምስክርነት ዙሪያ የሚነሱ ትችቶች

በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩህሩህ በጣም አዛኝ በሆነው

🟠የሐዲስን ትክክለኛ ዐውድ ባለመረዳት ከሚሰነዘሩ የተሳሳቱ  ትችቶች ውስጥ ሴት ልጅ የአዕምሮ ጎዶሎ ናት የሚለው ትችት ነው ።  በእስልምና አስተምህሮ ውስጥ "ናቂሳቱ ዐቅል" ሲባል የሚያመለክተው አጠቃላይ የማሰብ ችሎታን ሳይሆን፣  በተፈጥሮ ሂደት ውስጥ ሊከሰት የሚችልን  "የማስታወስ አቅም ድክመት" ነው። ይህም በንግድ ዕዳና  መሰል ወንዶች ሚዘወትሩባቸው ምስክርነቶች  ውስጥ ሊከሰት የሚችለውን የመርሳት እድል ሁለት ሴቶች በማድረግ  ለመከላከል እና ፍትህ እንዳይዛባ የተዘጋጀ የህግ ጥበቃ (Legal safeguard) ነው።

" የሴት ምስክርነት እንደ ግማሽ የወንድ ምስክርነት አይደለምን?’ እኛም ‘አዎን’ አልን። እሳቸውም ‘ይህ የሴት የአእምሮዋ  ጉድለት በመሆኑ ነው’ አሉ።"

📗Sahih al-Bukhari, 2658 

፨ ይህም ምስክርነት የሚገኘው  ሱረቱል በቀራ ሲሆን " አንዲቱ ብትረሳ አንደኛዋ ታስታውሳት ዘንድ ስለሚል የአዕምሮ ጉድለት የሚለው መርሳትን እንደሚወክል መረዳት ይቻላል ።

" ..فَرَجُلٌ وَامْرَأَتَانِ مِمَّن تَرْضَوْنَ مِنَ الشُّهَدَاءِ أَن تَضِلَّ إِحْدَاهُمَا فَتُذَكِّرَ إِحْدَاهُمَا الْأُخْرَىٰ ۚ ..."

​«...ከምስክሮችም የሆኑ አንድ ወንድ እና ሁለት ሴቶች ይሁኑ፤ (ይህም) አንዲቱ ብትረሳ ሌላይቱ ታስታውሳት ዘንድ ነው።»

📗ሱረቱል በቀራ 282

፨ ኢማም አል-ነወዊይ በሰሂህ ሙስሊም ሸርህ ላይ በግልጽ እንዳስቀመጡት፣ ይህ ጉድለት የሚባለው "የመያዝ/የማስታወስ ችሎታ" ጋር የተያያዘ ነው።

قوله : «أما نقصان العقل فشهادة امرأتين تعدل شهادة رجل تنبيه منه على ما وراءه وهو ما نبه الله تعالى عليه في كتابه بقوله تعالى : أن تضل إحداهما فتذكر إحداهما الأخرى أي إنهن قليلات الضبط،

"በአእምሮ መጉደልን በተመለከተ፡ የሁለት ሴቶች ምስክርነት የአንድ ወንድ ምስክርነት ጋር እኩል መሆኑ፣ ከዚህ በስተጀርባ ላለው ነገር ማስታወሻ ነው። ይህም አላህ በቅዱስ ቁርኣኑ ‘ከሁለቱ አንዷ ብትረሳ ሌላኛዋ እንድታስታውሳት’ ብሎ የገለጸው ነው። ይህም ማለት ሴቶች የማስታወስ (የመያዝ) አቅማቸው ደካማ ነው ማለት ነው።"

📗صحيح مسلم بشرح النووي، المجلد الأول، ص 59

፨ ዘመናዊ የሳይንስ ጥናቶች እንዳረጋገጡት፣ እርግዝናና መሰል ነገራቶች በሴቶች አእምሮ ላይ ተፅዕኖ ያሳድራል። ​በተለይ በሦስተኛው የእርግዝና ወር የመስማት #ማስታወስ ችሎታ፣ ትኩረት እና የአፈጻጸም ተግባራት ላይ መጠነኛ መዳከም ሊከሰት እንደሚችል ጥናቶች ያሳያሉ።

The results of this study revealed that the occurrence of mild impairment of auditory memory, attention and executive functions in the third trimester of pregnancy is consistent with the main hypothesis.

