Ethiopia Customs Commission Telegram channel photo

Ethiopia Customs Commission

Ethiopia Customs Commission shares Government Exams updates and media on Telegram. Join to stay updated.

19.2k (19,182 subscribers)
Members
—
Rating
51
Total Posts
Sep 17, 2026, 12:55 AM
Updated
Apr 3, 2026
Created
Stats

You are viewing English content. To see content in other languages, change the language of the site.

Channel Information

Channel Information
Channel NameEthiopia Customs Commission
Username@EthiopiaCustomsCommission
CategoryGovernment Exams
LanguageEnglish
CountryUnited States
Members19,182
Channel TypePublic Channel
CreatedApr 3, 2026
Last UpdatedSep 17, 2026 • 10 days ago
StatusActive

Ranking

Global Ranking
#11080-4
Language Ranking
#2327+2
Category Ranking
#24No change

Participant Growth (Last 16 Days)

Total: 19.2K
24h growth: -386 2%
04/0304/1104/1805/1406/0507/1908/1909/0709/17

Latest Posts

Ethiopia Customs Commission

Sep 09, 2026, 17:29

የጉምሩክ ኮሚሽን እና የኢትዮጵያ ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬሽን በጋራ ለመስራት የሚያስችላቸውን ስትራቴጅካዊ ስምምነት ተፈራረሙ
## ### ### ### ### ### ### ### ### ###
(ጉምሩክ ኮሚሽን፣ ጷጉሜን 4 ቀን 2018 ዓ.ም)

የጉምሩክ ኮሚሽን እና የኢትዮጵያ ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬሽን (EBC) ስትራቴጅካዊ በሆኑ ጉዳዮች ላይ በጋራ ለመስራት የሚያስችላቸውን ስምምነት በዛሬው ዕለት ተፈራርመዋል ።

ስምምነቱን የጉምሩክ ኮሚሽን ኮሚሽነር ደበሌ ቃበታ (ዶ/ር) እና የኢትዮጵያ ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬሽን ዋና ሥራ አስፈጻሚ ቢንያም ኤሮ ፈርመውታል።

የጉምሩክ ኮሚሽን ኮሚሽነር ደበሌ ቃበታ፤የጉምሩክ ኮሚሽን የገቢና የወጪ ንግድ በማሳለጥ እንዲሁም ገቢን በመሰብሰብ የኢትዮጵያን ኹለንተናዊ ብልጽግና ለማረጋገጥ እየተጋ መሆኑን ገልጸዋል።

የህግ ተገዥነትን ለማረጋገጥ እና የአገልግሎት አሰጣጡን ተደራሽ ለማድረግ የግንዛቤ ፈጠራ ሥራዎች ወሳኝ መሆናቸውን ኮሚሽነሩ ገልጸው ይህንን ዕውን ለማድረግ የሚዲያ ሚና አይተኬ ነውም ብለዋል።

የኢትዮጵያ ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬሽን ዋና ሥራ አስፈጻሚ አቶ ቢንያም ኤሮ በበኩላቸው፣ የኢትዮጵያ ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬሽን ህብረ ብሔራዊ አንድነትን ይበልጥ ለማጠናከር የሚያስችሉ ሥራዎችን እየሰራ መሆኑን አስረድተዋል፡

የታክስ እና የጉምሩክ ህግ ተገዥነቱ ያደገ ማህበረሰብን ለመፍጠር የሚያስችሉ ሥራዎችን አጠናክሮ ለማስቀጠል ስምምነቱ ወሳኝ መሆኑንም ዋና ሥራ አስፈጻሚው አብራርተዋል።

ጉምሩክ ኮሚሽንን የተመለከቱ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/ecczena
በድረ ገጽ፦ http://www.ecc.gov.et/
በቴሌግራም፦ https://t.me/EthiopianCustomsCommission
364001
Ethiopia Customs Commission

Sep 09, 2026, 17:29

ኮሚሽኑ የዘመን መለወጫ በዓልን ምክንያት በማድረግ ለ0ቅመ ደካማ ወገኖች ማዕድ አጋራ
### ### ### ### ### ### ### ### ###

(ጉምሩክ ኮሚሽን፣ ጷጉሜን 4 ቀን 2018 ዓ.ም )

በጉምሩክ ኮሚሽን የቃሊቲ ጉምሩክ ቅ/ጽ/ቤት የዘመን መለወጫ በዓልን ምክንያት በማድረግ ለ0ቅመ ደካማ ወገኖች በዛሬው ዕለት ማዕድ አጋርቷል ።