የዚህ ጥናት ውጤት እንደሚያሳየው፣ በእርግዝና ሦስተኛው ሶስት ወር ውስጥ የመስማት ችሎታ (auditory memory)፣ ትኩረት እና የአፈጻጸም ተግባራት (executive functions) መጠነኛ መዳከም መከሰቱ ከዋናው ግምት ጋር የሚጣጣም ነው።

📗Ali, S. A., Begum, T., Reza, F., Wan Rosilawati, W. R., & Wan Nor Azlen, W. M. (n.d.). Auditory Cognitive Function Assessment During Pregnancy: An Event-Related Potential and Neuropsychological Study. Chapter 6: Conclusion.

፨ ከንግድና መሰል ጉዳዮች ጋር የተያያዙ ምስክርነቶች ላይ ሴት 2 መሆኗ የተፈለገበት ምክንያት ሴት ልጅ ከንግድና መሰል ነገራቶች የራቀች በመሆኗ ቅድም ያነሳነው  የመርሳት ችግር ሊጎላ ስለሚችል ነው ።

፨ኢማም ኢብኑ ከሲር በታላቁ ተፍሲራቸው ላይ እንደገለጹት፤ 'ሴቶች ሁለት መሆን ያለባቸው በገንዘብ ነክ ንግድና መሰል ጉዳዮች እንደሆነ አስፍረዋል ።

فإن لم يكونا رجلين فرجل وامرأتان، وهذا إنما يكون في الأموال وما يقصد به المال»

"ወንዶች ሁለት ካልሆኑ (በምስክርነት ጊዜ)፣ አንድ ወንድ እና ሁለት ሴቶች ይሁኑ፤ ይህም የሚሆነው በገንዘብ ነክ ጉዳዮች እና ገንዘብን በሚመለከቱ ጉዳዮች ላይ ብቻ ነው"።

📗تفسير القرآن العظيم» للحافظ عماد الدين إسماعيل بن عمر بن كثير  سورة البقرة 282

፨የሴቶች ምስክርነት በሁለት መተካቱ አጠቃላይ አእምሯዊ አቅምን የሚለካ ሳይሆን፣ ከገንዘብ እና ከንግድ ውሎች ጋር በተያያዘ ሴቶች በብዛት ከነዚህ ነገራቶች የራቁ በመሆናቸው  ሊፈጠር የሚችለውን የመርሳት ክፍተት ለመቅረፍ የተቀመጠ ጥንቃቄ የተሞላበት ድንጋጌ ነው።   ከዚህ ውጭ ባሉ ጉዳዮች ማለትም በጡት ማጥባት፣ በሴቶች ተፈጥሮአዊ ክስተቶች እና በሌሎችም የቤት ውስጥ እውነታዎች ሴት ብቻዋን የምትሰጠው ምስክርነት ሙሉ በሙሉ ተቀባይነት እንዳለው 📗ሰሒሕ አል-ቡኻሪ (2659)ን ጨምሮ ሌሎች ማስረጃዎች ያረጋግጣሉ።

©
2,1400029
Meweda | Comparison

Sep 02, 2026, 16:32

🟠ለሹብሃዎች በቂ ምላሽ በመስጠት የምናውቀው የወንድም ሁሴን ኸድር ቻናል በጣም ወሳኝ ከምላቸው ቻናሎች ውስጥ ነው ተቀላቀሉ  👇

https://t.me/iwnetlehullu1
1,8800016
Meweda | Comparison

Sep 02, 2026, 16:32

🟠ከዚህ በፊት ባየናቸው ፅሁፎች በክርስትና ሴት ልጅ በግልፅ የአዕምሮ ጎዶሎ እንዲሁም የማመዛዘን ችግር ጭምር ያለባት እንደሆነችና በዚህም ምክንያት መመስከር መፍረድ ወጥታ መማርም ሆነ ማስተማር ወዘተ .... እንደማትችል አይተናል ። እስኪ ዛሬ እስልምና ላይ በዚህ ዙሪያ ለሚያነሱት ውሃ የማያነሳ ሙግት መልስ እንስጥ ...
1,5000017
Meweda | Comparison