በዚህ ማዕድ ማጋራት መርኃ ግብር የጉምሩክ ኮሚሽን ኮሚሽነር ደበሌ ቃበታ (ዶ/ር)፣ የቃሊቲ ጉምሩክ ቅ/ጽ/ቤት ሥራ አስኪያጅ አቶ አዲስ አየለ እንዲሁም የአቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተማ ከፍተኛ አመራሮች ተገኝተዋል።

የጉምሩክ ኮሚሽን ኮሚሽነር ደበሌ ቃበታ (ዶ/ር )፤ በጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አህመድ (ዶ/ር) አነሳሽነት እየተካሄደ የሚገኘው ማዕድ ማጋራት መርኃግብር ተጠናክሮ መቀጠሉን ጠቁመዋል።

በአቃቂ ቃሊቲ ክ/ከተማ ለሚገኙ ወገኖች የተደረገው የማዕድ ማጋራት መርኃ ግብር አብሮነትን ለማጠናከር ወሳኝ መሆኑንም ኮሚሽነሩ አብራርተዋል።

የአቃቂ ቃሊቲ ክ/ከተማ ምክትል ሥራ አስፈጻሚ አቶ ፈይሳ ፈለቀ በበኩላቸው፤ የጉምሩክ ኮሚሽን በክፍለ ከተማው እየተከናወኑ ለሚገኙ ሰው ተኮር የልማት ሥራዎች አጋዥ መሆኑን ገልጸዋል።

አቶ ፈይሳ አክለውም ፤ ለ0ቅመ ደካማ ወገኖች የተደረገው የማዕድ ማጋራት መርኃ ግብር ኮሚሽኑ የህዝብ አጋር መሆኑን ማሳያ ነውም ብለዋል ።

ጉምሩክ ኮሚሽንን የተመለከቱ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/ecczena
በድረ ገጽ፦ http://www.ecc.gov.et/
በቴሌግራም፦ https://t.me/EthiopianCustomsCommission
349000
Ethiopia Customs Commission

Sep 09, 2026, 17:29

የጉምሩክ እና ሎጂስቲክስ ዘመናዊነት የኢትዮጵያ የንግድ ተወዳዳሪነት እመርታ
*******

በአሁኑ የግሎባላይዜሽን ዘመን የሀገር ንግድ ተወዳዳሪነት የሚለካው በምርቶች ጥራት ብቻ ሳይሆን፣ ለገበያ በሚቀርቡበት ፍጥነት፣ ዝቅተኛ ወጪ እና ቀልጣፋ የአቅርቦት ሰንሰለት ጭምር ነው።

በመሆኑ የጉምሩክ አሠራርና የሎጂስቲክስ ዘመናዊነት ወሳኝ ድርሻ አላቸው። በለውጥ ዓመታት የተተገበሩት የዲጂታል ቴክኖሎጂ ማሻሻያዎች በስራ ላይ በመዋላቸው በእመርታ ቀን የምናከብረውን ሀገራዊ የአምራችነትና የንግድ እመርታ እውን አድርገውታል።

ይህ በእመርታ ቀን የምናበስረው የዘመናዊነት ጉዞ የጉምሩክ ኮሚሽን የአንድ መስኮት አገልግሎትን በመዘርጋት አስመጪዎችና ላኪዎች ፈቃዶችን፣ ሰነዶችንና ክፍያዎችን በአንድ የተቀናጀ የኦንላይን ፕላትፎርም እንዲፈጽሙ በማድረግ ጊዜና ወጪን በእጅጉ ቀንሶላቸዋል።

በአርቴፊሻል ኢንቴሊጀንስ እና በአደጋ ተኮር የፍተሻ ዘዴዎች ህጋዊና ዝቅተኛ ስጋት ያላቸውን እቃዎች ያለ ረጅም ወረፋ ማሳለፍ የተቻለ ሲሆን፣ የጉምሩክ ፍተሻዎችን ወደ ደረቅ ወደቦች በማዛወር በድንበር አካባቢ የሚፈጠርን እንግልት ማስቀረት ተችሏል።

የየብስ፣ የባቡር፣ የባሕርና የአየር ትራንስፖርትን ያቀናጀ የባለብዙ አማራጭ ሎጂስቲክስ አውታር መዘርጋቱ እና ከጎረቤት ሀገራት ጋር የአንድ ማዕከል የድንበር አገልግሎት መተግበሩ የንግድ ፍሰቱን አፋጥኖታል።

እነዚህ እርምጃዎች የሀገር ውስጥ ምርቶች በዓለም አቀፍ ገበያ ያላቸውን ተወዳዳሪነት በመጨመር ለኢኮኖሚ እድገቱ ከፍተኛ አቅም በመሆናቸው አዲስ እመርታ መመዝገቡን ያመላክታል።
2,540009
Ethiopia Customs Commission

Sep 09, 2026, 17:29

የኢትዮጵያ የገቢ እና የታክስ ሥርዓት ታሪካዊ የእመርታ ጉዞ ከቢሊዮን ወደ ትሪሊዮን
*****

ሀገራችን ኢትዮጵያ ባለፉት የለውጥ ዓመታት በየዘርፉ የምታስመዘግባቸው ሁለንተናዊ ስኬቶች እና የብልጽግና ማሳያዎች መካከል የሀገር ውስጥ ገቢ አሰባሰብ እና የታክስ ሥርዓት ትራንስፎርሜሽን በግንባር ቀደምትነት ይጠቀሳል።

የኢኮኖሚ ሉዓላዊነትን ለማረጋገጥ እና ግዙፍ ሀገራዊ የልማት ፕሮጀክቶችን በራስ አቅም ለመሸፈን በሚደረገው ጥረት፣ የገቢ አሰባሰብ አቅምን ከቢሊዮን ወደ ትሪሊዮን ብር ማደጉ ትልቅ ታሪካዊ ምዕራፍ ነው።

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) የ2018 በጀት ዓመት ሪፖርት ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ባቀረቡበት ወቅት እንደገለጹት፣ ሀገራችን ባለፉት 27 ዓመታት በአጠቃላይ የሰበሰበችው ገቢ 1 ትሪሊዮን ብር እንኳን የማይሞላ የነበረ ቢሆንም፣ በ2018 በጀት ዓመት ብቻ ግን 1.5 ትሪሊዮን ብር ገቢ በመሰብሰብ ከ150% በላይ ታሪካዊ ብልጫ ያለው እመርታ ማስመዝገብ ተችሏል።

ይህ የገቢ ማደግ እንደ ኮሪደር ልማት፣ የትምህርትና ጤና መሰረተ ልማቶች እንዲሁም የታላቁ ሕዳሴ ግድብ ግንባታን በራስ አቅም ለመሸፈን የሚያስችል ጠንካራ የፋይናንስ ነፃነት እና ኢኮኖሚያዊ መሰረት ፈጥሯል።

ለዚህ ታሪካዊ የገቢ እድገት እና እመርታ ዋናው ስኬት የግብር አሰባሰቡን አሠራር በዲጂታል ቴክኖሎጂ ማደራጀት እና ማዘመን ነው።

በሀገራችን የተጀመረው የኤሌክትሮኒክ ታክስ (ኢ-ታክስ) አጠቃቀም በስፋት ሥራ ላይ በመዋሉ ግብር ከፋዩ ኅብረተሰብ በየቢሮው በሰልፍ ያሳልፍ የነበረውን ጊዜና ወጪ በመቀነስ ባሉበት ሆነው በጥቂት ደቂቃዎች ውስጥ የታክስ ማሳወቂያ እንዲያቀርቡና ክፍያቸውን እንዲፈጽሙ አስችሏል።

ይህ አሠራር የአካል ንክኪንና ባህላዊ ቢሮክራሲን በማስቀረት የታክስ ስወራን፣ መዘግየቶችን እና ህገ-ወጥ አሠራሮችን በእጅጉ ቀንሷል።

የፖስ እና የኢ-ኮመርስ አሠራሮችን በቀጥታ ከገቢዎች ሚኒስቴር የመረጃ ቋት ጋር ማያያዝ መቻሉ በስርዓቱ ላይ ግልጽነትን የፈጠረ ሲሆን፣ ነጋዴውና ባለሀብቱ በታክስ ሂደቶች ላይ ያባክኑ የነበረውን ጉልበት ወደ ዋናው የምርታማነት ሥራቸው እንዲያዞሩ በማድረግ ለሀገር ውስጥ ምርት ማደግ ከፍተኛ አስተዋፅኦ አበርክቷል።

ከዲጂታል አሠራር ጎን ለጎን የግብር አሰባሰቡን በህግ ከማስገደድ ይልቅ በፈቃደኝነት ላይ ወደተመሰረተ የታክስ ባህል ማሸጋገር መቻሉ ሌላው እመርታ ነው።

ቀደም ሲል በግብር ሰብሳቢው እና በግብር ከፋዩ መካከል የነበረውን በፍርሃትና በጥርጣሬ የተሞላ ግንኙነት በመቀየር፣ ህዝባዊ ንቃተ-ህሊናን የሚያሳድጉ የዲጂታል ሚዲያ ዘመቻዎች፣ የምክክር መድረኮች እና በትምህርት ካሪኩለም ውስጥ የታክስ እውቀትን ማካተት የተቻሉ ስራዎች ተከናውነዋል።