Sep 02, 2026, 16:32

Photo
ጉድ! ክርስቲያኖች እያበዱ ነው። 🤭
1,4700043
Meweda | Comparison

Sep 02, 2026, 16:32

Video
🟠ለዲያቆን ከጓደኞቹ የተሰጠው አስተያየት :)
2,3500083
Meweda | Comparison

Aug 31, 2026, 09:00

🟠ቁርዐን ጥያቄ ማይነሳበት መሆኑን አስመስክረናል አላሁ አክበር ⚡️⚡️
1,9100042
Meweda | Comparison

May 24, 2026, 07:00

Photo
ኒቃብና የኦርቶዶክስ ተዋሕዶ አስተምህሮ

▪️በአክሱም እና በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ በሙስሊም ተማሪዎች አለባበስ ላይ እየተወሰደባቸው ያለው የክልከላ እርምጃ ፣ ስለራሳቸው እምነት ካላቸው የግንዛቤ ማነስና ኢስላም ጠልነት የመነጨ እንጂ ኦርቶዶክስም ሆነ አጠቃላይ የክርስትና አስተምህሮ ሴት ልጅ ፊቷን ጭምር መከናነብ እንዳለባት ነው ሚደነግጉት ።

፴፪. ነገር ግን ላመኑ ሴቶች ራሳቸውን በንጽሕና ሊከናነቡ ይገባል፤ የፊታቸውን ውበት በማሳመርና ቀለም በመቀባት አይደለም፤ እግዚአብሔር በፈጠረው መልክ ውስጥ ጥቅም በሌለው ኵል መኳልና ማጌጥም አይደለም እንዲህ ያለውንም ሁሉ አይሥሩ፤ ነገር ግን እነርሱ ተከናንበው በጎዳና ራሳቸውን ዝቅ አድርገው ይሂዱ፤ ምእመናት ሆይ! ራሳች ሁን ጠብቁ፤ ከማንም ጋር አትነጋገሩ ፤ ይልቁንም ከባሎቻችሁ ጋር ጥላቻን አትነጋገሩ፡፡
📚 መፅሐፈ ዲድስቅሊያ አንቀጽ ፫፣ ቁጥር ፴፪ (32)

©
9670089
Meweda | Comparison

May 24, 2026, 07:00

Photo
🎯አሰላሙ አለይኩም
እንደምታውቁት ፎቶ ላይ ያለው ሰውዬ ከአንዴም ሁለቴ የውይይት ጥሪ በኛም በወገኖችም ቀርቦለት ሊመጣ አልቻለም ነበር
❕1 million follower አለ ያው 1M ልንገባ ነው ስለዚህ ለመጨረሻ ጊዜ የውይይት ጥሪ የምናቀርብለት ይሆናል ፍርሀቱ ለቆት ከመጣ ኸይር ካልሆነ ግን ለአንዴ እና ለመጨረሻ ጊዜ የምናሰናብተው ይሆናል : :
🔔በዚህም መሰረት በ ግንቦት 10 ማለትም የፊታችን ረብዕ ከምሽቱ 3:00 ሰአት ውይይት የሚኖረን ይሆናል
98200112
Meweda | Comparison

May 24, 2026, 07:00

የሴት ልጅ አዕምሮ ጉድለት በክርስትና

▪️የክርስትና አስተምህሮ  የሴት ልጅ የተፈጥሮ ብቃት፤ የማስተዋል አቅም እና ለማህበራዊም ሆነ ለሃይማኖታዊ ሀላፊነቶች ያላትን ቦታ አስመልክቶ የአዕምሮ ጉድለት ያለባት በመሆኗ  ከምክንያታዊነት ይልቅ በስሜታዊነት የምትመራ እና ጥልቅ የሆኑ ማህበራዊም ሆነ ትምህርታዊ ሚናዎችን ለመወጣት የተፈጥሮ ውስንነት ያለባት አድርጎ ይፈርጃታል ።