ታማኝና ከፍተኛ ግብር ከፋዮችን በጠቅላይ ሚኒስትር ደረጃ ማሸለም አዎንታዊ ውድድርን የፈጠረ ሲሆን፣ ህዝቡም ገቢዎች ሚኒስቴርን የጋራ ሀብት አስተዳዳሪ አድርጎ የመመልከትና በራሱ ፍላጎት ግብሩን የማወጅ ልምዱ አድጓል።

በተጨማሪም የታክስ መሠረቱን በማስፋት፣ አዳዲስ የንግድ ዘርፎችን ወደ ፋይናንስ ሥርዓቱ በማስገባት እና ህጋዊ የሽያጭ ደረሰኝ የመጠየቅ ባህል እንዲጎለብት በማድረግ አስተማማኝ የገቢ መሠረት ተጥሏል።

ይህንን የታክስ እና የገቢ እመርታ ሙሉ ለማድረግ የኮንትሮባንድ ንግድ ቁጥጥር እና የጉምሩክ አሠራር ዘመናዊነት ከፍተኛ ድርሻ ተጫውተዋል።

እንደ ቡና፣ ሰሊጥ፣ ወርቅ እና የቀንድ ከብቶች ያሉ ስትራቴጂካዊ ምርቶች በህገ-ወጥ መንገድ እንዳይወጡ በማድረግ ሀገር ማግኘት የሚገባትን የውጭ ምንዛሪ እንድታገኝ ተደርጓል።

በሌላ በኩል በጉምሩክ ኬላዎች ላይ የኤክስሬይ ስካነሮችን፣ የካርጎ ክትትል ቴክኖሎጂዎችን እና በሰው ሰራሽ አስተውሎት የተደገፉ የፍተሻ ዘዴዎችን በመተግበር ህገ-ወጥ እቃዎችን በመቆጣጠር የሀገር ውስጥ አምራቾች ተጠብቀዋል።

የጉምሩክ ኮሚሽን ከአንድ መስኮት አገልግሎት እና ከባለብዙ አማራጭ ሎጂስቲክስ አውታር ጋር በመቀናጀት የድንበር ንግድን በማፋጠን የሀገራችንን የንግድ ተወዳዳሪነት አሳድጓል።

እነዚህ የተቀናጁ የገቢ፣ የታክስ፣ የዲጂታላይዜሽን እና የጉምሩክ ማሻሻያዎች ኢትዮጵያ በፅኑ መሰረት ላይ የቆመች እና በራስ አቅም የምትመራ የበለጸገች ሀገር ለመሆን ያደረገችውን ታሪካዊ የእመርታ ጉዞ በግልጽ ያሳያሉ።
2,190004
Ethiopia Customs Commission

Aug 25, 2026, 14:11

በህገ-ወጥ መንገድ ሲዘዋወር የነበረ አራት ኪ.ግ ጥፍጥፍ ወርቅ በቁጥጥር ስር ዋለ
### ### ### ### ### ### ### ###
(ጉምሩክ ኮሚሽን፣ ነሀሴ 9 ቀን 2018 ዓ.ም )

በጉምሩክ ኮሚሽን አዲስ አበባ ኤርፖርት ጉምሩክ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት በህገ-ወጥ መንገድ ሲዘዋወር የነበረ አራት ኪ.ግ ጥፍጥፍ ወርቅ በዛሬው ዕለት በቁጥጥር ስር ውሏል፡፡

በህገ-ወጥ መንገድ ሲዘዋወር የነበረው ጥፍጥፍ ወርቅ የተያዘው ፤ ከዱባይ ወደ ኢትዮጵያ በተደረገ የበረራ ፕሮግራም ተሳፋሪ የሆነ ግለሰብ በለበሰው ውስጥ ሱሪ በመደበቅ ለማሳለፍ ሲሞክር በተደረገ አካላዊ ፍተሻ ነው።

ተጠርጣሪው የተያዘው በአዲስ አበባ ኤርፖርት ጉምሩክ ቅ/ጽቤት አመራሮች እና ባለሙያዎች ባደረጉት ክትትል እና አካላዊ ፍተሻ ሲሆን በህግ ጥላ ስር ሆኖ ተጨማሪ ምርመራ እየተደረገበት ይገኛል፡፡

የጉምሩክ ኮሚሽን በዚህ የህግ ማስከበር ስራ ላይ ለተሳተፉ የአዲስ አበባ ኤርፖርት ጉምሩክ አመራር እና ሰራተኞች ምስጋናውን ያደርሳል፡፡

ኮንትሮባንድ እና ህገወጥ ንግድ የአፈጻጸም ስልቱ ተለዋዋጭ በመሆኑ ድርጊቱን ለመግታትና በሀገር ኢኮኖሚ የሚያሳድረውን ተጽእኖ ለመከላከል ጉምሩክ ኮሚሽን ብቻ የሚያደርገው እንቅስቃሴ በቂ ባለመሆኑ ሁሉም ባላድርሻ አካላትና ህብረተሰቡ የበኩሉን ድርሻ እንዲወጣ የጉምሩክ ኮሚሽን ጥሪውን ያቀርባል፡፡

ጉምሩክ ኮሚሽንን የተመለከቱ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/ecczena
በድረ ገጽ፦ http://www.ecc.gov.et/
በቴሌግራም፦ https://t.me/EthiopianCustomsCommission
5,1300016
Ethiopia Customs Commission

May 25, 2026, 01:39

ከ515 ሚሊዮን ብር በላይ ግምታዊ ዋጋ ያላቸው የኮንትሮባንድ እቃዎች በቁጥጥር ስር ዋሉ
### ### ### ### ### ### ### ### ### ###
(ጉምሩክ ኮሚሽን፣ ግንቦት 14 ቀን 2018 ዓ.ም )
የጉምሩክ ኮሚሽን ከግንቦት 6 እስከ ግንቦት 12 ቀን 2018 ዓ.ም ባደረገው ክትትል 484 ሚሊዮን ብር የገቢ የኮንትሮባንድ እቃዎች እና 31.2 ሚሊዮን ብር የወጭ፤ በድምሩ 515.2 ሚሊዮን ብር ግምታዊ ዋጋ ያላቸው የኮንትሮባንድ እቃዎች በተለያዩ ቅርንጫፍ ጽህፈት ቤቶች ተይዘዋል፡፡

በቁጥጥር ስር ከዋሉት የኮንትሮባንድ እቃዎች መካከል አዳዲስ እና ልባሽ ጨርቆች፣ ኤሌክትሮኒክስ፣ የግብርና ምርቶች፣ የተሽከርካሪ መለዋወጫ፣ የመዋቢያ እቃዎች፣ ጫት፣ አደንዛዥ እጾች፣ መድኃኒት፣ ማዕድናት፣ ነዳጅ፣ የቁም እንስሳት እና የውጭ ሀገር ገንዘቦች ይገኙበታል፡፡

በተጠቀሰው የጊዜ ገደብ የገቢ እና የወጭ ኮንትሮባንድን በመቆጣጠር ድሬድዋ፣ ሞያሌ እና ጅግጅጋ ጉምሩክ ቅርንጫፍ ጽህፈት ቤቶች ቀዳሚውን ስፍራ ሲይዙ በቅደም ተከተላቸውም 114 ሚሊዮን፣ 113 ሚሊዮን እና 73 ሚሊዮን ብር ግምታዊ ዋጋ ያላቸው የኮንትሮባንድ እቃዎችን መያዝ ችለዋል፡፡

የኮንትሮባንድ ዕቃዎቹ በጉምሩክ ኮሚሽን ሰራተኞች፣ በፌደራል ፖሊስ፣ በክልል ፖሊስ አባላትና ህብረተሰቡ ባደረጉት የጋራ ጥረት በፍተሻ፣ በጥቆማ እና በበረራ የተያዙ ሲሆን የኮንትሮባንድ እቃዎቹን ሲያዘዋውሩ የተገኙ 27 ተጠርጣሪዎች እና 14 ተሽከርካሪዎችም በቁጥጥር ስር ውለዋል፡፡

የጉምሩክ ኮሚሽን በዚህ የህግ ማስከበር ስራ ላይ ለተሳተፉ የኮሚሽኑ ሰራተኞች እና አመራሮች፣ የክልልና የፌደራል ፖሊስ አባላት እንዲሁም ለመላው ህዝባችን ምስጋናውን ያደርሳል፡፡

ኮንትሮባንድ እና ህገወጥ ንግድ የአፈጻጸም ስልቱ ተለዋዋጭ በመሆኑ ድርጊቱን ለመግታትና በሀገር ኢኮኖሚ የሚያሳድረውን ተጽእኖ ለመከላከል ጉምሩክ ኮሚሽን ብቻ የሚያደርገው እንቅስቃሴ በቂ ባለመሆኑ ሁሉም ባላድርሻ አካላትና ህብረተሰቡ የበኩሉን ድርሻ እንዲወጣ የጉምሩክ ኮሚሽን ጥሪውን ያቀርባል፡፡