📗መጽሐፈ ቀሌምንጦስ 2፡14
••••••••••
" ሴት በተፈጥሮዋ ደካማ ናት የሰማችውን ሁሉ ምንም ሳታመዛዝን አሜን ብላ ትቀበላለች ።

📗1ኛ የጴጥሮስ መልእክት 3:7
••••••••••
⁷ ባሎች ሆይ.... ደካሞች ስለሆኑና የሕይወትንም በረከት አብረዋችሁ ስለሚወርሱ አክብሯቸው።

፨ ጥንታዊ የቤተክርስቲያን አባቶች እነዚህን ጥቅሶች መሰረት በማድረግ የሴት ልጅ የአዕምሮ ብቃት ደካማነት ወይም ዝቅተኛነትን በጽሑፎቻቸው በግልፅ ሲያንፀባርቁ ይስተዋላል።

"ሴቶች ባሎቻቸውን፣ልጆች ደግሞ ወላጆቻቸውን ማገልገላቸው በሰዎች መካከል ያለ የተፈጥሮ ሥርዓት ነው ፤ ምክንያቱም የዚህ ፍትሃዊነት መሰረት ታናሽ (ደካማው) ታላቁን (ጠንካራውን) ያገለግላል 'በሚለው መርህ ላይ ያረፈ ነው።.... ደካማው አዕምሮ ጠንካራውን ማገልገሉ ተፈጥሮአዊ ፍትህ ነው።"

“It is the natural order among people that women serve their husbands and children their parents, because the justice of this lies in (the principle that the best serves the greater...
This is the natural justice that the weaker brain serve the stronger."

📗[ St. Augustine, Questions on the Heptateuch, Book 1, § 153]

፨ይህንን አዕምሮአዊ ድክመት መነሻ በማድረግ መፅሐፍ ቅዱስ ሴት ልጅ በማስተማር ተግባር ላይ እንዳትሰማራና የመማር ፍላጎት ቢኖራት እንኳን በቤት ውስጥ የቧሏን እገዛ እንድትጠይቅ ያዛታል።

📗 "1ኛ ወደ ጢሞቴዎስ 2:12
••••••••••
¹² ሴት ዝም እንድትል እንጂ እንድታስተምር ወይም በወንድ ላይ ሥልጣን እንዲኖራት አልፈቅድም፤

📗1ኛ ወደ ቆሮንቶስ ሰዎች 14:35
••••••••••
³⁵ ሴቶች ለማወቅ የሚፈልጉት አንዳንድ ነገር ካለ፣ ባሎቻቸውን በቤት ይጠይቁ፤

፨ ጥንታዊ የቤተክርስቲያን አባት የሆነው Epiphanius ይሄንን መሰረት በማረግ እንዲህ ይለናል

" በአጠቃላይ ስለሴቶች ያለው አመለካከት ፤ ማንኛውም ነገር ቢሆን፣ ቢያንስ በይፋዊ መድረክ ላይ ለማስተማር የሚያስችል የአዕምሮም ሆነ የስሜት ብቃት እንደሌላቸው የሚገልፅ ነው ።"

his view of women in general as not intellectually or emotionally qualified to teach (didaskein) any-thing at all, at least publicly."

📗[Epiphanius Women in Early christianity p .81]

፨ባጠቃላይ መፅሐፍ ቅዱስም ሆነ ጥንታዊ ቤተክርስቲያን አባቶች  የሴቶች የአዕምሮ ብቃት ውስንነትን (ጉድለትን )በመግለፅ  ሴቶች ከተለያዩ የማስተማርና ማህበራዊ ሃላፊነቶች መገለል እንዳለባቸው ይገልፃሉ።

©
3,07000106
Meweda | Comparison

May 24, 2026, 07:00

ጊዜያዊ ጋብቻ በክርስትና

▪️በክርስትና እምነት ተከታዮች ዘንድ ቅዱስ ብለው ከሚጠሩት ባይብል ይልቅ ለሰባኪያን ትርክት ቅድሚያ የመስጠት ዝንባሌ ይስተዋላል ፤ ይህም 'ብቸኛው የጋብቻ አይነት አንድ ለአንድ ብቻ ነው ' የሚል ድምዳሜ ላይ አድርሷቸዋል ። ይሁን እንጂ ባይብልን በስፋት ስንመረምር መለኮታዊ ፍቃድ የተቸራቸውን የተለያዩ የጋብቻ አይነቶችን እናገኛለን ። ከነዚህ መለኮታዊ  ፍቃድ ከተቸራቸው ጋብቻዎች ውስጥ ወታደሮች ስሜታዊ ፍላጎታቸውን ለመቆጣጠር ሲሉ በጊዜያዊነት እንዲፈፅሙ የተፈቀደላቸው የጋብቻ ስርዐት ነው ።


ኦሪት ዘዳግም 21:10-14
••••••••••
{¹⁰ ከጠላቶችህ ጋር ጦርነት ልትገጥም ወጥተህ አምላክህ እግዚአብሔር (ኤሎሂም ያህዌ) እነርሱን በእጅህ አሳልፎ ሰጥቶህ በማረክህ ጊዜ፣
¹¹ ከምርኮኞቹ መካከል መልከ መልካም ሴት አይተህ ብትማርክህ፣ ሚስትህ ልታደርጋት ትችላለህ።
¹² ወደ ቤትህ ውሰዳት፤ ጠጕሯን ትላጭ፤ ጥፍሯንም ትቍረጥ።
¹³ ስትማረክ የለበሰችውንም ልብስ ታውልቅ፤ እቤትህ ተቀምጣ ለአባትና ለእናቷ ወር ሙሉ ካለቀሰችላቸው በኋላ፣ ልትደርስባትና ባል ልትሆናት፣ እርሷም ሚስት ልትሆንህ ትችላለች።
¹⁴ በእርሷ ደስተኛ ባትሆን፣ ወደምትፈልገው እንድትሄድ ነጻነት ስጣት፤ ውርደት ላይ ጥለሃታልና ልትሸጣት ወይም እንደ ባሪያ ልትቈጥራት አይገባህም።"

፨ ይህ ህግ የተቀመጠው ያለጋብቻ በመዳራት ራሳቸውን እንዳያረክሱ በጊዜያዊ ጋብቻም ቢሆን መታጠር ስላለበት እንደሆነ ብዙ ምሁራኖች ይናገራሉ።

By this law a soldier is allowed to marry his captive if he pleased. For the hardness of their hearts Moses gave them this permission, lest, if they had not had liberty given them to marry such, they should have taken liberty to defile themselves with them, and by such wickedness the camp would have been troubled. The man is supposed to have a wife already, and to take this wife for a secondary wife

"በዚህ ሕግ አንድ ወታደር ደስ ካለው ምርኮኛውን እንዲያገባ ተፈቅዶለታል። ሙሴ ይህንን ፈቃድ የሰጣቸው ስለ ልባቸው ጥንካሬ ነው፤ እንዲህ ያለውን የማግባት ነፃነት ባያገኙ ኖሮ፣ ከእነርሱ ጋር በመዳራት ራሳቸውን ያረክሱ ነበርና፤ በዚህም ክፋት ሰፈሩ ይታወክ ነበር። ሰውየው ቀድሞውኑ ሚስት እንዳለው ይታሰባል፣ ይህቺንም ሚስት ለሁለተኛ ሚስትነት ይወስዳታል።"
📗[ Matthew Henry  ኢንግሊዛዊ የመፅሐፍ ቅዱስ ተርጓሚ እና ምሁር ]

Nothing shows the weakness of the Hebrews more than this liberty, which the law was in a manner forced to allow, to prevent greater evils. The soldier who has married a captive, may abandon her, if he set her free, (Calmet) which was but a slight punishment for his inconstancy.