ጉምሩክ ኮሚሽንን የተመለከቱ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/ecczena
በድረ ገጽ፦ http://www.ecc.gov.et/
በቴሌግራም፦ https://t.me/EthiopianCustomsCommission
1,970006
Ethiopia Customs Commission

May 25, 2026, 01:39

የሴቶችና ወጣቶችን ሁለንተናዊ አቅም ለማጎልበት የሚያስችሉ የተለያዩ ሥራዎች እየተከናወኑ መሆኑ ተገለጸ
*****************************************************
(ጉምሩክ ኮሚሽን፣ ግንቦት 12 ቀን 2018 ዓ.ም

የጉምሩክ ኮሚሽን የሴቶች እና ማህበራዊ ጉዳይ ዳይሬክቶሬት ከዋናው መስሪያ ቤት እና ከቅርንጫፍ ጽ/ቤቶች ከተወጣጡ የዘርፉ አመራር እና ባለሙያዎች ጋር ውይይት እያደረገ ይገኛል።

የሴቶች እና ማህበራዊ ጉዳይ ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር ወ/ሮ ማንጠግቦሽ ከበደ፤ ባለፉት አስር ወራት በኮሚሽኑ እያገለገሉ የሚገኙ ሴቶች፣ ወጣቶች እና የአካል ጉዳተኞችን መረጃ የማደራጀት እና የመተንተን ሥራዎች መከናወኑን ገልጸዋል።

ሴቶች እና ወጣቶች ወደ አመራር እርከን እንዲመጡ ለማድረግም በውስጥ እና በውጪ ዓቅም ተከታታይ የዓቅም ግንባታ ሥልጠናዎች መሰጠታቸውን ወ/ሮ ማንጠግቦሽ አስረድተዋል።

ሴት አመራር እና ባለሙያዎች ከስራ ገበታቸው ሳይነጠሉ የተሰጣቸውን ተልዕኮ በአግባቡ እንዲወጡ ለማስቻልም በዋናው መስሪያ ቤት እና በቅርንጫፍ ጽ/ቤቶች የህጻናት ማቆያ ማዕከል ተከፍቶ ተገቢውን አገልግሎት እየሰጠ መሆኑንም ዳይሬክተሯ ጠቁመዋል።

የኮሚሽኑን ርዕይ እና የተያዙ ዕቅዶች ማሳካት የሚቻለው ጤናው የተጠበቀ አመራር እና ባለሙያ ሲኖር ነው ያሉት ወ/ሮ ማንጠግቦሽ ፤ የተመቻቸ የጤና እና ስፖርታዊ ውድድሮች እየተካሄዱ መሆኑን ተናግረዋል።

በኮሚሽኑ የስርዓተ ፆታ አካታችነት እና ተሳታፊነት ለማረጋገጥ የተጀመሩ ተግባራት ተጠናክሮ ለማስቀጠል ትኩረት ተሰጥቶ እየተሰራ እንደሆነም የሴቶች እና ማህበራዊ ጉዳይ ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር ወ/ሮ ማንጠግቦሽ ከበደ አስገንዝበዋል።

ጉምሩክ ኮሚሽንን የተመለከቱ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/ecczena
በድረ ገጽ፦ http://www.ecc.gov.et/
በቴሌግራም፦ https://t.me/EthiopianCustomsCommission
2,3100013
Ethiopia Customs Commission

May 25, 2026, 01:39

በጉምሩክ ኮሚሽን የተተገበሩ የሪፎርም ስራዎች ተስፋ ሰጭ እና ያስቀመጠውን ርዕይ ለማሳካት የሚያስችሉ መሆናቸውን ምሁራን ገለጹ
****************************************
(ጉምሩክ ኮሚሽን፣ ግንቦት 13 ቀን 2018 ዓ.ም )
በጉምሩክ ኮሚሽን የተተገበሩ የሪፎርም ስራዎች ተስፋ ሰጭ እና ያስቀመጠውን ርዕይ ለማሳካት የሚያስችሉ መሆናቸውን የአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ መምህራን እና ትምህርታቸውን በተለያዩ የቢዝነስ ዘርፎች በሶስተኛ ዲግሪ እየተማሩ የሚገኙ ተማሪዎች ገልጸዋል፡፡

በአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ በምክትል ፕሬዝዳንት ማዕረግ የፕሬዝዳንት ጽ/ቤት ኃላፊ ፕሮፌሰር ማቴዎስ እንሰርሙ መሪነት በዩኒቨርስቲው በInternational business and strategy እና በLogistics and supply chain management የትምህርት መስክ የሶስተኛ ዲግሪ ትምህርታቸውን እየተከታተሉ የሚገኙ ተማሪዎች በጉምሩክ ኮሚሽን ዋናው መስሪያ ቤት ትምህርታዊ ጉብኝት አድርገዋል፡፡