ሕጉ ይበልጥ የከፉ ጥፋቶችን ለመከላከል ሲባል በሆነ መንገድ እንዲፈቀድ ከተገደደበት ከዚህ ነፃነት በላይ የዕብራውያንን ድክመት የሚያሳይ ምንም ነገር የለም። ምርኮኛ ያገባ ወታደር፣ በነፃ የሚለቃት ከሆነ ሊተዋት (ሊፈታት) ይችላል፤  ይህም ለውሳኔ ቢስነቱ የተሰጠ መጠነኛ ቅጣት ነበር።"
📗[George Leo Haydock የመፅሐፍ ቅዱስ ተርጓሚና ምሁር ]

፨ሊቃውንቱም እንዳስረዱት ይህ ጊዜያዊ ጋብቻ ወታደሮች በጦርነት ወቅት ሊገጥሟቸው ከሚችሉ  የሥነ-መግባር  ውድቀቶች  ለመታደግ መለኮታዊ ፍቃድ ያገኘ የጋብቻ አይነት ነው

፨ቀጥታ የባይብል ሀሳቦችን ከመቀበል ይልቅ በሰባኪያን ትርክቶች ላይ ብቻ ተመስርቶ የመጓዝን ልምድ በመቀየር፣ ወገኖቻችንን  በምክንያታዊነትና በጥልቀት የማንበብን ባህል እንዲያዳብሩ የምናደርገውን ጥረት በአላህ ፍቃድ እንቀጥላለን።"

©
3,46000133
Meweda | Comparison

May 24, 2026, 07:00

አሰላሙ አለይኩም ወራህመቱላሂ ወበረካቱህ

በአላህ ፍቃድ በዚህ ቻናል ሥር ምእመናን ላይ ብዥታ ሊፈጥሩ የሚችሉ ሀሳቦችን እያጠራን፣ ለተቃራኒ ወገኖችም ሙግቶችን በተደራጀ መልኩ እያነሳን ወገኖቻችንን ወደ ኢስላም  የምንጠራ እንዲሁም  'እምነትን በእውቀት' በሚለው መርኃችንም መሠረት በመጓዝ ራሳችንን የምንገነባበት ይሆናል። 
ٱدْعُ إِلَىٰ سَبِيلِ رَبِّكَ بِٱلْحِكْمَةِ وَٱلْمَوْعِظَةِ ٱلْحَسَنَةِ ۖ وَجَٰدِلْهُم بِٱلَّتِى هِىَ أَحْسَنُ ۚ إِنَّ رَبَّكَ هُوَ أَعْلَمُ بِمَن ضَلَّ عَن سَبِيلِهِۦ ۖ وَهُوَ أَعْلَمُ بِٱلْمُهْتَدِينَ
ወደ ጌታህ መንገድ በብልሃትና በመልካም ግሳጼ (በለዘብታ ቃል) ጥራ፡፡ በዚያችም እርሷ መልካም በኾነችው (ዘዴ) ተከራከራቸው፡፡ ጌታህ እርሱ ከመንገዱ የተሳሳተውን ሰው ዐዋቂ ነው፡፡ እርሱም ቅን የኾኑትን ሰዎች ዐዋቂ ነው፡፡
An-Nahl [16:125]

ቻናሉን ሼር በማረግ ተደራሽነቱን ያስፉ። ባረከላሁ ፊኩም።

©
2,78000127

Showing 22 of 22 posts

Rating

Login required

Frequently Asked Questions

What is the Meweda | Comparison Telegram channel about?+

Meweda | Comparison (@MewedaComp) is a Telegram channel in the Religion category. Faith through knowledge [ እምነትን በእውቀት ]

How do I join Meweda | Comparison (@MewedaComp) on Telegram?+

Open the channel profile on tgdio, then use the Join / Open in Telegram button to go to @MewedaComp in the Telegram app or web client and subscribe for free.

Is Meweda | Comparison a good Religion channel to follow?+

On tgdio you can check Meweda | Comparison's rating, user reviews, ranking, and latest posts before joining. It currently lists about 1,974 subscribers on tgdio. Compare it with similar Religion channels in the same category.

Where can I see Meweda | Comparison stats and latest posts?+

On tgdio, open the @MewedaComp channel page for subscriber stats, ranking, ratings, and recent posts. Use the Stats link on the profile for deeper growth and activity charts.