በጉብኝቱ ማጠቃለያ የጉምሩክ ኮሚሽን ታሪካዊ ዳራ፣ የተሰጡትን ተግባራት እና ኃላፊነቶች እንዲሁም ባለፉት ዓመታት የተተገበሩ የለውጥ ስራዎችን አስመልክቶ በድህረ ዕቃ አወጣጥ ኦዲት ማዕከል ኃላፊ በአቶ መንግስቱ ተፈራ ገለጻ ተደርጎላቸዋል፡፡

የጉምሩክ ኮሚሽን ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ተሰማ ኢዲኤ፣ ኮሚሽኑ የተሰጠውን ተልዕኮ እና የያዛቸውን ዕቅዶች ለማሳካት ከተለያዩ መንግስታዊ እና መንግስታዊ ካልሆኑ ተቋማት ጋር በቅንጅት እየተሰራ መሆኑን ጠቁመዋል፡፡
ከአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ ጋር ስትራቴጂካዊ አጋርነት በመፍጠር እየተሰራ ነው ያሉት ኃላፊው በዩኒቨርስቲው የንግድ ስራ ትምህርት ቤት የጉምሩክ የልህቀት ማዕከል ተቋቁሞ አገልግሎት እየሰጠ እንደሆነም አስረድተዋል፡፡

አቶ ተሰማ አክለውም፣ ኮሚሽኑ ለጥናት እና ምርምር ስራዎች ልዩ ትኩረት እንደሚሰጥ እና ጉምሩክ ነክ በሆኑ ጉዳዮች ላይ ጥናትና እና ምርምር ለሚያደርጉ የዩኒቨርስቲው ምሁራን እና ተማሪዎች አስፈላጊው ድጋፍ እንደሚደረግም አስገንዝበዋል፡፡

በአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ በምክትል ፕሬዝዳንት ማዕረግ የፕሬዝዳንት ጽ/ቤት ኃላፊ ፕሮፌሰር ማቴዎስ እንሰርሙ በበኩላቸው፣ በጉምሩክ ኮሚሽን የተተገበሩ የሪፎርም ስራዎች ተስፋ ሰጭ እና ያስቀመጠውን ርዕይ ለማሳካት የሚያስችሉ መሆናቸውንም ተናግረዋል፡፡

የኮሚሽኑ አመራር እና ባለሙያዎች እውቀት የታጠቁ እና ዘመኑን የዋጁ እንዲሆኑ ለማስቻልም ዩኒቨርስቲው ተከታታይ የሆኑ የዓቅም ግንባታ ሥልጠናዎችን እየሰጠ ነውም ብለዋል፡፡

ትምህርታዊ ጉብኝት ያደረጉት የዩኒቨርስቲው ተማሪዎች በሰጡት አስተያየት፣ በጉምሩክ ኮሚሽን የተመለከቷቸው የለውጥ ስራዎች አስደማሚ እና ከዚህ በፊት የነበራቸውን አሉታዊ አመለካከት የቀየረ መሆኑን አስገንዝበዋል፡፡

ጉምሩክ ኮሚሽንን የተመለከቱ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/ecczena
በድረ ገጽ፦ http://www.ecc.gov.et/
በቴሌግራም፦ https://t.me/EthiopianCustomsCommission
1,660002
Ethiopia Customs Commission

May 10, 2026, 14:19

የቀረጥ እና ታክስ ግንዛቤን በላቀ ደረጃ ለማሳደግ የተለያዩ የተግባቦት ዘዴዎችን መተግበር እንደሚገባ ተገለጸ
### ### ### ### ### ###

(ጉምሩክ ኮሚሽን፣ ሚያዚያ 30 ቀን 2018 ዓ.ም )

የገቢዎች ሚኒስቴር ታክስ ቶክ ፓድካስት ስቱዲዮ ፤ የገቢዎች ሚኒስቴር፣ የጉምሩክ ኮሚሽን አመራሮች እና ከተለያዩ ተቋማት ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች በተገኙበት በዛሬው ዕለት ተመርቋል።


በስቱዲዮ ምርቃቱ የተገኙት የገቢዎች ሚኒስትር ዓይናለም ንጉሴ ፤ ወቅታዊ የግብር መረጃዎችን፣ የፖሊሲ ማሻሻያዎችን እና የታክስ አስተዳደር ስርዓቶችን በማህበረሰቡ ውስጥ ለማስረጽ በርካታ ተግባራት እየተከናወኑ መሆኑን ገልጸዋል::


በተለይም በማህበረሰቡ ውስጥ ያለውን የቀረጥ እና ታክስ ግንዛቤን በላቀ ደረጃ ለማሳደግ የተለያዩ የተግባቦት ዘዴዎችን መተግበር እንደሚገባም አስረድተዋል።


"ታክስ ቶክ ፓድካስት " መረጃን በቀላል መንገድ ለማስተላለፍ ከፍተኛ አስተዋጽዖ እንደሚያበረክት የተናገሩት ሚኒስትሯ ይህ የተግባቦት አማራጭ ግብር ከፋዮች ጭምር የሚሳተፉበት የሁለትዮሽ የውይይት መድረክ እንደሚሆንም አብራርተዋል።


ጉምሩክ ኮሚሽንን የተመለከቱ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/ecczena
በድረ ገጽ፦ http://www.ecc.gov.et/
በቴሌግራም፦ https://t.me/EthiopianCustomsCommission
1,690007
Ethiopia Customs Commission

Apr 28, 2026, 01:04

የጉምሩክ መጋዘን ሥነ-ሥርዓት

“የጉምሩክ መጋዘን” ማለት የትራንዚት ሂደት ያጠናቀቁ ዕቃዎች የሚከማቹበት መጋዘን ሲሆን ዕቃዎቹ በመጋዘኑ ውስጥ እንዳሉ ተገቢው የእቃ አወጣጥ የጉምሩክ ሥነ-ስርዓት ተፈጽሞባቸው ሲጠናቀቅ ከመጋዘኑ የሚወጡበት አሰራር ነው፡፡

የገቢ/የወጪ ወይም ተላላፊ ዕቃዎች የጉምሩክ ሥነ-ስርዓት አፈጻጸም ተከናውኖባቸው እስከሚለቀቁ ድረስ እንዲሁም የጉምሩክ ሕግ በመተላለፍ ተይዘው የተወረሱ ወይም የተተው ዕቃዎች በሽያጭ ወይም በሌሎች የማስወገጃ አማራጮች እስከሚወገዱ ድረስ ደህንነታቸው ተጠብቆ የሚቆዩበት መጋዘን ነው፡፡

በጉምሩክ ቁጥጥር ስር ሆነው የሚቆዩበት ደረቅ ወደብን ጨምሮ ዝግ ወይም ክፍት የዕቃ ማከማቻ ሥፍራ ሊሆን ይችላል፡፡

የጉምሩክ መጋዘን አስፈላጊነት
• ቀረጥና ታክስ ተከፍሎባቸው ለአገልግሎት እስከሚተላለፉ ድረስ ደህንነታቸውን ጠብቆ ለማቆየት፤
• የታክስ እፎይታ ለመስጠት፤
• የግሎባል የጭነት አገልግሎቶችን ለማቀናጀት፤
• የቀረጥና የታክስ የክፍያ ሞዳሊቲ ለማሳለጥ፤
• የጭነት አገልግሎት ለሚሰጡ ድርጅቶች ፈጣን አገልግሎት ለመስጠት፤
• ለላኪዎችና አስመጪዎች የተሳለጠ አገልግሎት ለመስጠት፤
• የጉምሩክ ህግ ተላልፎ የተወረሱ ዕቃዎችን እስኪወገዱ ድረስ ደህንነታቸዉን ጠብቆ ለማቆየት ያገለግላል፡፡
1,830009

Showing 30 of 51 posts

Rating

Login required

Frequently Asked Questions

What is the Ethiopia Customs Commission Telegram channel about?+

Ethiopia Customs Commission (@EthiopiaCustomsCommission) is a Telegram channel in the Government Exams category. Ethiopia Customs Commission shares Government Exams content on Telegram.

How do I join Ethiopia Customs Commission (@EthiopiaCustomsCommission) on Telegram?+

Open the channel profile on tgdio, then use the Join / Open in Telegram button to go to @EthiopiaCustomsCommission in the Telegram app or web client and subscribe for free.

Is Ethiopia Customs Commission a good Government Exams channel to follow?+

On tgdio you can check Ethiopia Customs Commission's rating, user reviews, ranking, and latest posts before joining. It currently lists about 19,182 subscribers on tgdio. Compare it with similar Government Exams channels in the same category.

Where can I see Ethiopia Customs Commission stats and latest posts?+

On tgdio, open the @EthiopiaCustomsCommission channel page for subscriber stats, ranking, ratings, and recent posts. Use the Stats link on the profile for deeper growth and activity charts.